>

መቶ ሚሊዮኖች በአገራቸው ጉዳይ እኩል እንዲሆኑ የውሀ-ልኩን ያስተካከለ መሀንዲስ!!! (ደግፌ አስረስ)

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ነው። መልሶችን በውሸት የሚያጅል፣ ከሰውነቱ ይልቅ ብሄሩን የሚያልቅ፣ የፀጥታ ሀይሉ እርምጃ እንዲወስድ አምባገነናዊ ትእዛዝ የሚሰጥ፣ አለመያዝ እንጂ ስርቆት ስራ ነው የሚል፣ በሸፍጥና ሽንሸና  ፖለቲካ የተካነ፣ ከአንድ ዘር ሰራዊት ያዋቀረ፣ ያለጥፋት ዜጎችን ማሰር እንጂ መፍታት የማያውቅ፣ ሞቶ እንኳ በጠባቂ ከሙታን ያልገጠመ…
ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ነው። የሙት መንፈስ ታቅፎ ሲዞር ስድስት አመት የደነዘዘ፣ ገዳዮችን ሲያወድስ አልሞ ተኳሾችን ሲያቆለጳጵስ የከረመ፣ ከበታቾቹ ትዛዝ ለመቀበል ወደኋላ ያላለ፣ ለህዝብ ሳይሆን ለሃያ አራት የወያኔ ሌቦች ጥቅም የቆም፣ የህዝብን ሀይል መረዳት የተሳነው…
መንግስትን አሸባሪ ነው ያለልኝን አብይ እንደላይኞቹ ጠቅላይ ሚንስትር ነው አትበሉት ውሸትን ባነገሱ የቀን ጅቦች መሀል ሀቅን መስካሪ እንጅ፣ ሌቦችን በስማቸው የጠራ አልሞ ተኳሽ እንጂ፣ መከላከያ ዘር የለውም ብሎ በዘር የተኮለኮሉ ጄነራሎችን ምሽግ ደርማሽ እንጂ። የመቀነስ ልሂቃን ለ44 አመታት ሲደክሙበት የነበረውን በካይ ሂሳብ በመደመር ስሌት በሶስት ወሩ ያንኮታኮተ የሂሳብ ሊቅ እንጂ! አብይ ዘረኞች ፊቱ ቆመው ሊሞግቱት የማይችሉ ኢትዮጵያዊ አለት እንጅ እንደሀይለማርያም ጠቅላይ ሚንስትር አደለም! አገርን ሊያጠፋ የተነሳ ተስቦን ያከመ ሀኪም እንጂ ከወርቅ ዘር መገኘቱን የሚለፍፍ በቭታ አይደለም!
መቶ ሚሊዮኖች በአገራቸው ጉዳይ እኩል እንዲሆኑ የውሀልኩን ያስተካከል መሀንዲስ፣ ባገሬ ጉዳይ እኔ ከእገሌ አልበልጥምን የሰበከ ሀዋርያ ለኔ ጠቅላይ ሚንስትር አይደለም! አብይ አብይ ነው! አብይ!
Filed in: Amharic