>

በ'አብን' እና በአማራ የሎሚ እርሻ ውስጥ የተዘሩ እሾካማ የወያኔ እምቧዮች! (ሀይሉ አባይ)

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በማያሻማ መልኩ የሊብራል ርዕዮትን እንደሚከተል አስታውቋል:: ይህም ማለት ከ10 በላይ ከሆኑት የብሔረተኝነት ክፍሎች (Types of Nationalism) መካከል ሊብራል አይዲዮሎጂ የተጋባው ከሲቪል ብሔረተኝነት ነው:: ሲቪል ብሔረተኝነት በሁሉም መልኩ የጎሣ ብሔረተኝነት ተፃራሪ ነው:: ዴሞክራሲያዊም ነው::
‘አብን’ የተመሰረተውና ድጋፍ የቸርነው መሪ ተግባሩ የአማራን ጥቃትና ህልውና ለማስጠበቅ በመቆሙና አማራን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ባለመሰነቁና የክተት ጥሪም ባለማድረጉ ነው:: በየስፍራው በሃገሩ ኢትዮጵያ እየኖረ ያለውን ከ9 ሚሊዮን በላይ የሆነውን አማራ እንደ ፍልስጤሞች በምዕራብ ዳርቻ (West Bank) እና በጋዛ (Gaza) በማይገናኙ ግዛቶች ሰንጥቀንና በውሃ በግንብ ከፍለን መንግስት ልንመሰርትለት አይደለም:: የአብን መመስረት ሳይደራጅ በነጠላ እናጠፋዋለን ብለው የዘመቱበት ህወሃትን ጠላቶቹ አብን ከጅምሩ ወይም እነርሱ እንደሚሉት “እባብን ማጥቃት በእንጭጭነቱ” በሚል እሣቤያቸው የ’አብን’ አርማ በመለጠፍና በአማራ ስም የሚምሉ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን አሰማርተው በማህበራዊ ድህረ ገጾች ወይም ፌስቡክ ላይ በትናለች:: የእነዚህ ቅጥር የሳይበር ሠራዊትና ወያኔያዊ አብዮት ጠባቂዎች በቀላሉ ይለያሉ:: ከአማራ በላይ አማራ ሆነውና መስለው የአዞ እምባቸውን ይረጫሉ:: ፅንፈኛ፣ ሞራላዊና አማራዊ ያልሆነ ስነምግባር ያሣያሉ።
እነዚህ የተሸጡና ሆዳሞች የሚከተሉትን ይመስላሉ::
1. መርዘኛ መሪዎቹ በብዛት በብአዴን በተለያዩ የድርጅት ስሞች እዚህ ሰሜን አሜሪካ የተደራጁ ሃይሎች ናቸው:: የሚምሉት በጀግናው ፕ/ር አስራት ፎቶና ስም ነው:: ኢትዮጵያም ውስጥ ያልገባቸውን በአማራ ስም ይነዳሉ::
2. በአማራ ብሶትና እንግልት እየታከኩ “የበደለችህ ኢትዮጵያ ናት:: ኢትዮጵያ ገደል ትግባ” “ኢትዮጵያ ትፍረስ” ሲሉ እያደመጥንም ነው። ኢትዮጵያን ለማፍረስ መሻት ወያኔያዊ ነው::
3. ከአማራ ውጪ ያሉ አማራ ያልሆኑ ጎሣዎችን በጠላትነት በጥቅሉ በመፈረጅ “አማራን የሚወድ ማንም የለም” ሲሉ በጅምላ ፍረጃቸውብ(Hasty Generations) ከቁጥር በላይ የሆነውንና ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖረው አማራ ላይ ወያኔ እሣት ሲለኩስ እነርሱ ቤንዚን ይረጫሉ::
4. ‘አብን’ ተቀብለናል እያሉ ድርጅቱን ለማስጠላት በአብን ስም አቋም ይወስዳሉ:: በአብን ስም ይፅፋሉ:: ይገዝታሉ:: ፍጥጫን ይሰብካሉ:: በ’አብን’ ስር ሳይሆን ‘አብን’ ሊመሩ ይከክላሉ።
