>
5:13 pm - Wednesday April 18, 0942

ክፍል ሶስት ".... በስርአቱ መበስበስ ነው ሪዛይን ያደረግኩት!!" ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ

የቀድሞው የኢንሳ ዳይሬክተር ሜ/ ጀነራል ዶ/ር #ተክለብርሃንወልደአረጋይ በድምፂ ወያኔ ትግራይ ሬድዮ ቃለ መጠይቅ ፤ በኢትዮጵያ ላይ ያወጀው የጦርነት አዋጅ። (ከትግረኛ ወደ አማርኛ ቃል በቃል በ Kedir Endris የተተረጎመ)

ያለፈውን ያላነበባ ችሁ ቀጣዩን ይጫኑ …. በስርአቱ መበስበስ ነው ሪዛይን …..

ክፍል ሶስት

ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ:

እዋእ ማለት ከህዝብ ጥቅም አንፃር የማታስብ ከሆነ ሁሉግዜ ጫፎች የሚባሉ ነገሮች አይኖሩም። ወደ ሁሉም ጫፎች እንደፈልክ እንዳትገላበጥ የሚከለክልህ መርህ አይኖርህም።መርህ ስለማይኖር ወደ ስልጣን ለመውጣት ለግዜው ምንድነው የሚጠቅመኝ የሚል ነው አጀንዳው ማለት ነው። ስልጣንን ለመቆጣጠር ማለት ነው። ይህንን ስንል ግን አሁን ያለውን የህዝቡን ወቅታዊ ሁኔታዎች የምያንፀባርቅ አይደለም። እዋእ በእነዝህ ሁለቱ ህዝቦች ውስጥ በህዝቡ ላይም ችግር ይኖራል። አለም። ህዝቡም ችግር አለበት። በዋነኝነት ግን ኢሊት በምንለው ሃይል ነው ችግሩ ያለው። ከትምክህት በረት ነበር አሁን ወደ ጠባብነት በረት መግባት መቻል። በትምክህትና ጠባብነት መካከል መስመር የለም። መስመሩን እኮ አንጎላችን ነው የሚያሰምረው። በመሰረቱ ይህ ሁለቱ የተለያዩ ናቸው የሚለው አስተሳሰብ እኔን አይገባኝም። ጠባብ ሁኖ ትምክህተኛ ትምክህተኛ ሁኖ ደግሞ ጠባብ ይኖራል። አንተ ይህንን መለየት አትችልም። አንዳንዶቻችን እስካሁን ስናስብ በሁለቱ መካከል መስመር አስቀምጠን ነው የምናስበው። ከዛ አንዱ ወዳንዱ ሲሻገር በጣም ይገርመናል። ከጠባብነት ወደ ትምክህት ከትምክህት ወደ ጠባብነት መሸጋገር ሁኖ በረት ሲለዋወጡስ በጣም አስደንግጦን ይገርመናል። ግን መስሙሩን እኮ እኛ ነን ባንጎላችን ያሰመርነው። እዋእ ጠባብ ትምክህተኛ የሚለው በራሳችን ባንጎላችን በመካከላቸው መስመር ስላሰመርን እንጅ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ይህ አይደለም ዋናው ጉዳይ። ዋናው ጉዳይ የሁለቱ ፍላጎት ላይ ነው። ፍላጎቱ ምንድነው የሚለው ነው ዋናው። ከፖለቲካዊ ጀርባቸው አዝለውት ያለው motive ወይ ገፊው ሃይል የምንለው እስሱ ምንድነው የሚለው ነው ወሳኙ። የህዝብና የአገር ጥቅም ነው ወይስ ወይስ ስልጣን ትቆጣጥረህ ገዢ መሆን ነው?

ጋዜጠኛ (ወንዱ):

የእኔ ጥያቄ ያ ገፊ ሃይሉ ወይ ፍላጎቱ ነው የተቀየረው ወይስ ሌላ የሚለው ነው? አሁን እነዚህ የስልጣን የተለያዩ መንገዶች ናቸው ማለት ነው?

ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ:

መቆጣተር የስልጣን እድል ካጋጠመው ያ እገነጠላለሁ ሲል የነበረውም ሃይል እዋእ ያቺ ገንጥሎ ሊገዛት ያሰባት አገር ሰፋ ብትልለትኮ ነው ደስ የሚለው። አሁንም ያንን ጠባብ የምትለውኮ ለምስ ሳሌ የ አማራ ብሄርተኛ ነኝ ብሎ የተነሳው ሃይልኮ እጅና እግሩን በደምብ እንዲዘረጋ እስከ ራያ እስከ ማን ነበር የሚባለው? እስከ ተከዘ ድረስ እነዝህን ግዛቶቼ ናቸው እያለኮ ነው ያለው። እና ዋናው ገፊው ፍላጎታቸው ስልጣንን ተቆጣጠረው የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት ብያገኙ ሁለቱም አይጠሉም የሚለው ነው። አሁን ወደ ትምክህት የተቀየሩት ኦሮሞን የመገንጠል አላማ የነበራቸው ሃይሎች ኢትዮጵያዊ ነን ብለው አምነው በኢትዮጵያዊ ስልጣን ካገኙ እነዝያ ከትምክህት ወደ ጠባብነት የገቡት የአማራ ብሄርተኛ ሃይሎች ደግሞ እጅና እግራቸው መዘርጊያ ካገኙ ሁለቱ በአገሪቱ በትዳር የማይኖሩበት ምንም ምክንያት የለም። ይህ ነው ለእኛ አደገኛውና ዘግናኝ ክስተት የሚያደርገው። ስለዝህ በሁለቱ መካከል ድንበር የለም ማለት ነው። ሊያስቆጨንና ሊያታግለን እንጅ ሊያስገርመን አይገባም ማለት ነው።
ጋዜጠኛ (ወንዱ): እሽ የእኛ ሃይል የት ነው ያለው? እስኪ የእኛ ሃይል የት እንዳለ በዝርዝር እኘው?
ጋዜጠኛ (ሴቱዋ): ይህ የትግራይ ሃይል በይትኛው ሰልፍ በኩል ነው ያለው? ጠባብም ይሁን ትምክህተኛ አሁን የትግራይ ሃይል በየትኛው ሜዳ ላይ የቆመው?

ጋዜጠኛ (ወንዱ):

የእንየ ጥያቄ ትግራይን ሊወክለን የሚችል የኢሊት ቡድን አለን ወይ ነው?

ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ:

