” ድመቷ አቢዮት!!!”
ቬሮኒካ መላኩ
በዚህም የተነሳ በየትኛውም አገር ከተከሰተው ታሪካዊ ክስተት አንፃር አቢዮትን ” ድመቷ አቢዮት “ በማለት ይጠሯታል ።
በፓርቲ ውስጥ የሚደረግ አቢዮትም ያው የድመት ፀባይ ነው ያለው።
…
ታላቁ የፈረንሳይ አቢዮት የበኩር ልጇን ሮቢስፔርን በጊሎቲን በልታለች ። የእንግሊዙ ደም አልባ አቢዮት እየተባለ የተሞካሸው አቢዮት ልጇን ኦሊቨር ክሮምዌልን በልታለች።
የሩሲያው የጥቅምት አቢዮት አንቀሳቃሹ ኮሚኒስት ፓርቲ ትሮትስኪን በልቷል።
በኢትዮጵያው አቢዮት ደርግ የተባለው ስብስብ የመጀመሪያ ልጁን አጥናፉ አባተን በልቷል።
ኢህአፓ እንኳን በአቅሟ ጌታቸው ማሩን በልታለች። ህውሃትም እነ ገብሩ አስራትን ባይበላቸውም ቆርጦ ጥሏል። ኦህዴድም እነ ሙክታር ከድርን ፣ እነ አስቴር ማሞን ገለል በማድረጉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ግስላ ሆኖ ወጥቷል።
…
አሁን ተራው የብአዴን ነው።
ብአዴን የድመቲቱን የፓርቲ አቢዮት ባህሪ ይላበስ ዘንድ ግድ ሆኗል። ብአዴን እነ በረከት ስምኦን ፣ህላዌ ዮሴፍ ፣አለምነው መኮንን ፣ ጌታቸው አምባዬ ዝማም ፣ ገነት ገ/እግዚአብሄር ወዘተረፈ የሚባሉ ቆሞ ቀር የቀን ጅቦችና የህውሃት ተላላኪዎች ለማስወገድ ከመጨረሻው ምእራፍ ላይ ይገኛል። ብአዴን እነዚህን እፉኝቶች አስወግዶ ህዝባዊ ፓርቲ ለመሆን በሚያደርገው ጥረት ሁሉም ሊያግዛው ግድ ይላል ።
አሁን የድመቲቱ የፓርቲ አቢዮት ተራ የብአዴን ነው።ባቡሩ ሃዲዱን ጠብቆ ይጓዝ ዘንድ መቆረጥ ያለበት መቆረጡ የፖለቲካ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው።