>

ቢሮክራሲው መደርመስ ያለበት አፓርታይዱ አየር መንገዳችን!!! (ቬሮኒካ መላኩ እና ...)

ቢሮክራሲው መደርመስ ያለበት አፓርታይዱ አየር መንገዳችን!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ምኑም ያልተነካ ግን ውስጡ መፈተሽ ፣  መበርበርና ቢሮክራሲው መደርመስ ያለበት አንድ ተቋም አለ ። ይሄ ተቋም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይባላል።
ይህ አየር መንገድ በአንድ ብሄርና ቋንቋ ተናጋሪ የተወረረ መናድ ያለበት ድርጅት ነው።
በአንድ ወቅት 50 ሆስተስ አስመርቆ 50 ውም ከትግራይ ክልል ብቻ የመለመለ እጅግ ዘረኝነት እስከ አፍጢሙ የሞላው ተቋም ነው።
ይሄ አየር መንገድ ” የትግራይ አየር መንገድ ” እየተባለ በአፍሪካውያን ሁሉ ስም ወጥቶለት ነበር። ይሄ አየር መንገድ ውስጥ ካሉት ሱቆች ፣ ካፌዎች ጀምሮ በአንድ ብሄር የታጨቀ የዶላር ጥቁር ገበያ የሚያቀላጥፉ ኮንትሮባንድስቶች የሞሉበት ነው። በተጨማሪም ይሄው ተቋም በአንድ ብሄር አባላት በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሚሰራበት እና የሀገሪቱ ውድ እቃዎች ቅርሶችን ጨምሮ ህንድ እና ቻይና የሚያጉዙበት በአለም አቀፍ ህግ የተከለከሉ ነገሮች ሁሉ የሚዘዋወሩበት ተቋም ነው።
ዛሬ ይሄ ውስጡ በግማት የተሞላ ድርጅት አንድን ተሳፋሪ አማራ በመሆኑ ብቻ በአየር መንገዱ እንዳይጓዝ ከልክሎታል። ይሄ በምንም መልኩ ልንቀበለው የማንችልና በአፓርታይድ ዘመን እንኳን ያልተደረገ ከወራዶችና ከቀን ጅቦች የሚጠበቅ ወራዳ ተግባር ነው።
ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ይሄን ተቋም በፍጥነት ፈትሸው ተቋሙን በወረሩት የአንድ ብሄር አባላት ላይ ስር ነቀል ለውጥ እንድያደርጉ እጠይቃለሁኝ።
የኢትዮጵያ ወይንስ የትግራይ አየር መንገድ?
ይስሀቅ መኮንን
.
ባለፈው ሰሞን አየር መንገዱ 27 ሆስተሶችን (የሴት አስተናጋጆችን) ሲያስመርቅ በሚያስገርም ሁኔታ ሃያ ሰባቱም ትግሬዎች ናቸው። ፊንፊኔን የማያውቁና ብዙዎቹ ፊንፊኔ ውስጥ ቤተሰብ የሌላቸው ፍጹም ባላገር ሴቶች ናቸው። የተቀጠሩት ሁሉም ከትግራይ ምድር ነው። ለመሃላ እንኳን አንድም የሌላ ዘውግ  አልተቀላቀለባቸውም ፡፡
ታድያላቹ ባለፈው አንድ ጊዜ ወደ አፋር ዋና ከተማ ወደ ሠመራ አንድ የሀገር ውስጥ በረራ ነበር። ከነዚያ 27ቱ አንዷ አማርኛ እንደቁመት ያጠራት አስተናጋጅ ትግሬ “ህጅ አሥመራ ስለተቃሪብና ለቀቦቷቹ አጣብቁት” በማለት ለተሣፋሪዎች ማስታወቂያ በመናገሯ ተሣፋሪዎች አውሮፕላኑ ተጠልፎ አሥመራ ገብቶ ነው
