>
5:33 pm - Thursday December 5, 5669

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የወነጀለኞች መሸሸጊያ መሆን የለበትም!! (ከድር እንድሪስ)

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የወነጀለኞች መሸሸጊያ መሆን የለበትም!!
 
የጀኔራል #ክንፈዳኘ ፤ ሜ/ጀኔራል #ተክለብረሀንወልደአረጋይ አና ኮ/ል #ቢኒያም ከበደ ሚስጢር
 
የ #ኢንሳ አና #ሚቲከ ሚስጢር
ከድር እንድሪስ
 ( ምርመራ ላይ ካለው ፋይል የተገኘ) 
የሰዎቹ ክስ (የተክለብራሀንና የቀኝ እጁ ቢኒያም) አብይን ለመግደል ከማሴር በፊት ከበባድ ዘረፋ ላይ የነበሩ ናቸው ::  ኢንሳን ልክ እንደሜቴክ (በነገራችን ላይ ክንፈ አና ተክለብረሀን በጣም የቅርብ ወዳጆች ናቸው መልቀቂያ ያስገቡት ራሱ አንድ ላይ ነው በዚየ ወቅት ቀኑን ሙሉ አንድላይ ሲፈትሉ ነበረ ሚውሉት የሚያድሩት) አገር ማራቆቻ አርገውት ሲጠቀሙበት ነበር፡፡
የፌዴራል መስሪያ ቤት የሆነው ኢንሳ አመራር 70 ከመቶ ከፍተኛ አመራሩ ከአነድ ብሐር ሲሆኑ እሱም ከትግራይ ነው፣ የመካከለኛ አመራሩ 50 % ከትግራይ ነው ፣ 50 እክስፐርት ከትግራይ  ነው  :: ለዚህ ምክንያት ተክለብራሀን እና ምክትሉ ቢኒያም ከበደ ሆን ብለው መቀሌ ቴከኖሎጂ ኢኒስቲቱትና የሚመጡ ብቻ ያለምንም ውድድር በገፍ እንዲቀጠሩ ሲያደርጉ ነበር ::
የኢንፎረሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ቴሪስቴሪያል ቴሌቪዥን ስርጭት የተሳካ ሽግግር ለማከናወን ፕሮጀክት በመቅረፅ ፣  የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ምዕራፎች እና ንዑስ ክፍሎች በመለየት፣ የፕሮጀክት አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ስታንዳርድ መረጣ እና የዲዛይን ፍላጎት፣ የፕሮጀክቱ መስተጋብር ፍኖተ ካርታ /ሮድማፕ/ እና የጊዜ መርሃ ግብር ያካተተ አጠቃላይ ፕሮጀክት ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ 1,392,520,000.00 ብር በጀት በማስፈቀድ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የዲጂታል ቴሌቭዥን ፕሮጀክት በመስራት ጀምሮ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በዕቅዱ መሰረት በ2009 ሙሉ በሙሉ ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ ለመንግስትና ለህዝብ ቃል የተገባ ቢሆንም እስከ አሁን የተሰራው ሥራ ግልፅነት የጎደለውና የመንግስትና የህዝብን ሃብት ለተፈለገበት ዓላማ ሳይውል እየባከነ ይገኛል፡፡
በዕቅዱ መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን አድማሳዊ የቴሌቭዥን ስርጭት ሽፋን ለማስፋት ተጨማሪ 26 አዳዲስ እና ሙሉ የዲቪቢ-ቲ2 ትራንስሚተሮች በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች በማቋቋም የስርጭት ተደራሽነት ማስፋፋት፣ ብሔራዊ ማቀነባበሪያ ሄድ ኢንድ መሳሪያ ለመትከልና ለዚህም ሥራ የሚያስፈልግ መሰረተ ልማትና ግንበታ ማጠናቀቅ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ  አንድም የማሰራጫ ጣቢያ ሲስተም ተከላ ስራ አልተከናወነም፡፡ ለዲጂታላይዜሽኑ ብሔራዊ ማቀነባበሪያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሄድ ኢንድ/  የግንባታ ሥራ በኮንትራክተሩ እና በፕሮጀክት ክትትል የአፈፃፀም ጉድለት ምክንያት በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ስራው እንዲቋረጥ አማካሪው ድርጅቱባቀረበው የውሳኔ ኃሳብ መሰረት እንዲቋረጥ ተደርጓል፡
ይህን ሥራ ያለ ዕውቀትና ልምድ በመረከብ በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ አካሄድ የተፈፀመው በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አመራርነት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ተግባር ደግሞ ህዝብና መንግስትን ለመጥቀም ታስቦ የተፈፀመ ሳይሆን በግዥ ሂደት ያሉ ጥቅሞችን ለማሳደድ የታለመ ተግባር መሆኑን ከፕሮጀክት አፈፃፀሙ ሂደት መረዳት ይቻላል፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ኤጀንሲው ሚዲያን የማስተዳደር ፣ የመገንባትና የማሰራጨት ተልዕኮ ሳይኖረው ፕሮጀክቱን ከሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በመውሰድ ያለበቂ ልምድና ዕውቀት በመግባቱ በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሷል፡፡
(simulcast) ሲያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ቀስበቀስ በማቋረጥ ዲጂታል ስርጭትን ማስቀጠል መቻል በሚል በየዓመቱ ኤጀንሲው ለአራት ዓመታት የመንግስት በጀት እያስፈቀድ ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡
ፐሮጀክቱ ማለቅ የነበረበት በ2009 ሲሆን እነተክለ ብራን በፕሮጀክቱ ምክንያት የወሰዱት 1.3 ቢሊዮን ብር ወቶ አልቃል መሬት  ላይ ምንም የተሰራ ነገር የለም የለም ይላል ርፖርቱ ። ይሐም 1.3 ቢሊየን ብር የቀለጠ ነዉ ማለት ነው ።
ኢትዮሳት የሳተላይት ፕላትፎርም ፕሮጀክት ኤጀንሲው ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ ብሔራዊ የተቀናጀ የዲጂታል ሳተላይት ቴሌቭዥን ኘላትፎርም አቀርባለሁ በሚል የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ከ #ዩተልሳት እና #ኤስኢኤስ ከተባሉ የውጭ ኩባንያዎች የሳተላይት ባንድ ዊድዝ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በመከራየት የመንግስትና የግል ሚዲያዎች በዚህ የኪራይ ሳተላይት  እንዲጠቀሙ በማስገደድ የውጭ ምንዛሪ አስቀራለሁ ብሎ ለመንግስትና ህዝብ የተሳሳተ መረጃ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ ይሁን እንጅ ምንም አይነት የሴኩሪቲ እሴት በተቋሙ ሳይጨመር፣ የሳተላይት ኦፕሬተሮች በግልፅ ሳይወዳደሩ፣ የውጭ ምንዛሬ ሳያስቀርና ወጪ ቆጣቢ አካሄድ ሳይከተል፣ ጥራቱን ባልጠበቀና የሚዲያ ተቋማትን ፍላጎት በማይመልስ ባንድዊድዝ እንዲጠቀሙ በማድረግ የአገልግሎት ጥራት እንዲጓደል አድርጓል፡፡ ለአብነትም እስካሁን የወጣ የመንግስት በጀት ሲታይ በጠቅላላው ለሁለቱ ኩባንያዎች 5,681,798.32 USD (5.6 ቢሊዮን የአሚሪካ ዶላር) ወይም በብር  155,349,434.29 የተከፈለ (የቀለጠ ብር) ፐሮጀክቱ አሁን ተዘግታል ።