Anyway አሁን ይህ ጠባብና ትምክህተኛ የሚለው ድሮ ነበር የሚባለው። እኔ አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ጠባብና ትምክህተኛ በማለት ልንገልጠው አይገባም ነው የምለው። ስለዝህ ጥገኛ ሃይል በማለት ልንገልጠው እንችላለን። ጥገኛ ሃይል። ማለት ጥገኛ የሚለው ብዙ ትንተና የለውምና ከነዝ ህ ሃይሎች ውስጥ ሃይማኖትም አድርጎ ወደ ስልጣን ሊመጣ የምፈልግም ይኖራል። በውስጣቸው ለምስሳሌ በኦሮሞዎቹ ውስጥ እንደሰማናቸው የመጀመሪያ አጀንዳቸው የነበረችው ወደ ስልጣን እንዳንወጣ ችግር የሆነብን ሃይል ማንነው የሚል ነበር። ህገ መንግስትዋን ይዞ ወደ ስልጣን እንዳንወጣ የምያስቸግረን ሃይል ማንነው ብለው ሁሉም ጠላታቸውን መለየት ችለዋል። እነስሱ መለየት ችለው የምያስቸግረን ወያኔ ብለው ለዩ። ከዝያ ለወያኔ ምን የሚል ስም እንስጠው ተባብለው የትግራይ የበላይነት የሚባል መጠሪያ ቃል ሰጡን። ከዝያ የትግራይ የበላይነት በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብለው ፅፈው መተረክ ጀመሩ። ይህንን ትርካ መሰረት አድርገው እየሰሩ ቆዩ። ጠባብም ትምክህተኛ የሚባል ሳይኖርሁሉም ናቸው እዝህ ላይ የሰሩት። ዋና አላማቸው ደግሞ ከቻሉ አገሪቱን ተቆጣጥረው ሰጥ ለጥ አድርገው እንደፈለጉት የሚገዙበት ሁኔታ መፍጠር ነው። ስለዝህ እንደዚህ በጋራ እየሰሩ መጥተው ኢህአዴግ ደግሞ የትግራይ የበላይነት አለ የለም ብሎ በውስጥ አጀንዳ አድርገው ተከራከሩ። ኢህአዴግ እራስሱ እዝህ አጀንዳ ውስጥ ገባ። ይህ አሳፋሪ ነው። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚባሉት ወደዝህ አጀንዳ ገቡ። ይህ አሳፋሪ ነው። የእኛው ህወሓት ደግሞ የለም ብሎ እየተከራከረ ረጅም ግዜ ወሰደ። አለ ወይስ የለም ተብሎ የማንተማመን ከሆነ እማ እስኪ እን ይና ህንፃዎችን እንቁጠራቸው ተብሎ ህንፃዎችም ተቆጥረዋል። ይህ አሳፋሪ ነው። በትግራይ ህዝብ ትግል በጣም የሚያሳፍረኝ ነገር ብኖር ይህ ነው። በመጀመሪያ ያለውን ሁኔታ ባህርይ ነበር መረዳት የሚያስፈልገው። አለ የለም ብለህ ወደ ክርክር ከገባህ አጀንዳቸውን እንደራስህ አድርገህ ወሰድክ ማለት ነው። እንዲህ እየተባለ ተመጣ። ስለዝህ ይቺን መነሻ አድርገው ለግዘው የልባቸውን ሰርተዋል። እንግድህ ይህ ቡድን ስልጣኑን እያደላደለ ነው። ትንሽ ካደላልደለ ብሁዋላ ደግሞ እንዝያ እስላሞች ደግሞ ሊነሱ ነው። እነስሱ የራሳቸው አጀናዳ አላቸው። አገሪቱ በሸሪአ ህግ ነው መገዛት ያለባት የሚል አጀንዳ አላቸው። እስሱ ደግሞ ተነስቶ ጦርነት ሊያውጅ ነው። ችግር ሊያውጅ ነው ማለት ነው። ስለዝህ መንገዱ ስለተሳተ መጨረሻ ወደሌለው ችግር መግባት ነው የሚሆነው ማለት ነው። አሁን የምናየው የቀደመው ብቻ ነው። ከሁዋላው ሌሎች የተቀመጡ አጀንዳዎች አሉት። ስለዝህ የሚሉት ኦሮሞ ብዙ ስለሆነ አማራ ብዙ ስለሆነ እነዝህ የማይገዟት በትንንሽ ብሄሮች አንገዛም የሚል አቁዋም ነው ያላቸው። ወያኔያዊው መስመሩን ስተውታል ማለት ነው። ይህ አመለካከታቸው ግን ፀረ ህዝብ ነው። ፀረ ህዝብ ሁነዋል ማለት ነው። ከዝያ ደግሞ ሌላ ትርክት አመጡ። ተጋሩዎች ሌቦች ናቸው አሉ። ለህወሓት የቀን ጅብ የሚል ስም ሰጡዋት። የህወሓት መሪዎች ናዚዝስቶች ናቸው የሚል አጀንዳም አምጥተዋል። እንዲህ እያሉ ወደ ፋሽስትነት እየተቀየሩ ነው ያሉት። ይህ የሚያደርጉት ህወሓትን አዳክመው የትግራይ ህዝብ ለመምታት ነው። ግን አይሳካላቸውም። የትግራይ ህዝብ ግን ጥቅሙን የሚያውቅ የነቃ ህዝብ ነው። እንደኔ እምነት የትግራይ ህዝብ በቦታው ነው ያለው። ህወሓት ማለት ልጆችውንና እራሱን የሰዋባት ነው። እየመጣ ያለውን አደጋም ገብቶታል። ግን አሁን በትግራይ ያለው ሁኔታ አሁን ምን ይመስላል። አንተ እንዳልከው በየቦታው በኢሊቱ ውይይቶች አሉ። እነዝ ህ የተላያዩ ውይይቶች ግን ምንድነው የሚፈጥሩት የሚለውን ለመተንበይ ግን አስቸጋሪ ነው። ዙሮ ዙሮ ግን ኢሊቱ ከህዝባችን የወጣ ስለሆነ በህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ልይነት የላቸውም። በኢሊቱም በገበሬዎም ያለው ሓቅ ይህ ነው ብለህ ልትወስደው ትችላለህ። ግን የሁኔታው ግልፅ አለመሆን ደግሞ አለ። የግልፅነት ችግር አለ። ከዝህ ተነስተን ደግሞ ባስቸኳይ ማድረግ ያለብን ምንድነው የሚለው ላይ ደግሞ ትንሽ የመጨለም ሁኔታ አለ። ስለዝህ እነዝ ህን ገለጥ ብታደርጋቸው ግልፅነት ከተፈጠረ ወዴት ነው የምንሄዴው እንዴት ነው የምንሄዴው የሚለውን በራሱ ይገልጥልናል። ማእበሉ በራስሱ የሚመልሰው ነው የሚሆነው። ማእበሉ በራሱ መልስ ይሰጣል። ስለዝህ አሁን ያሉት ሁኔታዎች ይህን ይመስላሉ።

