>

ወቅታዊ ጥሪ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትና ጸጥታ አስከባሪ ሃይሎች ( ሃራ አብዲ)

ወቅታዊ ጥሪ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትና ጸጥታ አስከባሪ   ሃይሎች

(በመጠኑ የተከለሰ ሁለተኛ  እትም)

( ሃራ አብዲ)

‘…ይሁን እንጂ ህወሓት እና የትግራይን ህዝብ ለማዳከም እና ለመምታት በተለያዩ መንገዶች ፀረ ትግራይ ህዝብ እና ፀረ ህወሓት እንቅስቃሴ የሚያድርጉ የውስጥም የውጭም ሀይሎች ህዝቡ አምርሮ እንዲታግላቸው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል።’ (ከህወሃት መግለጫ የተወሰደ)

 ‘በሃገራችን ህገ መንግስት በሚገባ መልስ የሰጠባቸው የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎችን ፈደራላዊ ስርዓታችን በመፃረር እና የህዝባችን ክብር በሚነካ መልኩ በሀይል እና በተፅእኖ የትግራይ እና ህዝብ አድነት እና ሰላም ለመረበሽ እየተደረጉ ያሉት ፀረ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሶች ህወሓት ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅናት ለመታገል ወስኗል።’(ከህወሃት መግለጫ የተወሰደ

ከላይ የተገለጸዉ የህወሃት አቅዋም በቀላሉ ሊታይ የማይገባ ብቻም ሳይሆን። እጅጉን አሳሳቢም ጭምር ነዉ!!!

ለመላዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት

ለመላዉ የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ስራዊት

ለመላዉ የሀገር ደህንነትና ጥበቃ አባላት

ለመላዉ የክልሎች ልዩ ፖሊስ አባላት

በማንኛዉም የሀገራችን መለዮ ለባሽ የእዝ ሰንሰለት ለምታገለግሉ

በየትኛዉም ስፍራና የሙያ መስክ ላይ የተሰማራችሁ የቀድሞ ሀገር ወዳድ መለዮ ለባሾች

ህወሃት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ አደጋ መቃጣቱን ተከትሎ የቀረበ አስቸኩዋይ ጥሪ።

ህወሃት ገና እግሩ ቤተመንግስት ሲረግጥ የፈጸመዉ ቁጥር አንድ ወንጀል ከአፍሪካ አንደኛ የነበረዉን የሀገር ዋልታ መለዮ ለባሽ በትኖ ሜዳ ላይ መጣል ነበር። በዚህም፤ ጀግናዉ ሰራዊታችን ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት እንደተዳረገ የቅርብ ጊዜ ትዉስታችን ነዉ። አሁንም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ መኮንኖችን ከላይ ሆነዉ ሰራዊቱን እንዲቆጣጠሩ እየመደበ ፤ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑት በተለይ የአማራና የኦሮሞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቀጥታ ከሚያዙት ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ ለሙያቸዉ በማይመጥን ሁኔታ ከእዝ መስመር እያወጣቸዉ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የዜግነት መንፈስ በዉስጣቸዉ በሌለባቸዉ ይልቁንም ትግራይ ራስዋን የቻለች ሀገር ይመስል ትግራይና ኢትዮጵያ እኩል ናቸዉ በሚሉ ከሃዲና ዘረኛ የትግራይ ተወላጆች  የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ወድቃለች።

ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ሀገራችንን በብረት ክንድ ረግጦ በመግዛት ላይ ያለዉ ህወሃት፤ በሀገራችንና በህዝባችን ላይ ይህ ነዉ የማይባል ሰቆቃ የፈጸመዉና በመፈጸምም ላይ ያለዉ ኢትዮጵያን እንደ ሀገሩ፣ ህዝቡዋን እንደ ወገኑ ስለማያይ ነዉ። ህወሃት የተመሰረተበት አላማም በግልጽ በማኒፌስቶዉ ላይ እንደሰፈረዉ የትግራይን ህዝብ ሲጨቁን የኖረዉ የአማራ ብሄር ነዉ በማለት አማራዉንና የአማራዉ ሃይማኖት ነዉ የሚለዉን የኦርቶዶክስ ክርስትና ለማጥፋት ነዉ። ከዚያም ቢሳካለት ትግራይን በሃይል በመገንጠል ከኤርትራ ጋር በማደባለቅ የትግራይ ትግርኝን መንግስት በመመስረት በደስታና በተድላ ለመኖር ነበር። ይህ እዉነታ ቀደም ሲል ህወሃትን ያገለገሉና በትጥቅ ትግሉም ሆነ ከዚያ በሁዋላ ህወሃትን አሳምረዉ የሚያዉቁት እነ አቶ አብርሃም ያየህ፣ እነ አቶ ገበረመድህን አርአያ ና ሌሎችም ለእዉነት የቆሙ የትግራይ ተወላጆች በጥልቀት ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነዉ።

      ትግራይን ከኤርትራ ጋር አዋህዶ ትግራይ ትግርኝን መመስረት የቀንና የለሊት ሃሳባቸዉ ቢሆንም ሊሳካላቸዉ አልቻለም። ምንም እንኩዋን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኤርትራ ጋር ለመታረቅ አማላጅ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም ከንቱ ምኞታቸዉ ለወደፊትም አይሳካም።  ይህ ማለት ግን ትግራይን ገንጥለዉ የትግራይ መንግስት ለመመስረት በትጋት እየሰሩ አይደለም ማለት አይደለም።ለዚህም አስረጂ ሆኖ ሊቀርብ የሚገባዉ ህወሀት ከአንድ ወር በላይ በመቐሌና በአዲስ አበባ እየተመላለሰ በዝግ በተሰበሰበበት ወቅት ትግራይ ብትገነጠል ምን ይመስላችሁዋል? በማለት ከትግራይ ህዝብ የድጋፍ ሃሳብ ለማሰባሰብ ጥረት እንዳደረጉ መታወቁ ነዉ።

ህወሃት በቀጥር አናሳ ከሆነ ብሄረሰብ የተፈጠረ ፤የአንድ ብሄረሰብ ነጻ አዉጭ ቡድን በመሆኑ ህልዉናዉን አስጠብቆ ሀገራችንን በዉስጥ ቅኝ ግዛት ለመግዛት የሚችለዉ ከትግራይ ህዝብ በስተቀር ሌላዉ ኢትዮጵያዊ በሙሉ እርስ በርሱ እየተገፋፋ፣በድንበር ስም አለያም የሀሰት ታሪክ በመፍጠር የአንዱ ማህበረሰብ አያት ቅድመ አያት፣ የሌላዉን አያት ቅድመ አያት ሲጨቁን የኖረ በማሰመሰል አሁን ያለዉ ትዉልድ እንዲተላለቅ በማድረግ ነዉ። ህወሃት መሰሪ ተንኮሉን ወደሌላዉም የሀገራችን ክፍል በማዛመት ህዝብ ከህዝብ እያጋጨ  ከፍ ሲልም የራሱን የስለላ መረብና ደህንነት በጠብ አጫሪነት እያሰማራ ፍጅት ካካሄደ በሁዋላ አስታራቂ መስሎ በመታየት አሁን ሀገራችንና ህዝባችን ያሉበት አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሰናል።

ባጠቃላይ የህዝባችን በጎሳ ስም፣ በድንበር ስም፣ ጥንት ተፈጽሞብናል በሚባል በደል ስም እርስ በርሱ እንዲገዳደል ሲደረግ፣ ትግራይ ብቻ ሰላም አግኝታ በልማት ትገሰግሳለች።

ህወሃት ይህን ሁሉ ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋና ዘር ማጥፋት የሚያከናዉነዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዉስጡ ስለሌለ ነዉ። ህወሃት ሃገሬ ነዉ የሚለዉ ትግራይን ብቻ ሲሆን፤ ህዝቤ ነዉ የሚለዉ ደግሞ የትግራይን ህዝብ ብቻ ነዉ።

የሀገር መከታ የሆንከዉ ኢትዮጵያዊ መለዮ ለባሽና ጸጥታ አስከባሪ በሙሉ ከእንግዲህ የህወሃት የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ መሳሪያ ከመሆን ታቅበህ ህዝብህንና ሀገርህን ከሀገር በቀል የቅኝ አገዛዝ ስርአት እንድትታደግ አሰቸኩዋይ ጥሪ ቀርቦልሃል።

ከጥቂት ወራት በፊት የመከላከያ ሰራዊት ወደ ኦሮምያ ዘልቆ በመግባት በጨለንቆ እልቂት በመፈጸሙና ይህም የክልሉ መስተዳድር ሳያዉቀዉ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ የኦሮምያ መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  መከላከያዉ ከህዝቡ ጎን እንዲቆም በይፋ ጥሪ ማስተላለፋቸዉ ይታወሳል።

ሃገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በተወሳሰበና ዉሉ በተተበተበ የጎሳና የዘር ግጭት ምክንያት ወደአስፈሪ ብጥብጥ ልትገባ በነበረበት ዋዜማ፤ በህዝባችን ያልተዛነፈ ትእግስትና ፤ በይበልጥም በወጣቶቻችን የህይወት መስዋእትነት ፤ ዶ/ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን  ሊመጡ ችለዋል።በመሆኑም፤ አንጻራዊ ሰላምና የተስፋ ብልጭታ እየታየ ለዘላቂ ለዉጥ መሰረት እየተጣለ መምጣቱ ጥቅማቸዉን እንደሚጎዳ፤ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ለፈጸሙት አሳፋሪና አሰቃቂ ወንጀል ለፍርድ እንደሚያቀርባቸዉ የተረዱት የትግራይ ነጻ አዉጭዎች በይፋ ጦርነት ለማወጅ ዳር ዳር ማለታቸዉን ከሰኔ 3-5, 2010 እ,ኢ.አ ያደረጉትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ፤ባወጡት የፓርቲያቸዉ መግለጫ ላይ ፍንጭ አሳይተዋል። የጊዜያዊ አወጁ ከተነሳ ወዲህ ለዉጡን ለመቀልበስ እንዲሁም፤ እንደለመዱት ያንን አስከፊ የዉስጥ ቅኝ አገዛዛቸዉን በህዝባችን ትከሻ ላይ ለመጫንና በቅርቡ ለደረሰባቸዉ የፖለቲካ ሽንፈት የበቀል ጅራፋቸዉን ለማጮህ ሸሚዛቸዉን በመጠቅለል ላይ መሆናቸዉ ገሃድ እየወጣ ነዉ። «ህወሓት ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅናት ለመታገል ወስኗል።’(ከህወሃት መግለጫ የተወሰደ) ይህ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጦርነት ለማወጅ ዳር ዳር ከማለት ሌላ ምን ሊሆን ይችላል??

ከሰሞኑ፤ በጉጂና በጌዲዮ፤ በሲዳማና በወላይታ፤ በቀቤናና በጉራጌ፤ ቀደም ሲልም፣ በሶማሌና በኦሮምያ እንዲሁም በቤኒሻንጉልና በአማራ ማህበረ-ሰብ መካከል ዳር ዳሩን የለኮሱት እሳት ህዝባችንን እየፋጀ፤ መሀል ሲደርስ፤ እነሱ ሃያ ሰባት አመት ሙሉ ለብቻቸዉ ያካበቱትን ሃብት ይዘዉ ትግራይን  ይገነጥላሉ።ይህም ሊሳካላቸዉ የሚችለዉ፤ መለዮ ለባሹን ለእኩይ አላማቸዉ መጠቀም እስከቻሉ ብቻ ነዉ። በህዝባችን መካከል በመቀጣጠል ላይ የሚገኘዉ እሳት በአስቸኩዋይ በርዶ፤ የኢትዮጵያ ብሄር- ብሄረሰቦች እንደጥንቱ አነድነታችንን ጠብቀን እንደ አንድ አገር ህዝብ መቆም ከቻልን፤ ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይን እገባበት ገብተን መደምሰስና የትግራይንም ህዝብ ከኢትዮጵያዊ ወንድሞቹና እህቶቹ,ጋር በሰላምና በትብብር አብሮ መኖሩ እንዲቀጥል ማድረግ እንችላለን። ይገባናልም። ይህ አላማ ሊሳካ የሚችለዉ ግን  መለዮ ለባሹ በህዝብህ ላይ መተኮስህን አቁመህ፤ በተለያየ ቦታ የተከሰቱ ዘር ተኮር ግጭቶችን ለማብረድ ጠብመንጃህን ዘቅዝቀህ ለህዝብህ ሰላምና ደህንነት የምትሰራ የሆነ እንደሆነ ብቻ ነዉ ።ለዚህ ታላቅ ጥሪ ምላሽ መስጠት ይጠበቅብሃል።

በመጨረሻም፤ የሀገርና የወገን አለኝታ የሆንከዉ መለዮ ለባሽ፤በሰላማዊ መንገድ መብቱን በሚጠይቀዉ ህዝብህ ላይ በመተኮስ የሀገር አደራ እንዳታጠፋ ምከርበት። ህወሃት በየትኛዉም ክልል ወደሚገኝ ኢትዮጵያዊ ወገንህ ላይ በጥፋት ሊያሰማራህ ቢፈልግ አሻፈረኝ ብለህ ካለአንተ ጠባቂ በሌለዉ ህዝብህ ዘንድ የሚያስመሰግን አኩሪ ታሪክ እንድትሰራ እጅግ የከበረ ወቅታዊ ጥሪ ቀርቦልሃል።ይህን ጥሪ ባትቀበልና የህወሃት የጥፋት ተልእኮ አስፈጻሚ በመሆን ብትቀጥል፤ የትግራይ ጄነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ተጠያቂነት በሚመጣባቸዉ ጊዜ አሳልፈዉ የሚሰጡት አንተን፤ በእነሱ ትእዛዝ ተኩሰህ የምትገድለዉን መሆኑን አትርሳ።

ከህዝብህ ጎን ብትቆም ግን የሀገርህ ባለዉለታ ሆነህ ክብር ትጎናጸፋለህ እንጂ በጭራሽ ህወሃት እንዳደረገዉ ሜዳ ላይ የሚጥልህ መንግስት በሀገርህ ላይ አይሰለጥንም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝባችንን ይባርክ።

Filed in: Amharic