>
5:13 pm - Sunday April 19, 3964

የኢንሳ ም/ዳይሬክተር  ቢኒያም ተወልደ በቁጥጥር ስር ዋለ!!!

የኢንሳ ም/ዳይሬክተር  ቢኒያም ተወልደ በቁጥጥር ስር ዋለ!!!
ፋሲል የኔአለም

ባለፈው ሳምንት “ከግድያው ሙከራው ጀርባ” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሁፍ ውስጥ “ በአገሪቱ ውስጥ ለሚነሱ ግጭቶችም ሆነ በጠ/ሚኒስትሩ ላይ ለሚደረጉ የግድያ ሙከራዎች እቅዶች የሚዘጋጁት መቀሌ ነው። እቅዱን ደግሞ በበላይነት የሚነድፉት እና የሚያስተባብሩት የቀድሞው የኢንሳ ዳይሬክተር ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወልዳረጋይና ምክትሉ ቢኒያም ተወልደ ነው” በማለቴ፣ በተለይ የቢኒያምን ስም በመጥቀሴ አንዳንዶች “ቢኒያም እኮ የአብይ ጓደኛ ነው፣ ተሳስተሃል” እያሉ  በውስጥ መስመር ጽፈውልኝ ነበር። ( ከጽሁፉ ስር ያሉትን አስተያየቶችም መመልከት ይቻላል።) ለእነዚህ ሰዎች በጊዜው የሰጠሁዋቸው መልስ፣ “  ሰዎቹ ተይዘው ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ አድርጎ ነጻ ካላቸው በይፋ ይቅርታ ልጠይቃቸው ዝግጁ ነኝ፤ ለማንኛውም ግን ከትንሽ ቀን በሁዋላ አብረን እናያለን።” የሚል ነበር።  ቢንያም ተወልደ ትናንት መታሰሩንና የመኖሪያ ቤቱ መበርበሩን ዛሬ ሰማሁ።  ለማንኛውም ቢኒያምንም ለማታውቁ ፎቶውን ይህ ነው። አንደኛው የሴራ ማእከል ከተደረሰበት በሁዋላ ሊጠፋ ተቃርቧል። ሌላኛው ማእከል ደግሞ አሁንም አልተደረሰብኝም ብሎ ሴራውን እየጎነጎነ ነው። ለማንኛውም አረናዎች ሳይቀር የተሽ ከረከሩባት የክንፈ ዳኘው መኪና ብዙ ሚስጢሮችን ይዛለችና አሁንም ቶሎ ተይዛ ምርምራ ይካሄድባት።

ጀኔራል ተክለብርሃን ተክለአረጋይም የእስር ዋራንት እንደወጣበት እየተነገረ ነው 
ሰሞኑን ቅሊንጦ መግባቱ አይቀርም። በአቢይ የግዲያ ሙከራ አረናዎችም እጃቸው አለበት እየተባለ ነው። እነ አብርሃ ደስታ ሰሞኑን አለነገር አላንቀዤቀዣቸውም።
የሆነ ሆኖ እነዚህ ተጠርጣሪዎች እድለኞች ናቸው። አሁን ቃልቲና ቅሊንጦ በሀይላንድ ውሃ እየሞላ ብልት ላይ የሚያንጠለጥል፣ ጥፍር በጉጠት የሚነቅልና ዘቅዝቆ የሚገርፍ መርማሪ ስለሌለ ለውጡ እነሱንም እየጠቀመ ነው።
Filed in: Amharic