“ይሄ ክስተት እጅግ በጣም ታሪካዊ ነው!!!”
ቬሮኒካ መላኩ
የታመመ ሰሞን እንኳን ዶክተሮቹ በህይወት ብዙ ቀናት የመቆየት እድል እንደሌለው ሲነግሩት በህይወት ለመቆየት የነበረውን አጭር ጊዜ በመጥቀስ በሳኡዲ በኩል ለኢሳያስ የእንገናኝ መልእክት በከፍተኛ ሚስጥር ቢልክም አልተሳካለትም።
…
ሀይለማሪያም ደሳለኝም ገና ወደ ስልጣን ከመምጣቱ ለአልጄዚራዋ ጋዜጠኛ ጃኔ ዱተን… “If you ask me ‘Do you want to go to Asmara [the Eritrean capital] and sit down and negotiate with Isaias Afewerki right now ?’, then I will say ‘yes ” ” አሁን ኢሳያስ እንነጋገር ብሎ ቢጠይቀኝ አሁኑኑ በርሬ አስመራ እሄዳለሁ ብሎ ቢለምንም ሳይሳካለት ከስልጣኑ ወርዷል።
…

…
አሁን መለስ ዜናዊ አልጄርስ ላይ በፈረመው መሰረት ። ሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት በወሰነው መሰረት አሁን ባድሜ መሄዷ ተረጋግጧል ። ባድሜ የራሳችሁ ናትና ውሰዷት።
በዚች ታሪካዊ ቀን ግን ዶ/ር አቢይ አህመድ የኤርትራ ልኡካን ቡድንን እንድጠይቁ አንድ ጥያቄ እወረውራለሁኝ ይሄውም በኤርትራዋ የድንበር ከተማ በሆነችው ባድመ እንብርት ላይ ፍትሃዊ ባልሆነ ጦርነት ተማግደው ህይወታቸው ላለፈ ጀግና ኢትዮጵያውያን ሀውልት ይሰራላቸው ዘንድ እንድነጋገሩ ነው።
በተረፈ ዶ/ር አቢይ አህመድ ዛሬም እንደገና ላስመዘገበው ድፕሎማሲያዊ ድል እንኳን ደስ አለህ እላለሁኝ።