>

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አሁን ያለበት ሁኔታ እና መንስኤው?!? (አዳነ አጣነው)

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አሁን ያለበት ሁኔታ እና መንስኤው?!?
አዳነ አጣነው
ሰሞኑን ሱዳን ከባህር ስንዱስ የሱዳን አንስተኛ መንደር በመነሳት ጙንግን ተሻግሮ ደለሎ ላይ ቁጥር አንድ ተብሎ በተሰየመ የእርሻ ይዞታ ላይ ከፍተኛ ሰራዊት አስፍሯል፡፡ ይህ የሱዳን ሰራዊት እስከ አብራጅራ ድረስ ሌሊት ሌሊት እየተንቀሳቀሰ በኢትዮጵያ ገበሬዎች ላይ አፈና እና የከባድ መሳሪይ ድብደባ ሲካሂድ ሰንብቶ ከትላንት ጀምሮ ከኢትዮጵያ መሬት ላይ እንደ ዋና ካምፕ/Base አድርጎ በመሰረተው ቦታ ደለሎ ቁጥር 1 ላይ ተሰባስቦ ሰፍሯል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የወያኔ ሰራዊት ትእዛዝ አልደረሰኝም በሚል እንዳውም በሱዳን ሰራዊት እራሱ እንዳይጠቃ ወደ ኻላ አፍግፍጙል፡፡ ይህ የሱዳን ሰራዊት ከደለሎ ደቡብ ወደ ሽመለጋራም ተመሳሳይ ገብሬዎችን የማፈናቀ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ከትላንት ወዲያ ገላባት ላይ የተካሄደው የወያኔ ሹመኞች እና የሱዳን ባለስልጣናት የስብሰባ ውጤት ገና ምን ውጤት እንደሚያመጣ የሚታይ ይሆናል፡፡በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ መሽቆጥቖጥ እና ልመና የሞላበት በወያኔ የመንግስት ወኪሎች በአሳፋሪ መልክ ታይቷል፡፡
የችግሩ መነሻ/Background:-
በ1991 በፈረንጅ አቆጣጠር የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ከሱዳን፣ CIA ፣MI5፣ ሞሳድ እና ከደርግ በተደረገለት ሰፊ ትብብር የደርግ መንግስት ሲወድቅ የሱዳን ጦር  የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የጙንግን ወንዝ በመሻገር በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ጦር በማስፈር የሱዳን ባለሀብት ገበሬዎችን አስፍሮ ከለላ በመስጠት ሱዳኖች የኢትዮጵያን መሬት ማረስ ጀመሩ፡፡
 ለአዲሱ ገዥ ለወያኔ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ወያኔም በወቅቱ በሰላም እንፈታውለን ጊዜ ስጡን በሚል ህዝቡ ከሱዳን ጋር እንዳይጋጭ  ተማጸነ፡፡ህዝቡም በተወሰነ ደረጃ የወያኔን ጊዜ ስጡኝ ጥያቄ ከሞላ ጎደል ተቀብሎ እስከ 1992 በትእግስት ጠበቀ፡፡
በ1993 ሱዳን እንዳውም ይባስ ብሎ ከልጉዲ በሁመራ አቅጣጫ እስከ ነብስ ገባያ ድረስ ወደ 400 ኪሎ ሜ የሚያዋስነውን ለም መሬት እስከ 40 ኪሜ ዘልቆ በመግባት ይዞታውን አስፋፋ፡፡ህዝብ  ለወያኔ አቤቱታ በተደጋጋሚ ቢያቀርብም ሰሚ ጠፋ፡፡
1993 የወያኔ መንግስት፣  ከወያኔ ሰራዊት የተቀነሱ አባላቱን ሽመለጋራ ላይ አስፍሮ የሱዳን ገበሬዎች ከኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ጥቃት እንዳይደርሳባቸው እንዲከላከሉ እና እራሳቸውም በመሀበር ተደራጅትው እንዲያርሱ አሰፈረ፡፡ሱዳን ለሰፈሩ የወያኔ የተቀነሱ ጦር አባላት ትራክተር እና ቁሳቁስ አቀረበ፡፡ እንዳአጋጣሚ እኒህ የወያኔ የተቀነሱ የጦር አባላት ሰፋሪዎች ቦታው ለጤናችን አልተስማማንም በሚል ካፓቸውን ለቀው 1994 ተበተኑ፡፡የኢትዮጵያ ገበሬዎች በተቻልቸው መጠን ከሱዳን ጦር ጋር በመጋጨት ብዙም ሰላም ሳይሰፍን ሆኔታዎች እንዳሉ ቀጠሉ፡፡
