>

ህወሀት እጅ አዙር የለኮሰው የሱዳን ድንበር  ዘለል ጦርነት ሚስጥር በተጨባጭ መረጃ ሲጋለጥ ..!!! (ሚኪ አምሀራ)

ከድንበሩ ባሻገር..!!!
ህወሀት እጅ አዙር የለኮሰው የሱዳን ድንበር 
ዘለል ጦርነት ሚስጥር በተጨባጭ መረጃ ሲጋለጥ ..!!!
ሚኪ አምሀራ
የሱዳን ወታደሮች በባለፉት ሶስት እና አራት አመታት ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የኢትዮጵያ ገበሬወችንና ባለሃብቶችን መሬት እያጠቁ ለማስለቀቅ ሞክረዋል፡፡ በዚህ አመት ደግሞ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ሁሌም ቢሆን ሱዳን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተረጋጋ ሁኔታ በማይኖበት ግዜ ገበሬወችን ከደንበር በማራቅ መሬቱን መዉረር ይፈልጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህወሃትና ሱዳን የተስማሙበት ዝርዝር ምን እንደሆን ባናዉቅም የበፊቱ ጠሚ አንዴ የተናገረዉ በሁለቱም በኩል ያሉ ገበሬወች የያዙትን ይዘዉ ይቀጥላሉ የሚል ነገር እንዳለበት ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ደንበር ኦፊሻሊ ከመከለሉ በፊት ሱዳኖች አግሬስቨሊ የኛን ገበሬወች እያስለቀቁ የሱዳን ባለሃብቶችን መሬቱን በፍጥነት እንዲይዙት ከላይ ከአብደራፊ እስከ ቋራ መስመር ሲሰራ ሰንብቷል፡፡ ከዛም መሬቱ በሱዳኖች የተያዘ ስለሆነ ወደ እኛ ይካለል ለማለት እንዲያመች ነዉ፡፡ በጣም የሚያበሳጨዉ በጊዚያዊ ጥቅም ምክንያት የህወሃት ኮሎኔሎች የዚህ ተባባሪ መሆናቸዉ እና አገራቸዉን ለመሸጥ መነሳታቸዉ ነዉ፡፡
 
የህወሃት ኮሎኔሎች ከሱዳኖች ጋ ያላቸዉ የጥቅም ግንኙነት
ከላይ የህወሃት ፖለቲከኞች ባብዛኛዉ ሱዳን ተቃዋሚ ሃይል እንዳትፈቅድ እና ለኤርትራም ቦታ እንዳትሰጥ ለማደርግ ነዉ የመተማን መሬት ቆርጠዉ የሰጡት፡፡ እነ አባይ ጸሃየ ባብዛኛዉ የሰጡት የእርሻ መሬት እንደ እጅ መንሻ ነዉ (ከአባይ ጋር ሁነዉ የደለሎን መሬት ሄደዉ ልክተዉ የሰጡትን ብአዴኖች ወደኋላዉ ስማቸዉንና ፎቷቸዉን ይዠላችሁ እመጣለዉ መረጃዉ እጀ ላይ አለ)፡፡ከታች የተሰማሩት ኮሎኔሎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም የህወሃት ባለሃብቶች ደግሞ በጣም ብዙ የኮንትሮባንድ ጥቅም እና ንግድ ከሱዳን ወታደሮች ጋር እጅ እና ጓንት ሁነዉ ይሰራሉ፡፡የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸዉ፡፡
