>
5:13 pm - Friday April 19, 5568

ቢቢሲ የባድሜውን ጦርነት "የሰው ማእበል" ቢለውም እውነታው "የአማራና ኦሮሞ ማእበል" ነበር!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

” Operation sun set” ወይም ዘመቻ ፀሃይ ግባት እያሉ በሚጠሩት አሰቃቂ ውጊያ ከየትኛውም ክፍለጦር በፊት የባድመን ምሽግ ሰብሮ ባዲመ ከተማ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለበው በጄነራል አሳምነው ፅጌ የሚመራው ክፍለጦር ነበር።
ያችን ባንዲራም ለሚሰቅለው ወታደር ፈልጎ የሰጠው በመለስ ዜናዊ ማእረጉ ተገፎ እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የነበረው ጀነራል አሳምነው ፅጌ ነው።
 በወቅቱ ወጣት የነበረው ወታደር የዛሬው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአለቃው ጀነራል  አሳምነው ፅጌ  ክፍለጦር ስር ስለነበር
 ለቀድሞ አለቃው ጀነራል አሳምነው ፅጌ  በመለስ ዜናዊ የተገፈፈውን ማእረጉን ሲመልስለት ጀነራሉ ለአገሩ ያደረገውን ተጋድሎ በስማ በለው ሳይሆን በአይኑ በብረቱ ስለተመለከተ ነው።
ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በጥልቅ ስሜት “በባድመ ጉዳይ ላይ ወሬ ሲነዙ የሚውሉትን የተከዜ ማዶ ሰዎች የሞራል ውድቀት የገለፀበት ቃላት አሰደናቂም አሳዛኝም ነበር።
አቢይ አህመድ የወንድሙን ልጅ ማሙሽን
“የጀግና ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ ፣
ልጅሽን አሞራ እንጅ አይቀብረውም ዘመድ።” 
በሚለው ታሪካዊ  ኢትዮጵያዊ ብሂል  ይፈፀም ዘንድ ለባድመ አሞራ  ሰጥቷል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እናቶች ለዛች ኩርማን መሬት ለባድመ አሞራ አስረክበዋል።
አቢይ አህመድ ያን ጦርነት ” Irresponsible  በሆኑ መሪዎች ” የተከፈተ ቀፋፊ ጦርነት እንደነበር ገልፆታል።
BBC ያን ጦርነት ከሁለተኛው አለም ጦርነት ጋር በማመሳሰል እጅግ ኋላ ቀር በሆነ “Human wave ” በሚባለው ስልት የሰው ልጅ ፈንጅ ማምከኛ በመሆን ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ ለአለም ተናግሯል።
BBC  ያን ጦርነት “Human Wave ” ቢለውም ሀቁ የነበረው ግን “Amhara and Oromo Wave ” ነበር።  የሰው ሞገድ ሆነው ፈንጅ ማምከኛ የሆኑት አማራና ኦሮሞ ነበሩ ። አቢይ አህመድም ፈጣሪ ትረፍ ሲለው ነው የተረፈው እንጅ ከፈንጅ ማምከኛው ዌቭ አንዱ ነበር።
አሁን ሰላም ሲባሉ ጦርነትን እንደ ቲያትር ይደገምልን  የሚሉ የቀን ጅቦች እየተመለከትን ነው ። ከዚህ በኋላ ከፈለጋችሁ Human wave የሚሆንልህን ሰው እዛው ከተከዜ ማዶ ፈልገህ ማግድ ።  በዛን የሞኝነት ወቅት የሰው ደም መብላት የለመደው የአገራችሁ አሞራ በልቷቸው የቀሩትም ወንድሞቻችን ቁጭት እስከአጥንታችን ዘልቆ ያንገበግበናል።
Filed in: Amharic