>

‹‹መፈንቅለ መንግሥት አደርጋለሁ ብሎ የሚሞክር ኃይል ካለ ራሱ ነው የሚጠፋው›› (ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ)

‹‹ መፈንቅለ መንግሥት አደርጋለሁ› ብሎ የሚሞክር ኃይል ካለ ራሱ ነው የሚጠፋው››
ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ … 
‹‹በመከላከያ ውስጥ በከፍተኛ አመራር ደረጃ የብሔር ተዋፅዖው ችግር አለበት፡፡ ብዙ ጊዜ ‘ተመጣጥኗል’ ተብሎ ሲገለፅ ነበር፤አልተመጣጠነም፡፡ ለማመጣጠን የግድ ሪፎርም መካሄድ አለበት››
‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ተወካይ ነኝ ብለህ ጫካ ቆይተህ ምንም ውጤት ሳታመጣ ስትቀር፤ ሕዝቡ ታግሎ ባመጣው ለውጥና ውጤት ባለቤት ለመሆን መሞከር ነውር ነው፡፡ እንኳን ዛሬ ድሮ 30ሺ ተዋጊ ኃይል ይዞ ያልሠራውን ሥራ በአንዴ መጥቶ ለመሥራት መሞከር ትርጉም የለውም››
‹‹ሠራዊታችን የሕገ መንግሥት ጠባቂ ነው ሲባል ግልጽ ነው፡፡ ሕገ መንግስቱን ጠባቂ የሆነ ሠራዊት መፈንቅለ መንግሥት አያደርግም፡፡ ሀሳቡም ራሱ ነውር ነው፡፡ የእኛ ሠራዊት መፈንቅለ መንግሥት ቢያደርግ አደገኛ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግሥት ማድረግ በሠራዊቱ የግንባታ አቅጣጫዎች ላይ ክልክል ነው፡፡ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ይሄንን ጥሶ መፈንቅለ ‹መንግሥት አደርጋለሁ› ብሎ የሚሞክር ኃይል ካለና ቢሞክር ራሱን ነው የሚጠፋው››
‹‹አሁን ሕገ መንግሥቱን ስለሸረሸርነው ነው እንጂ ሕገ መንግሥቱ እኮ ስለ ኢትዮጵያ ነው የሚያወራው፡፡ ሠራዊታችን የሚያወራው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ሕገመንግሥቱ ነው፡፡ ቋንቋውም ይሄ ነው፡፡ ይህንን በአዋጆች፣ በደንቦችና በመመሪያዎች ወደ መሬት ማውረድ ያለበት ፖለቲካዊ አመራሩ መሆን ነበረበት፡፡ ፖለቲካዊ አመራሩ ደግሞ ይሄን በደንብ እየመራው አይመስለኝም፡፡ ለዚህ  ነው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ  ችግር ውስጥ የገባው››
‹‹ብዙ ዓመታት አገልግለው ጡረታ ሳያገኙ የተሰናበቱ የቀድሞው ሠራዊት አባላት የጡረታ መብታቸው  እንዲከበር እየተሠራ ነው፡፡ ጡረታቸው ሳይከበር የወጡ ሰዎች በጥፋት የተከሰሱ ሰዎች ነበሩ፡፡ ባለፈው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአንዳንዶች ማዕረጋቸው በክብር እንዲመለስ ጡረታቸውም እንዲከበር ካስደረጉ በኋላ በዚሁ መነሻነት በእነሱ ብቻ ሳይቆም ጡረታቸው ሳይከበር የተሰናበቱ የቀድሞው የሠራዊት አባላት በሙሉ ማሕደራቸው ተፈልጎ ታውቀውና ተለይተው መከላከያ ሚኒስቴር ውሳኔ ሰጥቶ ጡረታቸው እንዲከበር እየሠራን ነው›› … ብለዋል፡፡ ምንጭ :- ልኡል አምደጽዮን
Filed in: Amharic