>

ህወሀት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቃ ብትከለከልም "ማነው ከልካዩ!" እያለች ነው  (ፋሲል የኔአለም) 

ህወሃቶችና አጫፋሪዎቻቸው የአብይን መንግስት የሙርሲ መንግስት እያሉ መጥራት ጀምረዋል፥ አብይ በምስራቁና በሰሜን ያለውን ጦር ቢፈትሸው መልካም ነው ፣ ወታደሩና ደህንነቱ ላይ አይኑን ማንሳት የለበትም፥ አንዳንድ ጉብኝቶች ቢዘገዩ   ወይም ሌሎች ቢላኩ ይሻላል።

በየቦታው የሚለኮሱት ግጭቶች አላማ አብይን ሙሃመድ ሙርሲ አድርጎ ለማሳየትና ለሚወሰደው እርምጃ መንገድ ለማመቻቸት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ የ አል ሲሲ አካሄድ በአገራችን እንዲደገም አንፈቅድም፥

ህወሃት አብይን የማስወገድ አላማዋን ለማሳካት እሁድ በአዲስ አበባ ለማድረግ ያሰበችው የተቃውሞ ሰልፍም ብዙ መዘዞችን ይዞ ሊመጣ ይችላል። ህወሃት ከትግራይ ክልል ሳይቀር ሰዎችን ለማምጣት አስባለች። ለዚህ ስራ ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቧል። በየክልሉ በወኪሎቿ የምታስነሳው ተቃውሞና የምታወጣው መግለጫ አልበቃ ብሎ፣  አሁን ደግሞ  ዋና ከተማው ላይ  ከአዲሱ መንግስት ጋር በቀጥታ ለመፋለም መቁረጧን ያሳያል ። የአብይ መንግስት የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ መከልከሉ ተሰምቷል፣ ህወሃት በበኩሏ ማንም የሚከለክለኝ የለም እያለች ነው። አጋጣሚው ወደ ግጭት ካመራ በጸጥታ ማስከበር ስም ብዙ ያልተጠበቁ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉና የአዲስ አበባ ህዝብ ጉዳዩን በንቃት መከታተል ይኖርበታል ።
ወሃት የ 90  ሚሊዮን ህዝብ ጉልበት ሳያርፍባት ቆም ብላ ብታስብ ይሻላታል:።
Filed in: Amharic