>
5:13 pm - Friday April 18, 2775

ይህ ጉዳይ ስስ ቢሆንም አንድ ነገር ማለት እንዳለብኝ አምናለሁ!!! (ሞሀመድ እድሪስ)

ይህ ጉዳይ ስስ ቢሆንም አንድ ነገር ማለት እንዳለብኝ አምናለሁ!!!
ሞሀመድ እድሪስ
ይህ ባንዲራ የተለያዩ አርማዎች ታክለውበት በየወቅቱ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ከየወቅቱ ፖለቲካ ጋር የሚጨምርና የሚቀንስ ቢሆንም ቀላል የማይባል ህዝብም ለየባንዲራዎቹ ድጋፍ እና ተቃውሞ አለው፡፡ ይሄንን ስሜት ማክበር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ህዝብ የትኛውንም የባንዲራ አይነት ሲያነሳ ባንዲራውን ስለሚወክሉ ወይንም ይወክሉ ስለነበሩ ስርአቶች ድጋፉን እየሰጠ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ከዚህ ይልቅ የብሄርተኝነት (Nationalism) ስሜት መገለጫ ማድረጉ ነው መሰረታዊው ጉዳይ፡፡
ዳር ድነበር ለማስከበር ደሙን የሚያፈስ ወታደር ባለ ኮኮቡን ባንዲራ ለብሶ ሲታገል እና ሲወድቅ ጉዳዩ የኢህአዴግ መንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡  አንበሳ አርማው ላይ የነበረውን ባንዲራ ይዞ የዘመተ ወታደር በጦር ሜዳ ላይ ወድቆ ሲቀር የወደቀው ለናት ሀገሩ እንጂ በባንዲራው ላይ ለነበረው አርማ አልነበረም፡፡ ሁሌም ህዝብ እና ፖለቲከኞች በአንድ መስመር አይደለም የሚመዘኑት፡፡ በሰልፍ ላይ ለድጋፍ የወጣ ህዝብ ኮኮብ አልባውን ለብሶ ሲጨፍር አሁንም የአገር ፍቅሩን መግለጫ እንጂ ህዝብ በራሱ የጣላቸውና የቀበራቸውን ስርአቶች እያለመ አድርጎ መውሰድ አይቻልም፡፡ ኮኮብ አልባው ባንዲራ በህግ ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ግዚያት ባለኮኮቡን ባንዲራ ሚሊዮኖች ሆነን በመስቀል አደባባይ ይዘን ወጥተናል፡፡ ለኢህአዴግም ለቅንጅትም ተሰልፈናል፡፡ በጥምቀትና በዒድም ህዝቡ ይዞ ተገኝቷል፡፡  በነዚህ ሁሉ ግዚያት የሀገር ፍቅር ስሜት መግለጫ ምልከት እንጂ የትኛውንም ስርአት ወክለን እንዳልነበር ይታወቃል፡፡
በባንዲራው ተከልሎ ቄሮን ከፋኖ የመነጣጠል ሴራ!!!
መሰረታዊው ጉዳይ የልሂቃኑ፣ አርቲስቱ, ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ተቋማት በባንዲራው ላይ ያላቸው አቋም ነው፡፡ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ይወክለኛል የሚለውን ባንዲራ በይፋ የማሳወቅና ለዚያ የመታገል መብት አለው፡፡ ገዢው ድርጅትም በህገመንግስቱ ያፀደቀውን ሰንደቅ አላማ የመጠቀምና የማስከበር ግዴታ አለበት፡፡ ይላል
የአረናው አብርሀ ደስታ የሴራ ፖለቲካውን ህጋዊ ሽፋን  ለማልበስ እየተውተረተረ ሲቀጥልም..
… ኢትዮጵያን በአለምአቀፍ መድረክ ወክሎ የሚውለበለብን ሰንደቅ አላማ መቅደድ፣ መርገጥ እና ክብሩን ማጉደፍ የመሰሉ ህገወጥ ድርጊቶች ላይ እርምጃ መውሰድም ለፖለቲካ ስልጣን መደላደል በሚል ፈፅሞ ችላ የሚባሉ ጉዳዮች አይደሉም፡፡
እናም ህዝብ የሀገር ፍቅር ስሜቴን ይገልፅልኛል ብሎ ባንዲራውን ሲያውለበልብ የሀገር ፍቅር ስሜቱን ማንበብ መልካም ነው፡፡ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ተቋማት ግን ስለባንዲራ የሚይዙትን አቋም በህዝብ የሀገር ፍቅር ስሜት ውስጥ ሳይመሽጉ በግልፅ ሲያሳውቁ ስለታሪኩ፣ መገለጫው እና ተፅእኖው እንከራከራለን፣ የምናወግዘውንም እናወግዛለን፡፡
የባህርዳሩን “የድጋፍ” ሰልፍ አከብራለሁ። ግን ዶር ዐቢይን ለመደገፍ ነው ወይስ ደርግን (መንግስቱ ኃይለማርያምን)? ወይስ ሁለቱም ያው ናቸው? ዶር ዐቢይም ስለድጋፉ “አመስግኗል” አሉ። ግን ሲመስለኝ ለደርግ የተደረገ የድጋፍ ሰልፍ ነው። ዶር ዐቢይ ካመሰገነ እኔም ደርግ ነኝ እያለ ያለ ይመስለኛል። መብቱ ነው። ግን የትግራይ ህዝብ ደርግን እንደማይደግፍ መገንዘብ አለበት። የባህርዳር ህዝብ ደርግን ደግፎ ሲሰለፍ ከተመሰገነ የመቀለ ህዝብም ህወሓትን ደግፎ ቢሰለፍ ቅር የሚሰኝ አካል ሊኖር አይገባም። እኔ ግን ደርግ የአማራን ህዝብ እንደማይወክል ነበር ምከራከረው። ባለ ኮኮቡ ባንዴራ  “የህወሓት ስለሆነ” አንጠቀምበትም ከተባለ ልሙጡ ባንዴራም “የምኒሊክ ስለሆነ” አንፈልገውም የሚል አካል እንደሚኖር መገንዘብ ይኖርብናል። የቄሮ የትግል ዓላማ የደርግን ወይም የምኒልክን ስርዓት ማስመለስ ሳይሆን ነፃነት፣ እኩልነት እና ፍትሕ የሰፈነበት ሀገር ማየት ነው። የኦሮሞ ህዝብን ትግል ስደግፍ ነበር አሁንም እደግፋለሁ። ብዙ ለውጦችም አይተናል። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ግን አማካሪ ያለው አይመስለኝም። በመደመር ስም ሀገሪቷን እንዳይበታትናት እሰጋለሁ። አካሄዱ አላማረኝምና የኦሮሞ አክቲቪስትስ እስቲ ምክር ቢጤ አካፍሉት። ካልሆነ የቄሮ ትግል ሳያፈራ ይኮላሻል።
Filed in: Amharic