>
5:16 pm - Sunday May 24, 3164

ቤንሻንጉል ጉሙዝ- የሴረኞች የትግል ሜዳ

by Mengistu D. Assefa

የክልሉ እዉነታዎች

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በብሄሮች ስብጥር ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ትቀመጣለች፡፡ ከአጠቃላይ ነዋሪዎች የክልሉ አምስቱ ብሄረሰቦች 57.5% ሲይዙ ሌሎች ኢትዮጵያን 41.5% ናቸዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ ዋነኞቹ በርታ 25.9%፤ አማራ 21.25%፤ ጉሙዝ 21.11%፤ ኦሮሞ 13.32%፤ ሺናሻ 7.6%፤ማኦ 1.9%፤ ኮሞ0.96% ይወክላሉ፡፡ በጥቅሉ ከ70 በላይ ብሄረሰቦች ክልሉ ዉስጥ ይኖራሉ፡፡ የሀይማኖተ ሰበጥሩነ ስናይ እንደዛወ ነዉ፡፡ ክርስቲያን 45% ሙስሊም 45% ናችዉ፡፡ ባጠቃላይ ክልሉነ ትንሹዋ ኢትዮጵያ ብለን መጥራት እንችላለን፡፡ እንዲ ባለ ክልል ዉስጥ ዛሬ አንዱን ብሄር ማፈናቀል ለተጀመረ ነገ ሌሎቹ ተረኛ መሆናቸዉ አይቀሬ ነዉ፡፡ ይሄን ክስተት ተከትሎ ከሚመጣዉ ማህበራዊ ምስቅልቅልና ከሚያደርሰዉ ጠባሳ በላይ የሚያሳስበዉ ተከትሎት የሚመጣዉ ሀገራዊ የፖለቲካ ቀዉስና በሌሎች ክልሎች የድርጊቱ ምሳሌነት ነዉ፡፡ እዚህ ከተፈጸመ ሌላ ቦታ የማይደገምበት ምክንያት አይኖርም፡፡

ችግሮቹ

በ1981 አማራ ተወላጆች ተረሽነዋል፡፡ በድሀረ ኢሀአዴግ ዘመን ምርጫን በተመለከተ በክልሉና በአማራ ተወላጆች መካከል ዉዘግብ ተነስቶ ነበር፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለአማሮች በመፍረዱ ክልሉ ተከፍቷል፡፡ ከአመታት በፊት የክልሉ ሽምቅ ተዋጊዎች በኩርሙክ አካባቢ መኪና ዉሰጥ የነበሩ ከ60 በላይ “መጤዎችን” ገለዋል፡፡  እስከ ቅርብ ጎዜ ድረስ የአማራ ተወላጆች ሲፈናቀሉ ነበር፡፡ የዛሬ 10 አመት የክልሉ ታጣቂዎችና ባለስላጣናት ባደረሱት ጥቃት በኦሮሚያ ክልል ድንበርና አጎራባች አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወት ቀጥፈዋል፡፡
በሌላ በኩል ከሕወሀት ጋር ቁርኝተ ያላቸዉ ስፍር ቁጥር ሌላችዉ “ኢንቨስተሮች“ ቅኝ ግዛት በሚመስል መልኩ የክልሉን መሬት በገፍ ተከፋፍለዉታል፡፡ በዚህ ምክንያት “ኢንቨስተሮቹ“ የክልሉን ኢኮኖሚ ብቻም ሳይሆን የክልሉን መዋቅሎች ተቆጣጥረዉ ያሻችዉን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ በተጨባጭም የክልሉ “ሞግዚት አስተዳዳሪዎች“ ሆነዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ግጭቶችና ማፈናቀሎች የበዙትና የሰፉት እነዚህ “ሞግዚት አስተዳዳሪዎች“ ከመጡ በኋላ ነዉ፡፡ የአማራን ክልል መሬት በመቁረስ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድንበር ከትግራይ ክልል ድንበር ጋር እንዲገናኝ ተደርጎ ታትሞ የነበረዉ ካርታም በትግራይ ክልል መንግስት ተሳትፎ በነዚሁ “ሞግዚት አስተዳዳሪዎች“  የተቀነባበረ ነበር፡፡

ዛሬም በክልሉ አካባቢ እየተስተዋለ ያለዉ ማፈናቀልና ግጭት የዚሁ ሴራ ቀጣይ አካል አርጎ ማሰብ ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን ሕወሀት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን እንደ ጠንካራ ይዞታና ቤዝ በመጠቀም አዲሱን ዶ/ር አብይን አስተዳደርና እየመጣ ያለዉን ለዉጥና መተባበር መፈታተኑ አይቀሬ ነዉ፡፡ የቅርብ ጊዜዉ የአባይ ጸሀዬ የአሶሳ ጉብኝት ጥሩ ማሳያ ነዉ፡፡

በአሶሳ ከተማ የብሔር ግጭቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሬሳ

መፍትሄዎቹ ዉስጥ

በመሆኑም  የዶ/ር አብይ አስተዳደርና ሌሎችም በክልሉ ያሉትን የፖለቲካ ችግሮች መፍታት፤ አስተዳደሩ ዉስጥ የተሰገሰጉትን ሴረኞች ማጋለጥና ለህግ ማቅረብ እንዲሁም በክልሉ ዉስጥ ያሉትን ህዝቦች ግንኙነት ማጠናከርና አለበት፡፡ ከዚህ ሌላ ፖለቲካ ስልጣንን ተገን በማድረግ ከክልሉ ህዝቦች የተዘረፉትን መሬቶችና የማዕድን ስፍራዎች የንግድ ስራዎችን ፈቃድ መከለስና መሰረዝ ተገቢ ነዉ፡፡ ለተጎጆዎችም ሀብታቸዉን ከማስመለስ ወይም ካሳ ከማስከፈል በተጨማሪ ከኢኮኖሚዉ ተጠቃሚነታቸዉን ይበልጥ ማረጋገጥ የመፍትሄዉ አካል መሆን ይኖርበታል፡፡

በመጨረሻም  ፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ክልሉ ያቀረበዉ ጥያቄ አሻጥር ሊኖረዉ ይችላል (አባይ ጸሀዬ ሊኖርበት ይችላል)፡፡ ማለትም  የሚላከዉ ሀይል ቀድሞ የተለየና የአሻጥረኞቹን አላማ ለማስፈጸም አካባቢዉ ላይ ያለዉን ችግር እንደሚያባብስ ታሳቢ መደረግ አለበት፡፡ ልብ በሉ ጣልቃ ገብነቱን የጠየቁት የክልሉ ባለስልጣን በአሮጌዉን የፖለቲካ ቋንቋ መናገራቸዉና “ፀረ ሰላም ሀይሎች“ የሚለዉን ኮሚክ ወደ መድረክ መመለሳቸዉ አጋጣሚ አይደለም፡፡ በመሆኑም ወደዛ የሚላኩት የጸጥታ አስከባሪዎችና አዛዦች ምልመላ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ የስራ አፈጻጸማችዉንም በየዕለቱ የሚከታተል ታስክ ፎርስ ማቋቋም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

Gemechis A Duguma

Filed in: Amharic