1995/1996 በፈረንጅ የትግሬ ወያኔ እና ሱዳን በመጣላታቸው መልካም እድል ፈጠረ፡-
የወያኔ መንግስት ለሱዳን ውለታ ለመክፈል የኢትዮጵያ መሬት ሲወረር ዝምታን ቢመርጥም (በ1995/96 በፈረንጅ) መልካም እድል ተፈጠረ፡፡የሱዳን የስለላ ድርጅት ከግብጹ የእስላም ወንድመማቾች/Islamic Brotherhood ጋር በመመሳጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሚስጥራዊ ህዋስ ፈጠሩ፡፡ወያኔ መረጃው ደረሰውና ለሱዳን መንግስት እርማት እንዲደረግ ጠየቀ፡፡ከኻላ ሆኖ የሱዳን መንግስትን ይመራ የነበረው ዶር አል ቱራቢ የወያኔን ጥያቄ ከምንም ሳይቆጥር መልስ ሳይሰጥ ቀረ፡፡
በ1995 የግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባረክ አዲስ አባባን ሲጎበኙ ከቦሌ ወደ ማረፊያ ቦታቸው ሲጙዙ የግብጽ Islamic Brotherhood ደፈጣ ተዋጊዎች ተኩስ በመክፈት በግብጹ መሪ ላይ የግድያ ሙከራ አደረጉ፡፡ ወያኔም በሁኔታው ተበሳጨ፡፡በግብጹ መሪ ግድያ ሙከራ የተሳተፉ ግብጻውያን  አምልጠው በከፊል ወደ ሱዳን ገቡ፡፡ ወያኔ ተጠርጣሪዎችን ሱዳን አስሮ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመልስ ይጠይቃል፡፡ ሱዳን በወያኔ ላይ አፌዘ፡፡
በወያኔ እና ሱዳን በግብጹ  መሪ የግድያ ሙከራ ምክኒያት ግንኙነታቸው ተበላሸ፡፡ጠረፍ አካባቢም እንዲሁ፡፡ በመተማ ደቡብ ታያ አካባቢ የወያኔ ወታደሮች ስለ ጠርፍ ጸጥታ ጉዳይ ለመወያየት 5 አባላት ወደ ሱዳን ታያ ይልካሉ፡፡ሱዳንም ከወያኔ የተላኩትን የጦር መልእክተኞች በጥይት ረሸነ፡፡ነገር ተበልሸ፡፡
የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ ሱዳን ያሳየነውን መልካም ወዳጅነት ወደ ንቀት ቆጠሩት/Abused our Relationship ስል ሱዳንን ወነጀለ፡፡ወያኔ በ1996 በፈረንጅ ከልጉዲ አቅጣጫ እስከ ነብስ ገብያ ድረስ በሱዳን ወታድሮች ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት ከፈተ፡፡ ከሳምንት ውጊያ በኻላ ሱዳን ተሸነፈ፡፡ብዙ የጦር ኣባላቱ አንድ ሙሉ ጀነራልን ጨምሮ ተማረከ፡፡ኤርትራ ጣልቃ  ገብታ ለማስታረቅ ሞክራ የሱዳኑ ጀኔራል ተለቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ገበሬዎችም ተደሰቱ፡፡ወያኔ እንደገና ሀሳቡን ቀይሮ 2006 በፈረንጅ ሱዳን የጙንግን ወንዝ ተሻግሮ እንድያርስ እንደገና ፈቀደ፡፡ክ2006 ጀምሮ በጠረፍ አካባቢ ሰላም አልሰፈነም፡፡ስፊ የኢትዮጵያ መሬት በሱዳን ገበሬውች ተወረረ፡፡ እንዳዉም ወያኔዎች ከሱዳን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት እያለች፣ አንድ ሽለቃ ግወይን የሚባል እንግሊዛዊ በራሱ አነሳሽነት የኢትዮጵያ መንግስትን ባልተሳተፈ ያሰመረውን መስመር ተቀብያለሁ ሲል ለሱዳን ህጋዊ ሽፋን ሰጠ።
Filed in: Amharic