>

ቁስለኞቹ በጠ/ሚሩ ላይ ከያቅጣጫው ዘመቻ ከፍተዋል!!!

ቁስለኞቹ በጠ/ሚሩ ላይ ከያቅጣጫው ዘመቻ ከፍተዋል!!!
ከሦስት ቀን በፊት አብዲ መሀመድ ኢሌ – ጠቅላይ ሚኒስትሩን ዘለፉ።
ከትናንት በስቲያ ጀነራል ክንፈ ዳኘው ፦”ለውጡ ህገ መንግስቱን የጣሰ ነው”አሉ።
እነ ጌታቸው አሰፋ ነባር መዋቅራቸውን ተጠቅመው ሀገሩን ማተራመስ ቀጥለዋል።
ህወኃት እነ አረናን ፣ ብሎገር ነኝ ባዩን፣  ተቃዋሚ ነኝ ባዩን ባለሀብቶቿን …በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ሰብስባ  ስትዶልት ከርማለች።
ዛሬ ደግሞ አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን በኢትዮ ዲያስፖራ ራዲዮ ቀርበው ፦”ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሚያሳፍር ሁኔታ ከጠላት ጋር አብሮ እየወጋን ነው” ሲሉ ከሰዋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው እስከዛሬ በዘለቀው አሠራራቸው የኢህአዴግ ተሿሚ ለመሆን መስፈርቱ  በህዝብ መጠላት እንደነበር ስናጤን፣ “ጠላት” ብለው የጠሩት የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ዶክተር አብይን ከከሠሱበት ምክንያት አንዱና ዋነኛው “ሕዝበኝነት” የሚል ነው።ይሑንና በጥቁር መስተዋት ተሸፍኖ ከሰው ጋር ሳይቀላቀል እስከወዲያኛው ባሸለበው የቡድን መሪያቸው ምትክ -ራሱ ታክሲ እየነዳ እንግዳ የሚቀበል የሀገር መሪ ሢመጣ፣ “ሕዝበኝነት” ብለው መክሠሳቸው፣ ቅናታቸውን እንጂ ሕዝባዊነታቸውን አያሳይም። ስለዚህ ዛሬም ጠባቸው ከማንም ጋር ሳይሆን ከሕዝቡ ጋር ነው። ጠባቸው ከአንተ ለውጥ ከናፈቅከው ምሥኪን ወገኔ ጋር ነው።ስለዚህ ጅምር ለውጥህ እንዳይቀለበስ፣ በትጋት ጠንክረህ ጠብቅ!!!
ሶሚ
Filed in: Amharic