=====================================

የናዚዝስቱና ፋሽስቱ ጀነራል ዶ/ር እምቡር ትጋዳላይ ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ከጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጋር ስነበረው ከፍተኛ የቆየ ግጭትና የፖለቲካ፣ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይን ውጣ ብሎ ከኢንሳ እንዳባረረውና ጠቅላዩ ስላደረገው ተጋድሎ፣ ጠቅላዩ ምን ያህል ቆራጥ የቁርጥ ቀን ሰው እንደሆነ ከናዚስቱ አፍ ለትግራይ ህዝብ በድምፀ ወያኔ የተላለፈውን ቀጥሎ ይቀርባል። ጠቅላዩ ግን ቆራጥነቱ ይገርማል። ይህ መረጃ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መድረስ አለበት በልዩ ደግሞ ለጠቅላዩ መንግስት ለራሱ ይድረስ። ካለው ውስብስብ የአገራችን ፖለቲካ ሁኔታ አንፃር እኔ በግሌ ጠቅላዩ የወያኔ ተላላኪ ነው ብየ አስብ ነበር። አሁን ግን ክብር ለጠቅላዩ ይገባል። ጠቅላዩን ሳሳሁለት። ባጭሩ ጠቅላዩ የፈጣሪ ስጦት ነው ለማለት ተገድጃለሁ። ዳይ በሉ ወደ ንባቡ አምሩ። ይገርማል።

ጋዜጠኛ (ሴቱዋ):

አሁን ችግር እንዳለ ተግባብተናል። ስለዝህ ምን እናድርግ? ማን ምንስ ያድርግ? ህዝብ እንዴት ይንቃ? እንዴት ይቀስቀስ? እንዴት ነው የቁርጥ ትግሎቻችንን አቅጣጫዎች እየለየ የሚያሳማራን? ማን ነውስ እነዝህን የትግል አቅጣጫዎች የሚነድፍልን? እነዝህን ጥያቄዎች ብሁዋላ ትመልሳቸዋለህ። አሁን ግን ቅድምም ስንነካካው ነበርን አሁን ካለው አዲስ የአገሪቱ አመራር ዶ/ር አብይ ጋር በተያያዘ በፌደራል ደረጃ ዶ/ር አብይ በኢንሳ ውስጥ እያለ አንተ አለቃው ነበርክ። የግልህ ሚስጥር ጉዳይ እንደሆነ ይገባኛል ግን ሁሉም በግልፅ ማውራት አለብን። አንተ አለቃው እያለህ ተቀያይማችሁ ስለነበር አሁን ዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስተር ሲሆን እሱ አንተን ቀድሞ እንዳያባርርህ ነው አንተ ከኢንሳ ቀድመህ የወጣህ የሚባል ወሬ አለ። ማለት አንተ አለቃው እያለህ አስቀይመህው ስለነበር እንዲሚያባርርህ አውቀህ ነው እሱ እንዳይቀድምህ ቀድመህ የለቀቅከው የሚባል ነገር አለ። ስለዝህ በኢንሳ ውስጥ አለቃና ሰራተኛ ሁናችሁ ከዶ/ር አብይ ጋር የነበራችሁ ግንኝነት ምን ይመስል ነበር። እስኪ ስለዝህ ንገረን? በአቅም ደረጃ ከፍተኛ አቅም እያለህ ገና ወጣት እያለህ የስራ እድሜህ ገና እያለ ለምንስ አንተ ቀድመህ መልቀቂያ ጠየክ? ስለዝህ ተሎ መልቀቂያ ለመጠየቅ የገፋፋህ ሁኔታ የሚወራው ነገር ነው ውይስ ሌላ የተለየ ምክንያት አለ? ፍቃደኛ ከሆንክ ግንኝነታችሁስ ምን ይመስል ነበር የሚለውም ብትብራራልን?

ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ:

ባጭሩ ከአብይ ጋር የግል ፀብ የለንም። ሰው እንደዝያ ሊያስብ ይችላል። አብይ ከእኔ ጋር ነበር የነበረው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም የእኛ ኦፕሬተር ነው የነበረው። ከዝያ ደግሞ ኢንሳን ስናቁዋቁም ደግሞ ማቁዋቁዋሙ ላይ አብሮን ነበር። ከዝያ በመሃልም ሃላፊነት ነበረው። በሃልፊነቱም እየሰራ ቆይቱዋል። ካነሳሽው ጉዳይ በተያያዘ ከእኔ ስር ሁኖ እኔ አለቃው ሁኜ እየሰራ ቆይቱዋል። ስለዝህ የግል የሆነ ፀብ የለብንም። ግን እንዴአስተሳሰብ ባህርይ መጠን የአብይ አስተሳሰብና ባህርይ ለተቁዋማችን ስራዎች የሚጎዳ ስለነበር በመጨረሻ ከእኛ ጋር መቀጠል አልቻለም። ከስራው ውጣ አልነው ወጣ። ከወጣ ብሁዋላ ድርጅቱ ምንም አይነት ስጋት የለውም ማለት ነው። ከድርጅቱ ጋር ፍቺ ፈፀመ ማለት ነው። ስለዝህ ችግሩ የግል ችግር ሳይሆን አብይ ከድርጅታችን ተልእኮ ጋር የማይጣጣም ባህርይ ስለነበረው ነው። ከዝያን ግዜ አንስቶ ከእስሱ ጋር ተለያይተናል። አብይ ወጥትዋል። አብይ ስለሚጎዳን እንዲወጣ አደረግነው ማለት ነው። አሁን እኔ ከኢንሳ መልቀቄን እንድወስን ያደረገኝ የአብይ ወደ ስልጣን መምጣትና አለመምጣት አይደለም። አብይኮ ግለሰብ ነው። ስርአቱ ጤነኛ ሁኖ ግለሰቡ በሽተኛ ቂመኛ ቢሆን ችግር የለውም ነበር። ስርአቱ ስላለ በሽተኛ ሁኖ ቢያጠቃሽ በህግ ልትጠይቂው ትቺያለሽ። ፖለቲካዊ ጥቃት ከሆነም በፖለቲካዊ ትግል መግጠም ነው። ስለዝህ የእኔ መልቀቅ ከአብይ ጋር አይገናኝም። ትግሉን ከአብይ ከግለሰቡ ባህርይ ጋር ማያያዝም እኛን ትክክለኛ የትግል ስልትና አቅጣጫ እንዳናደርግ ስለሚገፋን ይህ አደገኛ አስተሳሰብ ነው። የስርአቱ መሸርሸር ከጀመረ ረጅም ሁኖታል። ስንከታተለውም ስንነጋገርበትም የነበረ ነገር ነው። እኛ ጀነራሎች ብንሆንም በስርአቱ መሸርሸር ጉዳይ ከሁሉም ባለስልጣናት ጋር በቅርበት ስንወያይበት የነበር ነው። ስርአታችን እየተበዘረዘ ነው ብለን ስንነግራቸው ነበር። ለምስሳሌ FDI ማለት foreign investment ነው። FDI መሰረት ያደረገ የኢንዳስትሪ እድገት አቅጣጫ ካሁን በፊት ለነበረው እርሻ መሰረት ያደረገ እድገትን የሚፃረር መሆኑ በGTP 2 በፅሁፍ በግልፅ ተቀምጥዋል። በሚቀጥሉት አምስት አመታት ያገር ውስጥ ባለሃብቶች አቅም ስለማይፈጥር የውጭ ባለሃብቶች FDI ለመሳብ ነው ትኩረት ሰጥተን መስራት ያለብን ተባለ። ይህ ከዝያ በፊት ለነበረው ፖሊሲያችን ፍፁም የሚፃረር ነው። በዝህ ተፃራሪ ሃሳብ ተወያይተንበታል። እኛ ጀነራሎች የፖለቲካ ፓርቲ አባል ስላልሆን ፖለቲካዊ መድረክ ባይኖረንም በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋርም በደምብ ተወያይተንበታል። በግልፅ አስተካክሉት ብለን ነግረነዋ። እሱም የቃላት አፃፃፍ ምናምን ነው እንጅ ችግር የለውም ሲለን እኛም በግልፅ ትእዛዝ የቃላት ይሁን የአፃፃፍ በተሎ አስተካክሉት ብለን ነግረነዋል። እኛ ግን ማለት እኔ በግሌ በወቅቱ ስቃወምበት የነበረው ምክንያት ስርአቱን የመሸርሸር ስራ በተግባርም እየተሰራ ስለነበር ነው። በተግባር ባገር ውስጥ ጥሩ ስራ እየሰሩ የነበሩ የግል ባለሃቦቶችም የተለያዩ አቅም ያላቸው ድርጅቶችም ስለነበሩ እነዝህን የሚያንቋሽሽ ያለንም ሁሉ ሃብት በኢንዳስትሪ ፓርክ ብቻ እንዲውል የሚያስገድድ ሁኔታ ስለነበር ነው። በዝያ ላይ የኢንዳስትሪ ፓርኮች ቢሰሩም ካገር ውስጥ የሚያገኙት አቅርቦት የለም። የኢንዳስትሪ ፓርኮቹ ቢሰሩም ከ አገሪቱ የሚገኝ ምንም አቅርቦት የላቸውም። ለምስሳሌ ጨርቅ የሚሰፉ ኢንዳስትሪዎች ጨርቅ ከውጭ ነው የሚመጣው። ጥጥም እንደዛ ከውጭ ነው። ምንም አቅርቦት የለም። ከእርሻ ኢንዳስትሪው ጋር የተያያዘ አይደለም። FDI ያስፈልገናል ግን የሚያስፈልገን እርሻን መሰረት ያደረገ የኢንዳስትሪ እድገት የሚባለው ፖሊስያችን ጋር መተሳሰር ያስፈልገናል። ስለዝህ ገበሬ ሊገነቡ የታሰቡን ፓርኮች በቂ አቅርቦት ሊያደርግበት የሚችል የእርሻ አቅም መፍጠር ይቅደም ከዝያ ደግሞ የውጭ ባለሃብት ደግሞ ይግባ ነበር ያልነው። ስለዝህ አንዱ መሰረታዊ ችግር የነበረው የዝህ ከኢኮኖሚያዊ ፖሊሳችን ጋር የተያያዘ ነበር።ይህ ስናደርገው የነበረ ኢኮኖሚያዊ ትግላችን ነበር። ሌሎች በቅርብ የምንከታተላቸው ጉዳዮች ነበር በጥልቅ ተሃድሶውም ወቅትም ክህደት ነው የሚል አቁዋም ነበር የነበረን። ጥልቅ ተሃድሶ አይደለም ስርአት ነው እየፈረሰ ያለው። ስለዝህ በስርአት መፍረስ ደረጃ ያለ ችግር ነው ተብሎ ሊታይ ይገባል የሚል ሃሳብ ነበረን። ይህን ትእዛዝም ሰጥተን ነበር። Anyway የችግሩ እድገት በቅርበት ስንከታተለው ነበርን ለ ማለት ነው። ስለዝህ ይህ የስርአቱ መበስበስ ባጭር ጊዜ የመጣ አልነበረም። ከዝያ የመጨረሻ ችግር ግን አሁን የመጣው ሁኔታ ነው ያለው። ኢህአዴግ የሚባለውም ቀደም ብየ እንደገለፅኩት እራሱን በልቶ እንደጨረሰ ተረድተን ጥለን ወጣን። እኔና ጀነራል ክንፈ ዳኘው ስ ህተታችንን ገምግመናል። እኔና ክንፈ መልቀቂያ ለማስገባት ስንወስን በርግጥ ተነጋግረን አልወሰንም ግን እኔ እራሴን ገምግሜ ነው የወሰንኩት። እሱም እንደዛ ነው ያደረገው። ስለዝህ አንድትም ቀን ትሁን ለስርአቱ የማይጠቅም ለህዝብ የማይጠቅም ሁኔታ ላይ መቆየት የለብንም ብለን ነው ወስነን የለቀቅነው። የምንቆይበት ትርጉም አጥተን ነው የለቀቅነው ማለት ነው። የምትቆይበት cause ካጣሽ ትለቂያለሽ እንጅ አብይ ሊያጠቃኝ የሚል ፍርሃት ስጋት የለም። የነበረው ሁኔታ እንዳውም በአንፃሩ ነው የነበረው። የነበረው ሁኔታ አንቺ ካነሳሽው ወሬ ተቃራኒ ነው የነበረው። እኔን ማጥቃት ሳይሆን ለእኔ ሌላ ሃልፊነት የመስጠት ዝግጅት ነበረ የነበረው። I know that ስለዝህ የአላማ የcause ጉዳይ ነው። የታገልነበት አላማ በጥያቄ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ሲፈጠር ቆም ብለን እንድናስብ የሚያስገድድ ሁኔታ ስለነበር ነው።

