>

245 ጥያቄዎች ለጠ/ሚ አብይ  (ደረጄ ደስታ)

1ኛ – ኤርትራ ዝም ካለች ባድመን አትፈልገውም ወይም እምትፈልገው ሌላ ነገር ነው ማለት ነው። ወይም ከሰዎችዋ ጋር -ስንተዋወቅ አንተናነቅ- ብላም ይሆናል። ስለሷ ምን ያስባሉ?
2ኛ- የመጀመሪያውን የትግራይ ህዝብን ጥያቄ መልሰን ወደ ሁለተኛው ጥያቄ (ካለ?) እንድንሸጋገር የትግራይ ህዝብ በባድመ ጉዳይ የበለጠ ቅርበትና ታሪካዊ ግንኙነት ስላለው የህዝቡን ጥያቄ ተቀብለን ለጊዜው አቆይተነዋል ቢባል ምን ይመስልዎታል? ያን ጊዜ ውስጥ ውስጡን በድርጅትዎ ጥያቄውን በሚስጥር የሚያጣድፉት- በውጭ ደግሞ ተቃውሞውን እሚያፋፍሙት የህወሃት ሰዎች ሴራ ግልጽ ሊሆን ይችላል። እርስዎ የተጠለፉባት ችግር ትሆን?
3ኛ- አብይ ሆይ እርስዎ -ጉዳዩን ለኛ ይተውሉን- ከሚሉ ወገኖች ጋር ምን አዳረቅዎ? ከኤርትራ ጋር እርቅ ከፈለጉ ድንበር ምናምን ውስጥ ሳይገቡ በእርቁ መሠረተ ሀሳብ ላይ ይነጋገሩና ስምምነቱ ከተገኘ በኋላ ወደ አፈጻጸሙ ጉዳይ ይገባሉ። ሁለቱም አንፈልግም ካሉ ደግሞ ጉዳዩ የአገር ጉዳይ ስለሆነ ወደኛ ዞር ብለው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ምን ይመስልሃል ብለው ይጠይቁን አያያዙን አይተን እንፈርዳለን። አሁን ግን ስንት እምንተኩሰው ጉዳይ እያለ ሀሳብ ሳይሆን ጥይት ብቻ መተኮስ ከሚወዱትና ጦርነትን ከናፈቁት ጋር ለምን ያጋፍጡናል። ለአገርም ለርስዎም ጥሩ አይደለም።
124ኛ-  የአገር ጥያቄዎችና ችግሮችን ለመመለስ ብቻዎን አይጋፈጡ። እስኪ እዚህ ላይ ህዝቡ ምን ይላል ብለው ለመምከር ትንፋሽ ይውሰዱ። ኢትዮጵያ ችግርና ጥያቄ ከማምረቷ ብዛት ለራሷም ተርፏት ኤክስፖርት ልታደርግ ገበያ እምታፈላልግ መስላለች። ስለዚህ ነገ እንኳን መልስ ሊሰጡ ጥያቄዎቹን ራሱ ስምቶ ለመጨረስ ዘመን አይበቃዎትም። እስኪ ተቃዋሚችዎንም ሀሳብ እንዲሰጡ ይጋብዟቸው። እኛም የነገ መሪዎቻችን ብስለት እንለካበታለን። ሥልጣን ከወጡ በኋላ ከምናያቸው ክወዲሁ ብንሰማቸው ማለፊያ ነው። እርስዎስ ቢሆኑ ብቻዎን ምን በወጣዎት!
245ኛ  ለመሆኑ እርስዎ እንደምን አሉ?
Filed in: Amharic