ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ” አሸባሪ ! ” ወንበዴ ! ” እየተባለ በተሰደበበት ፓርላማ “አንቱ ” እየተባለ ሲሞካሽ ዋለ!!!
ቬሮኒካ መላኩ

…
2~ህውሃት እንደ ኮሶ የሚመር ሽንፈቷን ግጥም አድርግባ ሰርግባ የፌደራል ዋና ከተማውን ትታ መቀሌ ከገባች ከርማለች ። አንዳንዶቹ ” ቴክኒካል ሪትሪት” አድርጋ እንደገና በድል ለመመለስ ነው ቢሉም እኔ ደሞ ህውሃትን እንደ ድሮው የበላይ ከምትሆን የፓርላማው ተጠሪን አስመላሽ ወልደስላሴን አይን ማብራት ይቀላል እላለሁኝ።
…
3~ የኢትዮ ሱማሌ ህዝብ ወደ 7 ሚሊዮን ይጠጋል ። የ ሄ ህዝብ ያለው የፓርላማ ወንበር ግን 21 ነው። የትግራይ ህዝብ 5 ሚሊዮን ነው ያለው የፓርላማ ወንበር ግን ካልተሳሳትኩኝ 38 ነው ። በኢህአድግ ምክር ቤትና በስራ አስፈፃሚ ያለው ውክልና ትላልቅ ህዝብ ካላቸው ኦሮሞ ፣አማራና ደቡብ ጋር እኩል ስለሆነ ይሄ በአስቸኳይ መታረም አለበት ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ይሄን የህገመንግስትና የህግ ጥሰት በአስቸኳይ ማስተካከል ይገባቸዋል።
…
4~ መለስ ዜናዊ ከመሞቱ በፊት ይመስለኛል የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ አንድ የህክምና ዶክተር ( የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት) ይመስለኛል አቅርቦ ማብራሪያ ከመጠየቁ በፊት ” እስኪ ስምዎን ለህዝቡ ያስተዋውቁልን? ” ብሎ ይጠይቃቸዋል።
ሃኪሙም ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ።” በማለት ሙሉ ስሙን ይናገራል።
ጋዜጠኛው አውቶማቲካሊ ድውክ ብሎ ቁጭ አለ። ሱፍ የለበሰ ድርጭት አከለ ። ከዛ በኋላ እንባ እንባ እያለው ድምፁ እየተንቀጠቀጠ ጥያቄውን ጨረሰ ።
…
ዛሬ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ” አሸባሪ ! ” ወንበዴ ! ” እየተባለ በተሰደበበት ፓርላማ “አንቱ ” እየተባለ ሲሞካሽ ዋለ ። ጊዜ ሲቀያየር እንደዚሁ ነው። ለነገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎሬላ ውጊያ ፋሽኑ አልፎበታል ወደ አገር ቤት ግቡ ከማለቱ ከወር በፊት እኔ ራሴ ግንቦት 7ቶችን በተመሳሳይ ቋንቋ ” ፋሽኑ አልፎበታል ግቡ ” ብዬ ነበር። ከጠቅላዩ ጋር በዚህ ጉዳይ በቃላት አገላለፅ መመሳሰላችን ገርሞኛል። 🙂
…
አሁን ፖለቲካው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈልገው መልኩ እየተቀየረ ነው ።ገና ግን ብዙ ይቀራል ።ያገኘነውንም ድል ከቀልባሾች መጠበቅ ይገባል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይንም እንደ ጥሩ ችግኝ ልንከባከበው ይገባል የሚል የግሌ እምነት አለኝ ።
በመጨረሻ ለቅዳሜው መሬት አንቀጥቅጥ የድጋፍ ሰልፍ መዘጋጄታችንን እንዳይረሳ እላለሁኝ።