5. ትልቁን አማራ በጎሣ ውሐ ልክ ይለካሉ:: በእነርሱ ደረጃ ሊያወርዱት ይጥራሉ:: በወያኔ ቅጥረኛ ቋንቋቸው “እኛ የምንፈልገው አብን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም:: ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንተባበር” ይሉናል:: አማራ ከወራሪ ወያኔና ከምስለኔዎቹ ጋር ሆኖ እራሱን አያፈርስም:: እራሱን ቡራሱ (suicide) አያጠፋም::
6. የዘርና የሃይማኖት ስድብን ይበትናሉ:: ሌላው አማራውን በጎሪጥና በጥላቻ እንዲስል ይሰራሉ:: ጭራሹንም ለየት ያለ ሃሣብን የሚያራምድ አማራን “ዲቃላ አማራ” “ሰባት ቤታቸው ይጣራ” እያሉ ከአማራ በላይ አማራ መስለው አማራ ውስጥ አደገኛ መርዝ ይተፋሉ:: ይህ አደጋ ነው::
7. ጭራሹኑ የአብን ሊቀምንበር ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔን “ለምን የጠ/ሚ አብይን ጅማሬ አወደሰ” ብለው በራሱ ፖስት ላይ ያቅራራሉ:: ያቀረሻሉ:: ጭራሹን መመሪያ ሊሰጡት ይግተረተራሉ:: ይገርማል!
8. “አማራው ወዳጅ የለውም” እያሉን ሁሉን ያለ ፍንጭና ምክንያት በጥርጣሬና በአይነ ቁራኛ እንዲያይ ይመክራሉ:: “ሁሉም ጠላቴ ነው” አማራው እንዲልም በመግፋት የእነርሱን የጥርጣሬ በሽታ (delusional paranoia) በአማራው ሊዘሩ ይዳዳሉ::
በአብን አርማ ስር (false flag) የሚንቦጫረቅ ሁሉ የአብንም ሆነ የአማራ ተወካይ አይደለም:: የአብን አቋም የሚገለፀው በአብን መድረክ ብቻ ነው:: ሁሉም አዋቂና ሁሉም መሪ ነኝ ብሎ ካሰበ ነገር ሁሉ ሳይወለድ ይሞታል:: በአማራና በሃገሩ ኢትዮጵያ መካከል የልዩነት መስመርን የሚስል ሁሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን ፀረ-አማራም ነው:: ይህ ጥንቃቄን ይፈልጋል:: አማራው መደራጀት ያስፈለገው የወገኑን አማራ ጥቃትና መገለል ለመመከት እንጂ ረቂቅ የሆነችውንና የሠራትን ሃገሩን ኢትዮጵያ ለመካድ አይደለም:: ኢትዮጵያ ሃገሩን በካዱ ሃይሎች ጋርም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጎናቸው አይቆምም:: ለአማራው ስቃይ ምክንያትም እነርሱ ናቸው:: አማራ ሲደራጅ ወቅታዊውን ሁኔታ በማጤንና መጀመራያ የመቀመጫዬን እሾክ ልንቀል ብሎ እንጂ ማንነቱና ምንነቱ ጠፍቶትም አይደለም:: አማራ ኢትዮጵያ ሃገሩን ከሌሎች ወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጋር የሰራው ወራሪንና ከሃዲዎችን ተፋልሞ እንጂ ከባንዳዎችና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብሮ አይደለም::
እነዚህ እሾክና አሜከላዎች በአማራ ውስጥ በወያኔ የተዘሩ እምቧዮች እንጂ የአማራ ሎሚ አይደሉምና እንደ አረም እንመንጥራቸው::
ማንኛውም ፅንፈኝነት ልክ አለመሆን ብቻ ሣይሆን አደጋም ነው:: እኛም ሆንን አብን እንጠንቀቅ (Let’s keep our eye on those fifth column subservient renegades)!
በአብን ስም ለአብንና አማራ ሞት በስምሪት የሚሰሩትን ሹምባሾች ላይ አይናችንን እናሣርፍ:: መርዛቸውን ለነርሱ መልሰን እንጋታቸው::
ነገ ብሩህ ቀን ነው!
Filed in: Amharic