>
5:13 pm - Wednesday April 19, 0124

"...የቆረጡት እግሬ ውስጥ ብረት በመክተት ሌላ ጊዜ ደግሞ በፒንሳ አጥንቴን በመሳብ ያሰቃዩኝ ነበር!!" (ከፍ ያለው ተፈራ)

“…የቆረጡት እግሬ ውስጥ ብረት በመክተት ሌላ ጊዜ ደግሞ በፒንሳ አጥንቴን በመሳብ ያሰቃዩኝ ነበር!!”

ከፍ ያለው ተፈራ
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ይህን ግፍ ስማ አንብብ በማእከላዊ የትግራይ ነፃ አውጪዎቹ ደህነቶች በሰው ልጅ ላይ ይህን አሰቃቂ ግፍ ይመፅማሉ::
ኦሮምኛ ቋንቋ ለማትሰሙ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ የቀረበ:: ይህ ግፍ ቂም አያሲዝም ወይ?
ይህ ጥያቄ እና መልስ ልቤን ነካው ጠያቂው አማተር ጋዜጠኛ ይመሥላኛል ተጠያቂው ግን በአንድ አጋጣሚ የሕይውት አቅጣጫው ተቀይሮ ላለፉት 12 ዓመታት በእስር ቤት ከነበረበት በቅርቡ በምህረት የተለቀቀ ከፊያለው የተባለ ወጣት ነው፡፡
ጠያቂ፦ እሺ ከፊያለው እንኳን ፈጣሪ ከቤተስቦችህ፡ዘመዶችህ እና ወዳጆችህ ጋር በሰላም አገናኘክ እያልኩ አሁን የምጠይቅክ እስቲ እስር ቤት ከመግባትህ በፊት ምን ነበርክ? እስር ቤት ለምን ገባክ እንዴት ተያዝክ? የእስር ቤት ቆይታክን በአጭሩ ምን ይመስል እንደነበር ግልጽልኝ?
ከፊያለው፦ በመጀመሪያ ስለሰጠከኝ እድል አመስግናለሁ እስር ቤት ከመግባቴ በፊት የ3ኛ ዓምት ዩንቨርሲቲ ትምርቴን ጨርሼ ከጒደኞቼ ጋር ለዕረፍት ወደ ቤተስቦቻችን ጉዞ ላይ እያለን መንገድ ላይ ጠብቀውን ከባድ ቶክስ ከፈቱቡን የሶስት ጒደኞቼ ህይወት እዛው ጋ አለፈች የኔም አንድ እግሬ እዛው ተቆረጠ ከጥቂት ቀናትም በኋዋላ ሌላኛውን እግሬን ከጉልበቴ በታች ቆረጡት በድጋሜ ከተወስኑ ቀናቶች በኋዋላ ጉልበቴ ድረስ ቆረጡኝ በመጨረሻም ለሦስተኛ ጊዜ ጭኔ አከባቢ ከፍ አርገው ቆረጡኝ ቁስሌም ሳይድን መአከላዊ በሚባልው መመርመሪያ ማዕከል  ወስደው በጣም ቶርች ሲያደርጉኝ ነበር በመአከላዊ ለስው ልጅ ለመንገር እንኳን የሚከብዱ ነገሮችን ነው ያሳለፍኩት አንዴ ቁስሌ ውስጥ ቀጭን ብረት በመክተት ሌላ ጊዜ ደግሞ በፒንሳ አጥንቴን እና ቁስሌን በመሳብ ያሰቃዩኝ ነበር እንደዚሁም ለ24 ሳዓታት በሦስት ፈረቃ እጆቼን ሰቅለው ሲገርፉኝ ጆሮዎቼ ከዱላ ብዛት ይመግሉ ነበር ስውነቴ በሙሉ ቆስሎ ሥለነበር መፀዳጃ  ቤት እራሴን ችዬ መኔድ ስለማልችል ሁለት እጆቼን አንጠልጥለው አንዳንዴም መሬት ላይ እየጎተቱ ሲወስዱኝ ከሌሎች እሥረኞች እና ከተወሰኑ ፀጥታ ሠራተኞች ደብቅው እና ምሽትን ጠብቀው ነበር  ሁሉም ስው በዚ ውስጥ የሚያልፍበት ሲሆን የኔን ለየት የሚያደርገው ሁለት እግሮች የሌለኝ እና ቁስሌም ያልደረቀ ስላልነበር ነው ሰውነቴ ሙሉ በሙሉ በድብደባ ብዛት ቆስሎ መተኛት መቀመጥ እስኪያቅተኝ ሲያንገላቱኝ  በንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ለ9ወራት ካሰቃዩኝ በኋዋላ ወደ ቃሊቲ ወሥደው ጨለማ ቤት ጣሉኝ እዛ ጨለማ ቤት ውስጥ ሌሎች 6ልጆች እጅ እና እግራቸው ታስሮ ስለነበረ ሊረዱኝ ስለማይችሉ እና የኔም እጆች በድብደባ ብዛት ደርቀው ስለነበር መፀዳጃ ቤት መሄድ ስለማልችል እዛው በፌስታል ነበር የምፀዳዳው እንግዲህ እንደዚህ ነው ያሳለፍነው፡፡
ጠያቂ፦ በእስር ቤቱ ውስጥ የስባዊ መብት ጥስቱ ምን እንደሚመስል እስቲ ግለፅልኝ ያው አንተ እግሮችክን አተካል እንዲሁም የስነ ልቦናም ጉዳት አድርሶብካል እስቲ ባጠቃላይ የነበረውን ሁኔታ ለወገን ግለፅልኝ?
ከፊያለው፦ይህንን ለመግለፅ በጣም ከባድ እና አስቸጋሪ ነው ማንም ሰው ካላየው ለማመን ይቸገራል ሰዎቹ እንደ ሰው አየደለም የሚያስቡት ትንሽ ንቃት ያላቸውን የኦሮሞ ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይዞ በማምጣት የወንድ መራቢያ አካላቸው ላይ ብረት እና ጠርሙስ በማንጠልጠል ማህን ያደርጒቸዋል ሴቶቹንም ጠርሙስ አግለው ብልታቸው ውስጥ በመክተት ቶርች ያደርጋሉ ሁሉም ከዚህ እስር ቤት የሚወጣ ሲታይ ጤነኛ ይመስላል እንጂ አብዛኛው የተኮላሸ ስለሆነ መውለድ አይችልም፡፡
(ናትናኤል መኮንን)

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=606938623024319&id=100011245608059

Filed in: Amharic