>

እውነተኛ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ያገለለው የነገው የቤተ መንግስት ጥሪ ( የኋላሸት ዘሪሁን ሺፈራው)

እውነተኛ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ያገለለው የነገው የቤተ መንግስት ጥሪ 

( የኋላሸት ዘሪሁን ሺፈራው)

ከዚህ ቀደም ማቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዘናዊ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ባናገሩበት ወቅት እጅግ አስቂኝ ና አሳፋሪ ነገሮች ተከስተው ነበር ።የፕሮግራሙ አስተባባሪ የነበሩት “ልማታዊ አርቲስቶች” በነገራችን ላይ እነዚህ ባለሞያዎች በሁለት ይከፈላሉ የመጀመሪያዎቹ በፊት ለፊት መንግስትን እሚደግፉና ከቤተ መንግስት ድርጎ እሚሰፈርላቸው ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ደግሞ የህዝብ ወገንተኛ ነን እሚሉ ህዝብ እሚወዳቸውን ታሪካዊ ሁነቶችን እያነሱ “ከኔ የበለጠ ኢትዮጵያዊ የለም” እሚሉ ከህዝብ ና ከ እውነት ጋር ወግነናል እሚሉ ነገር ግን በጓሮ በር ሄደው እሚሞዳሞዱ (እሚንጎዳጎዱ) ወይም ደግሞ ከባለስልጣናት ጋር በጥምረት እሚሰሩ ናቸው

ወደ ዋናው ነጥቤ ቶሎ ልግባ የዛኔ …አቶ መለስ ዜናዊ “የተለያዩ ባለሞያዎችን ማናገር እፈልጋለው” ሲሉ በፍጥነት ኮሚቴ ተቋቋመ ኮሚቴው ሆድ አደሮቹንም እውነተኛ ባለሞያዎችንም በጋራ የያዘ ነበር ። ምን ያደርጋል… እውነተኛ ባለሞያዎችን ሆን ተብሎ ከኮሚቴ አባልነታቸው እንዲወጡ ተደረገ የቀሩትንም አቅም አሳጥተዋቸው መወሰን እንዳይችሉ አደረጓቸው በመቀጠል በወቅቱ ከ ኢሃዲግ ፅህፈት ቤት ከተወከሉ ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን “ማን ይጠራ ማን ይቅር ማን ምን ይጠይቅ ” በሚል ከብዙ አተካሮ በኋላ ጥያቄ ጠያቂዎቹ ሰዎች(የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች) የተመረጡ ጥያቄዎች ተሰጧቸው ልምምዱም ቀጠለ ቤተ መንግስት ጥያቄ እንዴት መቅረብ እንደሚገባ እንደ ተውኔት በቃል ተሸመደደ…

አይደርስ የለም ቀኑ ደረሰ የተውሸለሸሉ ጥያቄዎች ቀረቡ: “ደሞዝ ይጨመርልን, ካሜራ እናስገባ, የተከለከሉ ቦታዎች ላይ ፎቶግራፍ እንድናነሳ ይፈቀድልን…” ወዘተ ብዙዎችን ያሸማቀቀው ጥያቄ አሳፋሪ በሆነው በሰራዊት ፍቅሬ ተደርሶ በተዘጋጀው ተውኔት የተጀመረው ፕሮግራም በሃፍረት ተገባደደ ሰውዬውም እንደ ጉድ ሙድ ያዘ “እኔ ብሆን የዚህ አይነት ተውኔት አልፅፍም ነበር” ሲል ተሳለቀ…

በወቅቱ ይሄንን አካሄድ ከተቃወሙት ውስጥ ሰዓሊ ስዩም አያሌው “ሰራዊትና ሰራዊቶቹ “በሚል በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የነበረውን ሸፍጥ ቁልጭ አድርጎ እሚያሳይ ፅሁፍ አወጣ አስቂኙ ነገር ደግሞ ለዝግጅቱ መጨናገፍ ዋነኛ ተዋናይ የነበሩት ልማታዊ ጅቦች “የፈሲታ ተቆጢታ “እንዲሉ አበው ከ ኮሚቴ “አባልነታችን ለቀናል “በማለት በአደባባ ተናገሩ
አሁንም እነዚሁ ሰዎች ማሊያቸውን ቀይረው ከአዲሱ ጠቅላያችን ጋር “እንደመራለን “ሲሉ በጓሮ በር ወደ ቤተመንግስት ገቡ እናም በነገው እለት ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ ስነ ጥበብ ባለሞያዎች ጋር በ ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ለሚኖረው የጋራ መድረክ አዛዥ ናዛዥ ሆነው ቁጭ አሉ ።
መድረኩ ላይ ሊገኙ እሚገባቸው ብርቱ ሰዎች (እውነተኛ) ባለሞያዎች እንዳይገኙ የተለደ ሻጥራቸው ሰሩ ለመሆኑ እዚህ ፕሮግራም ላይ አንዱ እንዲገኝ ሌላው እንዳይገኝ የተደረገው በምን መስፈርት ነው? እማይመለከታቸው ሰዎች ተጋብዘው እሚመለከታቸውን ባለሞያዎች አለመጋበዝ ምን እሚሉት ፈሊጥ ነው?
በተለይም የዚህ ፕሮግራም አስተባባሪዎች “መደመር “እሚቻለው ከ ተንኮል ፀድቶ ከሸፍጥ ተቆጥቦ በሌብነት የጨቀየን እጅ አንፅቶ ነው እንጂ “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ” እየሆናችሁ አታስቸግሩን! (ጊዜው የመሞዳመድ ሳይሆን የመደመር ነው!)

Filed in: Amharic