ሰላም ለሁላችሁም

ይሄ በእቅፌ ላይ የምታዩት ህጻን ማቲ አበበ ይባላል የዛሬ አራት ኣመት ወደ ሎንዶን በሄድኩበት ጊዜ በአንድ የቤተሰብ ምሽት ነው የተዋወኩት ::
ሳየው እንደ ልጆች አይስቅም አይጫወትም ለምንድን ነው ብየ እናቱን ስጠይቃት እሷና ባሏ( አበበ ወንድማገኝ) ከጋብቻቸው በኋላ ልጃቸውን ለቤተሰቦቻቸው ለማሳየት ወደ ኢትዮጵያ በሄዱበት ጊዜ አበበን “የግንቦት 7 “አባል ነህ በማለት በህጻን ልጁ ፊት እጁን ወደ ኋላ አስረው በፊቱ ላይ ቦንብ ደርድረው በቪዲዮ ከቀረጹት በኋላ እሱን ወደ ማእከላዊ ህጻኑን ማቲንና እናቱን ደግሞ ወደ እንግሊዝ ዲፖርት አደረጓቸው :: በመጨረሻም በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ መስክር ሲሉት በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ የ11 ኣመት እስራት ፈረዱበት::
ዛሬ ወንድማገኝ አበበ መፈታቱን ሰማሁ ያኔ ማቲን ለማሳቅ ብዙ ቀልድና ብዙ ነገር ሞክሪያለሁ ዛሬ ግን ማቲ ለመሳቅ የእኔ ቀልድ ሳይሆን የአባቱን ፊት ብቻ ማየት ይበቃዋል። እስከዳርና ማቲ እግዚአብሄር እንኳን መከራችሁን አሳጠረው
– ህወሀት ወያኔ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬዋለሁ በሎ በግፍ ያሰረውን አበበ ወንድማገኝን ቢፈታም ከቤተሰቡ ጋር ሊቀላቀል አልቻለም በዜግነት እንግሊዛዊ በመሆኑ ለኤምባሲ ነው የምናስረክበው እያለ ነው ።
– ሌላው