የኩላሊት ንግድ
ኮሎኔሎች በጭልጋ መተማ፤ጋላባት መስመር ከሚነግዱት ንግድ አንዱ የሰዉ ኩላሊት ነዉ፡፡ አንዴ ጭልጋ ላይ ታርጋ የሌላት አባዱላ መኪና ሌሊት ስትንቀሳቀስ ትያዛለች፡፡ የያዟት ሁለት ፖሊሶችና አንድ የትራፊክ ፖሊስ ነዉ፡፡ መኪናዋ ከሹፌሩ በኩል ያለዉ ጋቢና ወንበሩ ተነስቶ በቀዝቃዛ ፍሪጅ የተገጠመ ነዉ፡፡ ትራፊክ ፖሊሱ ያን ፍሪጅ ሲከፍተዉ ፍሪጁ በትኩስ የሰዉ ኩላሊት በደም ተለዉሶ ያገኛል፡፡ ትራፊክ ፖሊሱ ከዛን ቀን ጀምሮ የአእመሮ ህመምተኛ ሁኖ አሁንም ጭልጋ አለ ይባላል፡፡
የኩላሊት ንግድ ሽሪካቸዉ ግድያ
አንድ የጎንደር ጓደኛየ እንዳጫወተኝ በዚህ ንግድ ዉስጥ አብረዉ የሚሳተፉ የሚባሉ የጭልጋ ወረዳ የፖሊስ መመሪያ ዉስጥ የሚሰሩ እንዲሁም አንድ ጎንደር ዉስጥ ታዋቂ ደላላ የነበረ:: ከጊዜ በኋላ ባለመግባባትም ይሁን በእዉነተኛነት የአማራ ክልል ፖሊስ እኒህን ሰወች ይዞ ያስራቸዋል፡፡ አንደኛዉ ጎንደር ዉስጥ በጣም ታዋቂ ነዉ፡፡ስሙን ለጊዜዉ ረሳሁት፡፡ ብዙ ወጣቶች ጋር ይተዋወቃል፡፡ መኪናም ባጃጅም እየገዛ ለብዙ ወጣቶች ሰቷል ይባላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ህገወጥ ንግድ የተገኘ ገንዘብ ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ ጎንደር ይታሰራል፡፡ ባንኩ እና ባጠቃላይ የንግድ ሸሪኮቹን በምርመራ ይለያሉ፡፡ በራሱ አካዉንት ከንግድ ባንል ለሁለት ሰዉ ትራነስፈር ያደረገበት ሰነድም ይገኛል፡፡ ለእያንዳንዳቸዉ 1.5 ሚሊየን ብር ትራንስፈር አድርጓል፡፡ ከዚህ ዉስጥ አንዱ ሚኒስቴር ነዉ፡፡ አንዱ ከፍተኛ የመካላከያ አዛዥ ነዉ፡፡ ይሄን ሚስጥር ለመደበቅ ሲባል የጎንደር እስር ቤት በእሳት ይያያዝና ሰወች እንዲጎዱ ይደረጋል፡፡ ጥይት ተተኩሶ ከተመቱት ሰወች ዉስጥ አንዱ ይህ ልጅ ነዉ፡፡ በአንድ ጥይት እግሩን ተመቶ ነበር የቆሰለ፡፡ ከፌደራል ተደዉሎ እንደሞተ እና እንዳልሞተ ያረጋግጣሉ፡፡ ከዛም ከቆሰለ በኋላ ሆስፒታል እንዉሰድህ ብለዉ ይዘዉት ይወጣሉ፡፡ ሆስፒታል ሲደርስ በ 8 ጥይት ተደብድቦ የሞተዉ አካል ነበር የደረሰዉ ጥይት ተደብድቦ የሞተዉ አካል ነበር የደረሰዉ፡፡
ህገወጥ የሰዉ ዝዉዉር
