በፈርኦን ቤት ላደገው የዘመናችን ሙሴ ቴዲ አፍሮ ሊያቀነቅንለት ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ

…
ቴዲ አፍሮ ለእምዬ ምኒልክ ” ጥቁር ሰው ” በማለት አስደምሞናል ። ለአፄ ሀይለስላሴ ” የአፍሪካ አባት ” በማለት አስደንቆናል ። ለአፄ ቴዎድሮስ ” ጎንደር ” በሚል ዜማው መላ ሰውነታችንን እንድነዝረን አድርጎናል።
ቴዲ እንደ ሌሎች አርቲስቶች መሪ በተቀየረ ቁጥር ጃኬቱን እየቀየረ የሚያወድስ ተራ አርቲስት አይደለም። ቴዲ አፍሮ በጣም ብቻውን ተራራ ነው።
…
ባለፉት 20 አመታት ቴዲ አፍሮ ” ፍቅር ያሸንፋል ” የሚለውን እንደ ተራራ የገዘፈ ሀይለ ቃል ብቻውን ተሸክሞት ኖሯል ። ስለ ይቅርታ ሰብኳል። ” ፍቅር ያሸንፋል ” የሚለው ሀይለ ቃል ቴዲ ፓተንት ባይወስድበትም በስፋት ለኢትዮጵያውያን ሲያሰርፅ ኖሯል ። ቴዲ አፍሮ ብቻውን ተሸክሞት የኖረውን ” ፍቅር ያሸንፋል” የሚለውን ቃል ፖለቲከኛውና የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚ/ር አቢይ አህመድ ተቀብሎ ለኢትዮጵያውያን እየሰበከ ነው። የቴዲና የአቢይ አህመድ መናበብ የሚገርም ነው ። ቴዲ በዘፈኑ የነገረንን ዶ/ር አቢይ አህመድ በንግግሩ ያስተላልፋል።ቴዲ አፍሮ ለአቢይ አህመድ ዘፈን ማውጣቱ ተገቢና ወቅታዊም ስለሆነ ሊመሰገን ይገባዋል።