>

ካድሬው አሉላ ሰለሞን ዶ/ር አብይን ከሚቀበለው ኮሚቴ ውስጥ ይውጣላን!!!  (ሰላም ለሀገሬ)

ካድሬው አሉላ ሰለሞን ዶ/ር አብይን ከሚቀበለው ኮሚቴ ውስጥ ይውጣላን!!! 
ሰላም ለሀገሬ
ዶክተር አብይ ወደ ሃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት ጀምሮ እሳቸውን በማጥላላት፣ በመዝለፍ፣ እና በከፍተኛ ጥላቻ ስማቸውን ሲያጠፋ የቆየው የህወሓት ካድሬ በአሜሪካ የትግራይ ነዋሪዎች ፕሬዝደንት አይኑን በጨው አጥቦ ዶክተር አብይ በአሜሪካ ለሚያደርገው ጉብግኝት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ሆኖ በመድረክ ላይ ታይቷል።
  በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ካሳ ተክለብርሃንም የሚገኝ ሲሆን አሉላንም ወደ ኮሚቴው በማምጣት የሱ ሚና  ምን ሊሆን እንደሚችል ልብ ይበሉ። በመሆኑም በዶክተር አብይ ላይ የከረረ ጥላቻ ያለው መሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህንንም በተደጋጋሚ በአደባባይ ሲገልጽ የቆየና በመስቀል አደባባዩ የግድያ ሙከራ ዋዜማ ይሄ ሊፈጠር እንደሚችል ሟርት እና ማስፈራሪያ ጽፎ የነበረው አሉላ ሰለሞን ለዶክተር አብይ ደህንነት ሲባል ከዚህ ኮሚቴ ውስጥ እንዲወጣ ሁላችንም ማሳሰብ አለብን። ዶክተር አብይን የማግኘት እድል ካለው ምን ማድረግ እንደሚሞክር ከማንም የተሰወረ አይደለም። አሉላ ሰለሞን በአደባባይ ጥላቻውን ከገለጸባቸው ጽሁፎች የሚከተሉት ይገኙበታል
• በሰላም፣ በይቅርታ፣ አንድ እንሁን ብሎ ዶክተር አብይን ለመደገፍ የወጣውን የኢትዮጵያን ህዝብ በጅምላ  ከአንገት በላይ፣ የውሸት በሆነ አንድነት የኋለኛው ጥርሱ እስኪታይ የሚገለፍጥ ብሎ በ አደባባይ የተሳደበ
• የ ኢትዮጵያ አንድነት አስፈላጊ ነው መከፋፈል ያጠፋናል ያሉትን  ኢትዮጵያውያን የግዛት  አንድነት ናፋቂዎች በማለት ህልማችሁ ላይመለስ ተቀብሯል በማለት የጻፈ
• የአማራና የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ ‘መንጋው’ በማለት ቁጥራችሁ ብዙ ስለሆነ ምንም አታመጡም የህወሓትን የበላይነት ከማስቀጠል ልታቆሙን አትችሉም በማለት የጻፈ
• በትግራይ ዶክተር አብይን የሚቃወም ሰልፍ እንዲጠራ ያስተባበረ በዚሁም ሰልፍ የዶክተር አብይ ፎቶ እንዳይያዝ ያሳሰበ
• የዶክተር አብይን ንግግር ሃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው ያለ
• ይህቺ qerro በቀናቶች ውስጥ 11 ፋብሪካ አቃጥላ 60ሺህ ቤተሰቦቿን ሥራ አልባ በማድረግ ጎዳና ላይ በትና። አለቃዋ ከአሜሪካ በሚሰጣት ስሜት ቀስቃሽ ፕሮፖጋንዳ እየነጎደች ክልሉን ወደ stone age ልትመልሰው ነው?  በማለት የጻፈ Oct 7 2016
• ሰሞኑን ደግሞ ከጃዋር ጋር ተነጋግረን በትግራይ ጉኝት እንዲያደርግ ጋብዤው ግብዣውን ተቀብሎኛል ይለናል
• በስተመጨረሻ ዶክተር አብይን እቀበላለሁ ሲለን  ፈጣሪ ለሰጠን ለዶክተር አብይ ደህንነት ሲባል ጥንቃቄ እንዲደረግ እንመክራለን።
አሉላ ሰለሞንን በሚመለከት በዚህ ጽሁፍ ስለተካተቱት ጉዳዮች ተጨማሪ ማብራሪያ እና ማስረጃ ካስፈለገዎት ሁሉም በእጃችን የሚገኙ በመሆናቸው በደስታ እናካፍልዎታለን።
መደመር እና ይቅርታ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ!
የናንተው ኢትዮጵያዊ ልጅ!
Filed in: Amharic