በሚል ተደናግጠው ክው ይላሉ። በኋላ ግን የቋንቋ ችግር መሆኑ ተነግሯቸው አሥመራ ሣይሆን ሠመራ
እንደደረሱ ተገልጾ ይቅርታ ተጠይቀዋል -ተሣፋሪዎች። ሐሰት እንዳይመስልህ ሁሉም የአየርመንገዱ ሠራተኛ ሰምቶ የሚያላግጥበት እውነተኛ ታሪክ ነው።
ከወርቆቹ ዘር ካልሆንክ አየር መንገዱ ለአንተ ቦታ የለውም!!!
አማን ተስፋዬ 
እኔ ደግም የደረሰብኝን ልንገራችሁ፡ ከዪኒቨርሲቲ ተመልምለን አየር መንገድ ለፈተና ተላክን፡ ፈተና ተፈተንን፡ በወቅቱ ለፈተና የቀረብነው 1000 አካባቢ እንሆናለን፡ ነገር ግን ከተፈተንነዉ ጓደኞቼ ለመዳኒት እንኳን አንዳችንም አልገባንም፡፡ ከ 2 አመት በኀላ ሚስጥሩን ደረስኩበት፡፡ አንዱን ጓድ ሽይ ቤት ባጋጣሚ ተገናኝተን ስንጫወት ስለ ትምህርትና ስራ ተጫወትን፡፡ የኔን ነገርኩት የሱን ቀጠለ “የተማርኩት መቋሌ የግል ኮሌጅ ነው፡ 165  ነን ፤ 165 ታችንም አየር መንገድ ነው የገባነው ” አለኝ እንዴት ሁላችሁም ፈተናዉን አለፋችሁ አልኩት? “አይ ፈተና አልተፈተንንም ቀጥታ ነው ስራ የገባነዉ” አለኝ፡ የገቡትም ዓ/ም ሲነግረኝ ልክ እኛ ለሲምቦል የተፈተንበት ዓ/ም ነበር፣ አይ አሪፍ ነው አልኩት፡፡ ውስጤ እያረረ እየተቃጠለ፡፡ ተመልከቱ የራሳቸዉ  ሰው ነው እንደ ጨዋታ አድርጎ ሳያውቀው ትልቁን ሚሰጥሩን የነገረኝ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሬ ነው አየር መንገዱ በአንድ ብሔር መጥለቅለቁን የተረዳሁት እውነቱንም ያወቁት፡፡ ያለዉድድር ትልቅ ድርጅት ላይ ቀጥታ አንድ ብሔር ሌላውን እየተረማመደ መግባት ምን ያህል በገዛ አገርህ የሁለተኛ ደረጃ ዜጋነት እንዲሰማ አስቡት፡፡
በተያያዘ:-
 
የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ ርምጃ ወስዶ ሪፖርት እንዲያደር ታዟል
ቬሮኒካ
በአፄ ሀይለስላሴ እና በጠቅላይ ሚ/ር አክሊሉ ሀብተወልድ ያላሰለሰ ጥረት ተመስርቶ የአፍሪካ ኩራት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ   ውስጥ በፍጥነት እየተከናወኑ ያለ ሪፎርም የሚከተለው ነው :-
1ኛ ~ በቅርቡ በጠ/ሚ አቢይ አህመድ ትእዛዝ መሰረት ጥናት ተጠንቶ ከ 900 በላይ የቅጥር መስፈረት ያለሟሉና ያለህግ የተቀጠሩ የትግራይ ተወላጆች መኖራቸው ተረጋግጦ ለአቶ ተወልደ እርምጃ ወስዶ ሪፖርት እንዲያደርግ መመሪያ ተሠጥቶታል።
2ኛ~ የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደም ህንድና ቻይና የቅርስ ኮንትሮባንድ ሲያስነግድበት የኖረውን አየር መንገድ ኦዲት ካስደረገ በኋላ ቀጣዩን ውሳኔ እንዲጠባበቅ ተነግሮታል።
Filed in: Amharic