መተማ ከሁለት በኩል ከፍተኛ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር ታካሂዳለች፡፡ ይህ በዋነኛነት የሚፈጸመዉ በህወሃት ኮሎኔሎች ነዉ፡፡አንደኛዉ ከሽሬ የኤርትራወች ካምፕ የሚነሳ ሲሆን ሁለተኛዉ ከአዲስ አበባ ነዉ፡፡ ኤርትራወች መጀመሪያ ከካምፕ በኮሎኔሎች አማካኝነት ይወጣሉ ከዛም በኮንተራት መኪና ደባርቅ ይገባሉ፡፡ ደባርቅ ያንድ ባለስልጣን ቤት አለ እዛ ለሁለት እና ሶስት ቀን ይቆለፋሉ፡፡ ሲመቻች ወደ ጎንደር ይገባሉ ጎንደር ወጣ ብሎ አንድ የህወሃት ባለሃበት የሆነ ሌላ ምንም ነገር የማይሰራ አዘዞ አካባቢ መጋዘን አለ እዛ እንደገና የቆለፋሉ፡፡ ከዛም በማታ ወደ መተማ ጉዞ ይደረግ እና መተማ ከተማዉ ሳይደርሱ ገጠር ገጠሩን በማድረግ ድንበር ላይ ለሱዳን ወታደሮች እና እዛ ላሉ ለህወሃት ደላሎች ይሰጣሉ፡፡ እዛ ለመድረስ በነብስ ወከፍ 20 ሺህ ብር ይከፍላሉ፡፡ከሶማሌ እና በተለይም ከኦሮሚያ የሚመጡት ደግሞ ከአዲስ አበባ ተነስተዉ ባህርዳር መኮድ የአንድ የህወሃት ኮሎኔል ቤት ያድራሉ፡፡ ከዛም ማክሰኝት የአንድ የባለሃብት መጋዘን ዉስጥ ይቆለፋሉ ከዛም አዘዞ ከኤርትራወች ጋር ይቀላቀላሉ፡፡ይህ በህወሃት ኮሎኔሎች እና በሱዳን ኮሎኔሎች የሚሰራ ስራ ነዉ፡፡ ለዚህ ዳረጎት ደግሞ ህወሃቶች ለሱዳኖች ባካባቢዉ ያለዉን የእርሻ መሬት እንደፈልጉ ከገበሬ እየቀሙ እንዲወስዱ ፈቅደዉላቸዋል፡፡ እንደተስማሙ ደግሞ ሚታወቀዉ በሁመራ በኩል እንዲች አይነት ነገር አይነሳም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የትግራይ ነዉ የአማራ ይሄ ነዉ ብለዉ አስምረዉ ሰተዋቸዋል፡፡ከሁለት አመት ወዲህ ደግሞ የሱዳንና የትግሬ ጠላት አማራ መንግስት ሊሆን ነዉ በሉት እያሉ ገበሬዉን አስጨርሰዉታል፡፡ ይሄን መሬት አሁን ካልወሰዳችሁ መቸም አትወስዱትም ይሏቸዋል፡፡
የዶላር ዝዉዉር
መተማ ዮሃኒስ ማለት የበሬ ግንባር የምታክል ከተማ ነች፡፡ 13 ባንኮች ግን አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ዋናዉ ስራቸዉ የዶላር ምንዛሬ ነዉ፡፡የአካባቢዉ የዶላር ገቢያ በኮሎኔሎች የተያዘ ነዉ፡፡ በዚህ አካባቢ የሚገኝ ዶላር አንዲትም ለብሄራዊ ባንኩ ገቢ አይሆንም፡፡ ስራዉ ሁለት ነዉ፡፡ በሱዳን በኩል የሱዳን ኮሎኔሎች ዶላር አምጥተዉ መተማ ላይ ለህወሃት ባለሃብቶች ይሸጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ዶላር በካረቱም በኩል ዱባይ ያደርሳሉ፡፡ በተለይም በሶማሌ ላንድ ባኩል አሁን አሁን እየተዘጋ ስለመጣ ህገወጥ ገንዝብ ዝዉዉር አሁን በመተማ በኩል ሁኗል፡፡ ወጋገን ባንክን ለህጋዊነት ይጠቀሙታል፡፡ ባንድ ወቅት ወታደር እየተጫወተበት እኛ እዚህ በሙቀት እየነደድን እየሰራን ይሉ እና የንግድ ባንክ ሰራተኞች የተሰበሰቡወን ዶላር አዉጥተዉ ተከፋፍለዉ ይሸጣሉ፡፡ ከማህላቸዉ ከኮሎኔሎች ጋር ግንኙነት የነበረዉ ሰራተኛ ይሄን ያጋልጣል፡፡ ከዛም ብዙ ሰራተኞች በወቅቱ ተባረሩ፡፡
