>

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ!!!  

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ!!!
ጌታቸው ሺፈራው
ከሶስት ቀን በፊት ሱዳን ውስጥ የሚኖሩ የወልቃይት አማሮች ከሚቀርቧቸው የሱዳን ባለሀብቶች አንድ መረጃ ይደርሳቸዋል።  በአንድ ወቅት ባዕከር የሚባል ቦታ መምህር የነበርና በወልቃይት አማሮች ላይ ጥቆማ እያደረገ  በማሳሰር ለትህነግ በዋለው ውለታ ትህነግ የፀጥታ ኃላፊ ያደረገው ተኪ ተኩ በአዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደሰነበተ ይነግሯቸዋል። ይህን ጉዳይ እኔም ትናንት ምሽት ዘግቤው ነበር።
ተኪ መተኩ  ትህነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለው ወልቃይት ዞን ፀጥታ ኃላፊ ሲሆን  ገዳዲፍ፣ ገላባትና አዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች  በመዞር የትህነግ ደህንነቶች ጋር በመሆን የአማራ ገበሬዎች ላይ ጦርነት እንዲከፈት ሲያደራጅ ሰንብቷል።
የሱዳን ባለሀብቶች ለሱዳን ጦር ቀለብ እስከቻሉ ድረስ የጠየቁት የሰራዊት  ይሰጣቸዋል። የዚህን ውጊያ ዋጋም ተኪ የተባለው የትህነግ የፀጥታ ሀላፊ ገንዘብ ከፍሎ መመለሱን የሱዳን ባለሀብቶች ለወልቃይት ተወላጆች ተናግረዋል። በጉዳዩ መሳተፍ ያልፈለጉት ባለሀብቶች  “ከእናንተ ጋር ሊያጋጨን ነው” ሲሉ ቀድመው አሳውቀዋል።
የትህነግ የዞን ፀጥታ ሀላፊ ተኪ አስተባባሪነት የተደረገው ዝግጅት ሲጠናቀቅም፣ ለትህነግ ተባባሪ በሆኑ ባለሀብቶች በኩል በሶስት አቅጣጫ ጦርነት ተጀምሯል።በቋራ፣ በመተማ ቁጥር አንድ እና በጓንግ  በኩል የታቀደው ጦርነት በቋራና በመተማ በኩል ተጀምሯል። በቋራ በኩል የአማራ ገበሬዎች አንድ የሱዳን ፓትሮልን መማረክ ሲችሉ፣ በመተማ በኩል የተከፈተ ጦርነት የብዙ ገበሬዎችን ህይወት ቀጥፏል።
 በጓንግ በኩል ገበሬዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀ የሱዳን ጦር እንዳለ ታውቋል። በአማራ ገበሬዎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ያለው የሱዳን ሰራዊት ከባድ መሳርያ የታጠቀ ሲሆን ገበሬዎቹ ያዙት አጭር ርቀት መሳርያ ነው። በመሆኑም የክልሉ ልዩ ሀይል እገዛ እንዲያደርግላቸው፣ እገዛ ካላደረገም የረዥም ርቀት መሳርያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል ተብሏል።
በዛሬው ጦርነት የቆሰሉ ገበሬዎች እና የልዩ ሀይል አባላት በጦርነቱ ከሱዳን ጦር በተጨማሪ “ኢትዮጵያውያንም” አሉበት ሲሉ የተናገሩ ሲሆን “የወጋን ሕወሓትም ጭምር ነው ብለዋል። አንድ የልዩ ሀይል ሀላፊ ገንዳውሃ ከተማ መተማ ሆስፒታል የቆሰሉትን ለመጠየቅ ለሄዱት የከተማው ሀላፊዎች “የወጋን ህወሓት ነው” ሲል ተናግሯል።

 

Filed in: Amharic