>

የሰመራው የህውሃት ቀሽም ድራማ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የሰመራው የህውሃት ቀሽም ድራማ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ባለፈው ታስታውሱ ከሆነ  አብዴፓዎች አፋር ሰመራ ላይ ዶ/ር አቢይ አህመድን እንዳስከፉትና ቀደም ብሎ ፕሮግራም የወጣለትን የምሳ ፕሮግራም ሰርዞ ከሰመራ ወደ አዲስ አበባ እየበረረ እንደነበር ፅፌ ነበር።
ለዚህ ደሞ ምክንያቱ ህውሃት የአብዴፓን ለምድ ለብሳ እንደገባችና አገር ወዳዶቹ አፋሮች ገና ከጅምሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዳያገኙ ተደብድበው መታሰራቸው ነበር።
 ዶ/ር  አቢይ አህመድ ሰመራ ከተማ ተጎንጉኖ የነበረውን ሴራ ቀድሞ ደርሶት ስለነበር ብስጭቱን ዋጥ አድርጎ ነበር ወደ አዳራሹ የገባው። በተለይ እውነተኛዎቹ የአፋር ህዝብ ተወካዮች አዳራሽ እንዳይገቡ መከልከለሰቸው ሳያንስ ተደብድበው መታሰራቸው  ጠቅላዩን እጅግ አበሳጭቶት ነበር።
የሆነው ሆኖ ህውሃት የአብዴፓን ጭምብል ለብሳ አዳራሽ መግባቷን ከሚያረጋግጡት ነገሮች ውስጥ የተጠየቁት ጥያቄዎች ነበሩ ።
ለማንኛውም ሙሉ ስእሉን ትመለከቱ ዘንድና ጥያቄዎቹም ሙሉ በሙሉ የህውሃት እንደነበር ያዙልኝና ለምሳሌ ይሆናችሁ ዘንድ ሰአትም ላለመፍጀት ከጥያቄዎቹ ውስጥ ሁለቱንና ዶ/ር አቢይ  የመለሰውን መልስ ላቅርብ።
ጥያቄ 1 ተጠየቀ፦
ደርግን የሚያክል ጉዙፍ ጨፍጫፊ ለገረሰሱ ታጋዮች ክብርና እዉቅና ለምን አይሰጣቸዉም?
( በዚህ ጥያቄ ላይ ምን ትዝ አላችሁ?  ታስታውሱ ከሆነ ህውሃት ከሶስት ሳምንት በፊት በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ አንዱ የወሰነው ውሳኔ መንግስት ለአንጋፋ ታጋዮች እውቅና ይስጥልን የምትል ነበረች። ይችው የህውሃት ውሳኔ ሰመራ ላይ የአብዴፓነን ለምድ ለብሳ ከች አለች)
#መልስ በጠቅላያችን፦ ሲጀመር ደርግን የጣለዉ ኢህአዴግ ሳይሆን ደርግ እራሱ ነዉ።”
በዚህ መልስ ዶ/ር አቢይ ደሞ እጅግ ቅኔ በተሞላበት መልክ  ለዘራፊ እውቅና እንደማይሰጥ “ደርግን እኮ የጣላችሁት እናንተ አይደላችሁም በማለት መለሰ ።
ጥያቄ 2 ተጠየቀ~ በኢህአድግ ውስጥ ነፋስ ገብቷል ይባላል ። እባካችሁ ድፈኑት?
የጠቅላዩ መልስ ~ በኢህአድግ ውስጥ ነፋስ ሲገባ የመጀመሪያ አይደለም ። በፊትም በተደጋጋሚ ነፋስ ገብቶ የሚቆረጠው እየተቆረጠ እየተቀነሰ እዚህ ደርሰናል። አሁንም ነፋስ እንዳይገባ ኢህአድግን በጭቃ እየደፈንን ሳይሆን የምንጓዘው የሚቆረጠውን እየቆረጥን እንሄዳለን።
በተለይ ይሄኛው መልስ ኢህአድግ ወስጥ ያለው ስንጥቅ እየሰፋና በቅርቡ ወደለየለት ፍትጊያ በመግባት የለውጥ እንቅፋት የሆኑትን ሀይሎች አቢይ የተባለ ሱናሚ ጠራርጎ እንደሚያ  ቸው የተመለከትኩበት ነው።
ለማንኛውም አብዴፓዎች የራሳቸውን መድረክ አሳልፈው ለህውሃት መስጠታቸው እጅግ በጣም ሳይቆጫቸው አይቀርም ። በእውነትም የሚያስቆጭ ነው።
ጠ/ሚ አብይ ኣህመድ በአፋር ያደረጉትን ውይይት ለመመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ
Filed in: Amharic