>

“ከመጣው ጋር ማሸርገድ እዚህ ጋር ይቆማል።” ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአርቲስቶቹ መድረክ የተናገሩት

ቃሊቲ ፕሬስ

በዛሬው እለት በቤተ መንግስት ከአርቲስቶች ጋር የተከናወነው የስልጠና አላማ ኪነ ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ምን መሆን አለበት እና ከአርቲስቶች ምን ይጠበቃል የሚል እንደ ነበረ ተሰብሳቢዎች ለቃሊቲ ፕሬስ ገልጸዋል።

በእለቱ ውይይቱን የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድም እነዚህን ነገሮች  ተናግረዋል።

1 ጌትሽ ማሞ እና ቴዎድሮስ ተሾመን በስም ጠርቱ አብረን አድገናል ጓደኛ ነን አሁን ግን ቤተሰብ ነን ምናምንም የምትሉተ ከዚህ በኃላ አያዋጣም።  ከመጣው ጋር ማሸርገድ እዚህ  ጋር ይቆማል። ከዚህ በኋላ አውቀዋለሁ ምናምን  ማለት አይሰራም።  ሁሉም እኩል መታየት አለበት፣

2 አርቲስት ሙዚቃኞች 10 ሺ ብር ካሙዙ ጋር ከፍላችሁ ታሰራላችሁ እሱ አሰቃየኝ ብላችሁ  ኤልያስ  መልካ ጋር ሄዳችሁ ታሰራላችሁ ለስራው ሁለታቹም ወገኗች ስርዓት  የላቹህም።

3 ህዝብ ለህዝብን መድገም አለብን

4 ቤተ መንግሥት  ውስጥ  ቲያትር  ቤት የመገንባት ሃሳብ አለኝ

ይሁንና በውይይቱ ላይ የተሳተፉት አርቲስቶች አንዳቸውም ጥያቄ  ሳይጠይቁ መውጣታቸውንና ከውይይቱ ይልቅ ብዙ  ሰዓት የፈጀው ቤተመንግስት በመጎብኘት  ነው ተብሏል።

Filed in: Amharic