የኤርትራ መኮንኖችና ህወሃት
ባንድ ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ከመተማ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ታርጋ የሌለዉ መኪና ጭልጋ ላይ ይያዛል፡፡ ወደ 10 የሚሆኑ ሰወች ወርደዉ ሲፈተሹ ከኤርትራ የመጡ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት መታወቂያ የያዙ እና ትቂት ኢትዮጵያዉን ናቸዉ፡፡ አሸባሪዉን ያዝነዉ ብለዉ ፖሊሶች በደስታ ፈነደቁ፡፡ ሹፌሩም ፖሊሶችን ወደ ማስፈራራት ይገባል፡፡ እኒህ ሰወች ለጉዳይ ነዉ ወደ ጎንደር የሚሄዱት ከላይ ድረስ ይታወቃል እንሀድበት ይላል፡፡ ፖሊሶችም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ለመዉሰድ ሲዘጋጁ፡፡ ስልክ ወደ ፌደራል ይደዉላል፡፡ ወዲያዉ ለሰሜን ጎንደር ዞን ጸጥታ ሃላፊ ተደዉሎ እንዲህ አይነት ሰወችን ያስቆሙ ፖሊሶች ባስቸኳይ እንዲያዙ ተብሎ መልክት ይተላለፍል፡፡ ፖሊሶቹ ባይያዙም እንዲለቋቸዉ ተደረገ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ የመተማ እና ጭልጋ ፖሊሶች ታርጋ የሌላቸዉን መኪና ለህይወታቸዉ በመስጋት ማስቆም እና መፈተሸ አቆሙ፡፡
የመሳሪያ ንግድ
የህወሃት ኮሎኔሎችን ከሱዳን ወታደሮች ጋር በደንብ በጥቅም ያያዘዉ ሌላዉ የመሳሪያ እና ጥይት ንግድ ነዉ፡፡ የሱዳን ወታደሮች የማያመጡት መሳሪያ የለም፡፡ በተለይ ማየካሮቭ ሽጉጥ፤ የቱርክ ሽጉጥ እና የክላሽ ጥይት፡፡ ይሄን ንግድ የሚያጧጡፉት የህሀዋት ኮሎኔሎች ኬላ ላይ ከተቀመጡት ህዋሀቶቸ ጋር በመሆን ነዉ፡፡ የጉሙሩክ ባለሙያወች ከፌደራል የተመደቡ ሁሉም ህወሃት ናቸዉ፡፡ እናም ከኮሎኔሎች ጋር ሁነዉ ይሄን ንግድ ይነግዳሉ፡፡ ኮሎኔሎቹ ባካባቢዉ ላሉት አማራወች ይሸጡታል፡፡ ወደ ጎንደር እና መስል ከተሞች እንዴት ሊወስዱት እንደሚችሉ ከገዙት ሰወች ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ጉዞ ሲጀምሩ መከታተል ይጀምራሉ፡፡ መተማ ያለዉ ኮሎኔል ጭልጋ ሰራባ አካባቢ ላለዉ ኮሎኔል በዚህ በዚህ አይነት መንገድ እኔ የሸጥኩላቸዉ ሰወች ይዘዉ እየመጡ ነዉ ብሎ መረጃ ይሰጣል፡፡ ወዲያዉ ይያዙ እና መሳሪያዉ እና ጥይቱ ይወረሳሉ፡፡ መጀመሪያ የሸጠዉ ኮሎኔል እና ጭልጋ ላይ ወራሹ እንደገና ይሸጡታል፡፡ የጭልጋዉ ኮሎኔል ደግሞ ጎንደር አዘዞ ላለዉ ወይም በአርማጭሆ በኩል ከዞረ ሳንጃ ላለዉ ደዉሎ መቶልሃል ይላል፡፡ አሁንም ይወረሳል፡፡ እና ሻጩ ሳይያዝ ገዡ አማራ በዚህ መንገድ ሁለቴ ከስሮ ይያዛል፡፡ በጣም የተጣሉት ከሆነ ሚዲያ እንዲዘጋጅ ይደረግ እና በሚያ እጅ ከፍንጅ ተያዘ ይላሉ፡፡ እነዚህ ገዥወች ሲታሰሩ ደግሞ የኮሎኔሎቹ ገቢያ ስለሚቀንስ ሄደዉ ያስፈቷቸዋል፡፡ እኔ ነኝ ያስፈታሁ በማለት ከዛ በኋላ ባሪያዉ አድርጎት ይቀራል፡፡
ለዚህ ሁሉ ዉለታ፤ ሱዳን የህወሃት የጦር መኮነኖች እንደፈለጉ እንዲፈነጩ በመፍቀዱ የህሀዋት ወታደሮችም የሱዳን ወታደሮች እንደፈለጉ ድንበር አካባቢ እንዲፈነጩ ፈቅደዉላቸዋል፡፡ አንዳነዴ ገበሬዎች ተደራጅተዉ ሊገጥሙ ሲሄዱ ቀድመዉ በወታደራዊ መገናኛቸዉ እነዚህ የህወሃት ኮሎኔሎች ለሱዳኖች ሁኔታዉን ይነግሯቸዋል፡፡ ለዛ ነዉ ገበሬወች ሳያስቡት ብዙ ጊዜ የሚሞቱት፡፡
መተማ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰልፍ መዉጣት እንፈልጋለን ያሉ እና ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች በደህንነቶች እየታፈኑ ሲታሰሩ ሰንብተዋል፡፡ ምን አለፋችሁ ሰሜን ምእርብ አማራ የህወሃት ነዉ፡፡ ለስሙ ነዉ በአማራ ክልል ስር ያለዉ፡፡
ይሄ ሁሉ ሲሆን ብአዴን ምርት እና ምርታማነት ለመጨመር እያለ እርከን የሆነ ቀበሌ ዉስጥ ሲያሰራ ይዉላል፡፡ ይሄን አያዉቁትም፡፡
እዛ አካባቢ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፡፡ የጉሙሩክ እና የባንኮች ስራ መፈተሸ አለበት፡፡ ሰራተኞች መባረር አለባቸዉ፡፡ ወታደሩ ከንግድ እንዲወጣ ብሎም እድሜ ልክ እዛ አካባቢ ያሉ አዛዦች ወይ መጠየቅ አለባቸዉ አለያም መነሳት አለባቸዉ፡፡ የአማራ ክልል መንግስት የአካባቢን ጸጥታ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር አለበት፡፡ የሰሜን ጎንደር ዞን፤ የመተማ ወረዳ፤ የምእርብ አርማጭሆ እና ጭልጋ አካባቢ የጸጥታ ሰወች ሙሉ ለሙሉ መቀየር አለባቸዉ፡፡ ባካባቢዉ ያሉት ደህንነቶች ንግድ ዉስጥ እና ህወሃት የመደባቸዉ ስለሆኑ መባረር አለባቸዉ፡፡ የሱዳን መንግስት ወታደሩን ካካባቢዉ እዲያርቅ መነገር አለበት፡፡ የሞቱት እና የቆስሉት ገበሬወች እንዲሁም የታፈኑት እያንዳንዱ ተቆጥሮ የሱዳን መንግስት እና የአካባበዉ ጸጥታ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የአማራ ልዩ ሃይል በመተማ እና ቋራ መስመር ማስፈር አስፈላጊ ነዉ፡፡
Filed in: Amharic