>

ኤርትራውያን ወንድም እህቶቻችን ክረምቱ ሳይወጣ ኑ እንቁጣጣሽን አብረን እናክብር!! ጠ/ሚ አብይ አህመድ 

ኤርትራውያን ወንድም እህቶቻችን ክረምቱ ሳይወጣ ኑ እንቁጣጣሽን አብረን እናክብር!!

ጠ/ሚ አብይ አህመድ 
.– አርቲስቶቻችን መጭውን አዲስ አመት የምናከብረው አዲስ አበባ እና አስመራ ስለሆነ ተዘጋጁ
– ምጽዋ ላይ ዎክ ማድረግ ያማራችሁ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ስለሚጀምር እንድትዘጋጁ
– ከኤርትራ ወንድሞቻችን ሲመጡ እንኳን መጻእኩም ብላችሁ እንድትቀበሉ
– ኢትዮጵያውያን የሚያምርባችሁ ፍቅር ብቻ ነው። የጸቡ ጊዜ እንደ አንበሳ እንደ ነብር ስለሚያደርጋችሁ ጸጉራችሁ ሁሉ ይቆማል ። በፍቅር ጊዜ ፊታችሁ ሁሉ ጥርስ ይሆናል። ያ ነው ማማራችሁ።
– ከኤርትራውያን ወገኖቻችን ጋር የሚያዋጣን ፍቅር ብቻ ነው። ጸቡን ሞክረነዋል። በሁለታችንም ወገን አክሳሪ ነው።
– ለልጆቻችን ጸብ፣ጥላቻ እና ቂም አናውርሳቸው…
– ለእርቅ የሚከፈለውን ማንኛውንም ዋጋ ከፍለን ከኤርትራውያን እህት ወንድሞቻችን ጋር ተደምረን ለማደግ ከፍተኛ ፍላጎት አለን

 

Filed in: Amharic