ጋዜጠኛ (ወንዱ):

አሁን እነዛ ያሉንን እድሎች እስኪ እንያቸው? በዝህም አለ በዝያ የለውጥ ሁኔታዎች ተጀምርዋል። ኢህ አዴግ ያዋታል ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ጀምርዋል። በክልላችን ንቁ የሚባሉት ኢሊቶች በዝህ በድምፀ ወያነ ሬድዮ አሁን እንደምናደርገው ውይይቶች ሲያደርጉ በዝህ ክልል እየታዩ ያሉ አንዳንድ የክፍተት ሁኔታዎች አሉ። ብዙ ምሁራን ከነዝህ ክፍተቶች ገሚሶችም ጠልፈው ሊጥሉን የሚችሉ አደገኛ ክፍተቶች ናቸው ሲሉ ይደመጣሉ። አሁን ባለንበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሊኖሩን የሚችሉ መልካም እድሎችን እስኪ በዝርዝር እናስቀምጣቸው? ለምስ ሳሌ በህወሓት መጀመር እንቻላለን። ትግራይ ያሉዋትን የምሁራን እድል ማየት እንቻላለን። ትግራይ አሁን ያላትን የተላያዩ ፀጋዎችም ማየት እንችላለን። የእናንተ ወደ ትግራይ የመምጣትም አለ። እናንተ ምን እየሰራችሁ ነው የሚለው ብሁዋላ የናወራበት ጉዳይ ነው። አሁን ያለንበትን ሁኔታ ወደ መልካም ፀጋ ለመቀየር የሚያስችሉን ምን ምን መልካም አጋጠሚዎች አሉን?

ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: ክፍል 4 ይቀጥላል…

ሊንክ ፡ https://youtu.be/F7MgpzvrSK0

Filed in: Amharic