>

ስለ ባንዴራ ኣመጣጥ!?! (አምዶም ገ/ሥላሴ)

ስለ ባንዴራ ኣመጣጥ!?!
አምዶም ገ/ሥላሴ
) የኣፄ ቴድሮስ መንግስት፦
 ቀይ፣ ነጭ፣ ሰማያዊ ነበር።
፪) የኣፄ ዮውሃንስ ፬ መንግስት ፦ቀይ፣ ብጫ፣ ኣረንጓዴ ሆኖ በመሃሉ መስቀል ፊትለፊት የያዘ የሞዓ ኣምበሳ ምስል ያለበት
፫) የኣፄ ምኒሊክ መንግስት፦ ኣረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሆኖ በመሃሉ መስቀል ወደኋላው የያዘ ሞዓ ኣምበሳ ነው።(ከኣፄ ዮውሃንሱ ባንዴራ የቀለማቱ ኣቀማመጥና የመስቀሉ ኣያያዝ በተቃራኒ ነው)
፬) የደርግ መንግስት ባንዲራ ፦ ኣረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሆኖ በመሃል በዘምባባ የተከበበ፣ ከላይ ቀይ ኮከብ ያለበት፣ ሰማያዊ ጮራ ያለበትና የመንኮራኮር ያለበት ነበር።
፭) የሽግግር መንግስት፦ ኣረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ በማሃሉ ምንም ዓይነት ምልክት የሌለበት ልሙጡ ባንዴራ ነው።
፮) የኢህኣዴግ መንግስት ፦ ኣረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሆኖ ማሃሉ ላይ ባለ ኮከብ ክብ ሰማያዊ ህብር ኣለበት።
 በኢትዮጵያ የመንግስት ባንዴራ ታሪክ ውስጥ ልሙጡ ባንዴራ እውቅና ሰጥቶ የተጠቀመበት  የሽግግር መንግስት ብቻ ነው።
በተለምዶ ግን ኣረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ባንዴራ መጠቀም ከኣፄ ዮውሃንስ እስከ ኢህኣዴግ የባንዴራ ኣዋጅና የባንዴራ ቀን በዓል እስኪያውጅ በየቦታው፣ በየመስራ ቤቱ መጠቀም እንደ ነውር ኣይቆጠርም ነበር።
* ልሙጡ ባንዴራ ከመንግስታት በላይ በቤተ ክርስትያን ኣገልግሎት እየሰጠ መጥቶ በመስጠት ላይም ይገኛል።
በትግራይ በቤተ ክርስትያናት ፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ፋሲካ፣ወዘተ ጥቅም ላይ ይውላል። በማህበረሰባችንም ቀብር፣ ሰርግ፣ ተዝካርና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች በስፋት ሲውለበለብ ይታያል።
ስለዚ የሃገራችን መንግስታዊ እውቅና ያገኙ ባንዴራዎች በከኣፄ ዮውሃንስ እስከ ኢህኣዴግ የነበሩ ባንዴራዎች ቅርፃቸው ይለያይ እንጂ ከቀይ፤ ብጫ፣ ኣረንጓዴ ቀለማት ኣይወጡም።
* ኦነግም ቢሆን በባንዴራው ቀይ፣ ብጫና ኣረንጓዴ ናቸው።
* የዓረና፣ ኦፌኮ፣ ሲኣን፣ ኢሦዴፓና የድሮው ኣንድነት በጥምረት የፈጠሩት መድረክ የድርጅቱ ባንዴራ ልሙጡ ኣረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ኣድርጎ በ2002 ዓ/ም ሃገራዊ ምርጫ ውድድር ላይ ተሳትፎበታል።
Filed in: Amharic