>

አቢይ አህመድን ልናግዘው የሚገባን ህውሃት የጋራ የሆነ ስትራቴጅክ ጠላታችን ስለሆነች ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ፖለቲካ ሳይንስ ነው ፣ ጥበብ ነው ፣ ጌም ነው ፣ እውነታ ነው ።ፖለቲካ ግግምና ግን  አይደለም ። ፖለቲካ እኔ ያልኩት ካልሆነ አይሆንም የምትልበት ድንቁርናም አይደለም።
 በፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ የትኛውንም አይነት የሚያስፈራ ሀይል ቢኖርህ በቻህን ሆነህ አንድ ኢንች መራመድ አትችልም ።
በ30 ግዛቶቿ  99 nuclear ሪአክተር ያላትና እያንዳንዱ አረር የአለምን ግማሹን ክፍል አመድ ሊያደርግ የሚችልና  በጠቅላላው   6,800 ተተኳሽ nuclear  ቅንቡላ ያላት የአለም ሀያሏ አገር  አሜሪካ አጋር ፍለጋ እግሯ እስኪቀጥን ስትዞር የምትውለው ካለስትራቴጅክ አጋርና ቴክኒካል አጋር ብቻዋን ኪሳራ ላይ እንደምትወድቅ ስለምታውቅ ነው።
ስትራቴጅክ ጠላትህን እንዳያንሰራራ አድርገህ የምትቀብረው ከሌላው ጋር ስትራቴጅክ አጋርነት ስትፈጥር ነው።
* የአማራ ህዝብ በሰሜን በኩል ህውሃት የሚባል ስትራቴጅክ ጠላት አለው።
* የኦሮሞ ህዝብ በምስራቅ በኩል አብድ ኢሌ የሚባል ስትራቴጅክ ጠላት አለው።
* የኦሮሞ ህዝብና የአማራ ህዝብ ህውሃት የሚባል የጋራ ስትራቴጅክ ጠላት አላቸው ።
* ህውሃትና አብዲ ኢሌ የጋራ ጠላታቸውን ለመጨፍለቅ ስትራቴጅክ አጋርነት ፈጥረዋል።
የአማራ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ ብቻቸውን  የፈለገ ሀይል ፣ ነፍጥና የህዝብ ብዛት ቢኖራቸው  በተናጠል  ሳይተባበሩ በጋራ  የተሰለፈ ስትራቴጅክ ጠላታቸውን ለማሸነፍ እጅግ በጣም ከባድ ነው ወይም አይቻልም።
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን ከህውሃት ጋር በሚያደርገው የፖለቲካ ጦርነት ልናግዘው ይገባል ስንል ለአቢይ አህመድ ብለን ሳይሆን  ህውሃት የጋራ የሆነ ስትራቴጅክ ጠላታችን ስለሆነች ነው ።
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በፊትም ሆነ በኋላ  አሜሪካና ሩሲያ ፣ ታላቋ ብሪታኒያና ሩሲያ  በአይነ ቁራኛ የሚተያዩ ጠላቶች ነበሩ ። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ግን  ለሁሉም የማይራራና እጅግ ጨካኝ የሆነ አዶልፍ ሂትለር የሚባል ዞምቢ ድምጥማጣቸውን ሊያጠፋ መጣባቸው። እነዚህ በአይድዮሎጅም ሆነ በምንም የማይጣጣሙ አገሮች  የጋራ የሆነ ስትራቴጅክ ጠላታቸውን አፈር ድሜ ለማስበላት ሳይወዱ በግድ የጋራ የአጋርነት ግምባር ፈጠሩ።
ጆሴፍ ስታሊን ምስራቅ ጀርመንን ከሂትለር መንጋጋ ያላቀቀው  የአሜሪካው ፍራንክሊን ሩዝቬልት በሰጠው ታንክና የሩሲያ  ወታደር የሚበላው መኖ ነው ። ሩዝቬልትና ስታሊን ግን በሰላሙ ጊዜ እርስ በርሳቸው ሊጠፋፉ የሚፈላለጉ መሪዎች ነበሩ ። ዌንስተን ቸርችልና ጆሴፍ ስታሊንም እንደዛው ነበሩ ይሄ ሁሉ ልዩነት ግን በጋራ ተሰልፎ ጠላታቸውን ለመቅበር አልከለከላቸውም።
Filed in: Amharic