>

ከሰብአዊነት ውጭ የሆነ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ስቃይ የደረሰባቸው የህግ ታራሚዎች በቃሊቲ?!? (በሀብታሙ ደባሱ - ኢ.ቴ.ቪ

ከሰብአዊነት ውጭ የሆነ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ስቃይ የደረሰባቸው የህግ ታራሚዎች በቃሊቲ?!?
በሀብታሙ ደባሱ ኢ.ቴ.ቪ
በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረማያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች በቆይታቸውና በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ፡
“…አያያዛችን ክብራችንን ባዋረደ መልኩ በመሆኑ መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጠን እንጠይቃለን” ከሚሉ የህግ ታራሚዎች የተወሰኑት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ለምሳሌ እኔ ይላል አንዱ የህግ ታራሚ “…  በማላውቀው ጉዳይ ከቤቴ ታፍኜ ከመምጣቴም በላይ ብልቴ ላይ ውሀ አንጠልጥለው ባደረብሱኝ አሰቃቂ ድብደባ ለከፋ ጉዳት ተዳርጌያለሁ…” ያለ ሲሆን ሌላኛው የህግ ታራሚ በፊንጢጣቸው ውስጥ እንጨት እየከተቱ እንደሚያሰቃይዋቸው ተናግሯል።
አንዲት ሴት የህግ ታራሚ ጥፍር ከመንቀል አንስቶ በርካታ ማሰቃያዎችን እንደሚፈጽሙባቸው ፤ የጉልበት ስራም እያሰሯቸው ለበሽታ እንደዳረጓቸው ገልጻለች።
የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት በበኩሉ
 “… የሀይል እርምጃ በህግ ታራሚዎች ላይ አይወሰድም ” ብሏል፡፡
 በማረሚያ ቤቱ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት አላስጠበቀም በሚል በእስራት የተቀጣው የማረሚያ ቤት ሀላፊ በዋስ እንደተለቀቀም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቀውን ታራሚ ጉዳይ ለመመልከት ተለዋጭ  ቀጠሮ ይዟል፡፡
በተያያዘ:-
“አሁን በቃሊቲ እና ቂሊንጦ ወህኒ ቤቶች ያሉ ታራሚዎች በሚዲያዎች ኢንተርቪው ከተደረገላቸው በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ እየደበደቧቸውና እያሰቃይዋቸው ነው።
‘ከስራ ገበታችን ልታስነሱን ነው? ማን
እንደሚያስጥላቹ እናያለን’ እያሉ እያሰቃይዋቸው ነውና እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ድረሱላቸው::”
Filed in: Amharic