ይህ ከፍተኛ መስጢር ነው
ሜ/ጀኔራል  #ተክለብራን ወልደአረጋይ እና ቀኝ እጁ ኮሌኔል #ቢኒያምከበደ የሚዘውሩት ኢንሳ የመንግሰት ተቓማትን አስገድዶ እንዲገቡ ባደረጋቸው #አስርቢሊዮን ብር የሚያወጣ 218 ፐሮጀክቶች ውሰጥ አንዱንም ሳያጠናቅ ሙሉ የፕሮጀክት ክፍያ ሙልጭ አድርገው በልተውታል።
የሃኪንግ ታለንት ያላቸውን የትግራይ ልጆች እናሰለጥናለን ብለው 3.5 ሚሊዮን ነው የበሉት ለህፃናት የሚሆን መዳኒት መግዣ ከልላት ሀገር ካዝና የዘረፉት ።
የሳይበር ታለንት ማናጅመንት ፕሮግራም
የዚህ ፕሮግራም ዓላማ ለተቋሙ የተልዕኮ ስኬት የሚያስፈልጉ ታለንት ያላቸው አባላትን ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከማህበረሰቡ እና ልዩ ልዩ ተቋማት በመመልመልና በማሰልጠን ወደተግባር ማስገባት ያለመ ፕሮግራም ነው፡፡ ይሁን እንጅ በፕሮግራሙ አፈፃፀም ግዥዎች ዙሪያ ያሉ ክፍተቶች የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡
1. ውሉ የተፈረመበት ቀን፡- በፈረንጆች አቆጣጠር 26 July, 2016
2. ውሉ የሚጠናቀቀው፡- በውሉመሠረት መጠናቀቅ የነበረበት ግንቦት 2010 ዓ.ም ቢሆንም ተማሪዎች ስልጠናቸውን በውጭ ሀገር አጠናቀው የሚመለሱት ገና ጥቅምት 2011 ዓ.ም መሆኑ፣
የውሉ ዋጋ ፡- 3,200,000.00 USD (  #ሶስትቢሊየንሁለትመቶሺህ የአሜሪካ ዶላር )
3. የአከፋፈሉ ሁኔታ፡- ክፍያው ኩባንያው በውሉ የተቀመጡ አስር ፌዞች በሶስት የአከፋፈል ምእራፍ ተከፋፍሎ መጠናቀቃቸውን ኢመደኤ ማረጋገጫ ሲሰጥ  የሚከፈል መሆኑ በውሉ ተቀምጧል፡፡
አሁን ያለበት ሁኔታ፡- ፕሮጀክቱ ገና በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም 100% ክፍያ ተከፍሏል፡፡ በውሉ የተቀመጡት ፌዞች ከ5 እስከ 10 ያሉት ተግባራትም እስከአሁን ያልተፈፀሙና በመፈፀም ሂደት ላይ ናቸው፡፡ በውሉ በተቀመጠው መሰረትም፡-
1ኛ ክፍያ 30% (960,000 USD) ቅድመ ክፍያ ሲሆን ኩባንያው Indirect Bank Guarantee ስያስይዝ የሚከፈል በመሆኑ በዚህም መሠረት ክፍያው ተፈፅመዋል፡፡
2ኛ ክፍያ 25% (800,000 USD) በተ/ቁ አንድ እስከ አራት የተቀመጡት እና በተራ ቁጥር አምስት የተቀመጠው በከፊል ሲጠናቀቅ የሚከፈል ሲሆን ይህም በቀን February15,2017 መጠናቀቁን በመግለፅ ክፍያው እንዲከፈል ተደርጓል::
3ኛ እና የመጨረሻው ክፍያ 45% (1,440,000.00 USD) ከ 5-10 ያሉት ተግባትና ግብዓቶች  ሲጠናቀቁ የሚከፈል ሲሆን እነዚህ ስራዎች ገና ሳይጠናቀቁ የተጠናቀቁ በማስመሰል ሁለተኛው ማረጋገጫ በተሰጠበት ተመሳሳይ ቀን February15,2017 ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለኩባንያው በመስጠት ክፍያው እንዲከፈል ተደርጓል፡፡
የሀኪንግ ክሎት ያላቸው ልጆች እንሰብስብ ብለው እንዳለ ከመቐሌ ቴክኖሎጂ የትግራይ ተወላጆችን ብቻ ለሰበሰቡበት 3.5 ሚልዮን ዶላር ከድሃው ህዝብ ወስደዋል።
ይቀጥላል……
Filed in: Amharic