>
5:13 pm - Sunday April 19, 9243

የጠ/ሚሩ የለውጥ አብዮት ከፈርንሳይ እና ስፔን አብዮቶች ሊማር ይጋባል!!!

 ቬሮኒካ መላኩ
እነ ጀነራል ክንፈ ዳኘው የፖለቲካ ስልጣናቸውን ከመነጠቃቸው የተነሳ የተጀመረውን ለውጥ ለማቆም ለመግታትና ለመቀልበስ ያለ የሌለ ሀይላቸውን እየተጠቀሙ ነው።  ለዚህ ደሞ የበጀት እጥረት የለባቸውም ። ለምሳሌ ጀነራል ክንፈ ዳኘው ብቻውን ከሜቴክ የዘረፈው 50 ቢሊዮን ብር አለው። ሌላኛው ጓደኛው አባይ ፀሃዬ ከስኳር ኮርፖሬሽን የዘረፈው 70 ቢሊዮን ብር አለው ።
አቢይ አህመድ ህልቆ መሳፍርት ከሌለው የቅልበሳ አቢዮት ታሪኮች ብዙ መማር ይችላል ።
የ1871 ያልተሳካው የፓሪስ አብዮት ፊውዳሎችን ጠራርጎ ማጎር አቅቶት ለውድቀቱ ምክንያት ሆኗል።
የግንቦት 28  1870 ስፔን አቢዮትም ያራገፋቸውን ቡርጅዊዞች በሰላም ሴራቸውን እንድጠነስሱ በማድረጉ እንደ ጉም በኖ ጠፍቷል።
ለውጥ አንድ ጊዜ ከተጀመረ ከስትራቴጅ አንፃር የአጥቂነት ቦታ በመያዝ ሳያቋርጥ በተጧጧፈ መልክ መቀጠል ይኖርበታል።
የተገኘውን ድል እንደ ሞራል ስንቅ በመጠቀም ህዝቡን በበለጠ ከጎን በማሰለፍ ጠላት ሀይሉን አሰባስቦ እንደገና እንዳያንሰራራ ጊዜ ሳይሰጡ ሽንፈቱን በመከታተል የመጨረሻ ተስፋውን አስቆርጦ በቁጥጥር ስር ማዋልና የሽንፈት ሄምሎኩን እንድጋት ማድረግ ያስፈልጋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የአሮጌውን የወያኔ አውታር  ለማፈራረስ  መዘናጋት የለበትም ። በተረፈ የወያኔ Old guards እና ተስፋቸው የጨለመባቸው ልጆቻቸው  እያሞከሩት ያለው ነገር ተራራን እንደመግፋት ከባድ ስለሆነ ሀይላቸውን እንዳያባክኑ እመክራለሁኝ።
Filed in: Amharic