>

በህወሀቱ ጄነራል የሚመራው ደም ያረገዘ የመፈንቅለ መንግስት ውጥን!! (ፋሲል የኔአለም)

በህወሀቱ ጄነራል የሚመራው ደም ያረገዘ የመፈንቅለ መንግስት ውጥን!!
ፋሲል የኔአለም
እነ ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ተክለብርሃን ወልዳረጋይ የሚመሩት ቡድን የለውጡን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ አሁንም የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረገ ነው። ከአረናና ሌሎች ድርጅቶች ጋር በማበር የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀምሯል። በጠ/ሚ አብይ አህመድና በሌሎችም ባለስልጣናት ላይ የመግድል ሙከራዎችን አድርጓል። የመብራትና የኔትወርክ እንዲሁም የአማራ ቴሌቪዥንን የባህርዳርን ዝግጅት በቀጥታ እንዳይተላለፍ ለማፈን ሞክሯል። በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንዲፈጠሩ ጥረቶችን አድርጓል። የአማራ ክልል ዋናው የግጭት ማዕከል እንዲሆን በመምረጥ በአሶሳና በኦሮምያ ድንበር አካባቢ ግጭት ለማስነሳት ሞክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል።  አሁን ደግሞ ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር፣ ሱዳን “በመሬት ይገባኛል” ስም ወረራ እንዲፈጽም አድርገውታል። በቅርቡ የተፈጸመውን ወረራ ብአዴን ሚሊሻውንና አርሶአደሩን አስተባብሮ ለመቀልበስ ሞክሯል። ዛሬም ተመሳሳይ ወረራ ተፈጽሟል።  ከሱዳን ጀርባ ሆኖ የመሬት ወረራ እንዲፈጸም የሚያደርገው ህወሃት ነው። ፌደራል መንግስቱና የብአዴን አመራር የክልሉንና የኢትዮጵያን ህዝብ አስተባብረው ህወሃት መራሹ የሱዳን ጥቃት እንዲቆም ማድረግ አለባቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ጄ/ል ክንፈ ዳኘውና ተክልብርሃን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማድረግ ደጋፊዎችን ለማሰባሰብ እየተንቀሳቀሱ ነው። አስተባባሪዎቹ ለዚህ እቅዳቸው ማስፈጸሚያ የመከላከያ ታርጋ የለጠፈችውን የጄ/ል ክንፈ ዳኛውን  መኪና እየተጠቀሙ ነው።  ክንፈ ዳኘው ስልጣኑን ቢለቅም ፣ መኪናው አልተወሰደበትም። መከላከያ መኪናውን ለመሰብሰብ ለምን እንዳልፈገ ግልጽ አይደለም። የደህንነት ሰዎች በዋና ተዋናዮች ላይ ፈጣን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ እቅዱን እየተከታተሉ ማጋለጥ የተሻለ ነው የሚል ስትራቴጂ እየተከተሉ ነው።   የዚህን ስልት አዋጪነት በሂደት የምናየው ይሆናል። በአጠቃላይ ግን የእነ ጄ/ል ክንፈ ዳኘውና ተክለብርሃን እቅድ በራዳር ውስጥ እንደገባ እነሱን ለመከተል ያሰቡ ሃይሎች ቢያውቁት አገራችንን አላስፈላጊ ከሆነ ደም መፋሰስ መታደግ ይቻላል።  በተለይ አረናዎች።
በዚህ አጋጣሚ ለስራ ጉዳይ ከአምስተርዳም ወጣ ብዬ ስለነበር የባህርዳሩን ሰልፍ በቀጥታ ለመከታተል እድል አላገኙሁም ነበር። በሁዋላ ላይ እንዳየሁት ሰልፉ እጅግ የተዋጣለትና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በሰልፉ ላይ የተሳተፉትን ዜጎች ፣ በበጎ ፈቃደኝነት ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ ከ1 ሺ በላይ ወጣቶች፣ የብአዴን አመራሮችና የደህንነት ሰዎችን  ማመስገን ይገባል።
Filed in: Amharic