>

ህዝቡ ጠይቆ የተነፈገውን ዳኝነት በራሱ መንገድ ከማግኘቱም በላይ መልእክት አስተላልፎበታል!!!

ህዝቡ ጠይቆ የተነፈገውን ዳኝነት በራሱ መንገድ ከማግኘቱም በላይ መልእክት አስተላልፎበታል!!!
እየሩሳሌም ተስፋው
ዛሬ በደብረማርቆስ የተፈጠረውን ነገር ግማሹ ሲያወድስ ግማሹ ሲያወግዝ ተመለከትኩ ሁሉም የመሰለውን ሃሳብ መግለፁን ባልቃወምም ምንም ነገር ላይ ለመፍረድ ግን የጉዳዩ ባለቤት ጫማ ላይ መቆም ያስፈልጋል
ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች እየተዘዋወሩ መርዝ በመርጨት እርስ በርስ በማጋጨት ላይ የሚገኙ የተለያዩ የህወሃት ነባር ታጋዮችን እያየን ሲሆን በተለይ በረከት እና ህላዌ በተለያዩ የአማራ ክልሎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ
በዛሬው ቀን ደብረማርቆስ ላይ የበረከት ስምኦን መኪና ናት የተባለችው እና አርፎበታል የተባለው ሆቴል በእሳት መጋየቱን አይተናል
☞እነዚህ ሰዎች እንደልባቸው ከተማ ለከተማ እየተዘዋወሩ ጥቃቅን ገንዘብ ከመስጠት ጀምሮ መሣሪያ እና ቦንብ እያስታጠቁ ሰለማችንን ለመንሳት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ
 
☞እነዚህ ሰዎች የፌደራል መንግስቱ በከባድ ወንጀል ጠርጥሮት ለምርመራ እሚፈልገውን ወንጀለኛ አሳልፈን አንሰጥም ብለው የወንጀለኛ መሸሸጊያ ዋሻ እየገነቡ ይገኛሉ
 
☞እነዚህ ሰዎች የሀገሪቱ ጠ/ሚር በሚያደርገው ጉዞ ለደህንነቱ በመስጋቱ በጅቡቲ ዞሮ እንዲሄድ ያስደረጉ የሀገር አሸባሪዎች ናቸው 
 
☞እነዚህ ሰዎች እኛ ፈልጠን ቆርጠን ካልገዛናችሁ በሚል እብሪት ተነሳስተው ከሱዳን ገጥመው የውክልና ጦርነት ከፍተውብናል
 
☞እነዚህ ሰዎች እኮ….በጣም ብዙ ጥፋት የፈፀሙ ለመፈፀምም ያላቸውን ሃይል በሙሉ እየተጠቀሙ ይገኛሉ
በሀገር ደረጃ አስጊ የሆኑ በመንግስትም በዝምታ እየታዩ ያሉ የወንጀለኞች ስብስብ እንዴት ይህ ርምጃ ይወሰድባቸዋል ለፍርድ ማቅረብ ነው ያለብን ለሚሉ ሰዎች ለፍርድ እንዲቀርቡለትማ ህዝቡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድምፁን ሲያሰማ ነበር
ከላይ የዘረዘርኩትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ አድራሻቸው ጠፍቶበት አልነበረም መንግስት እስካሁን ያላሰራቸው(በራሱ መንገድ እየሄደ ሊሆን ቢችልም መዘግየቱ ግን ዋጋ እያስከፈለን ነው)
ይህ ህዝብ በተደጋጋሚ ጊዜ አስታግሱልን ለፍርድ አቅርቡልን በማለት ሲማፀን ቆይቷል
በዛሬው እለትም ሆቴሉን ከበው እንዲወጣ በድምፅ ሲጠይቁ ነበር ከዛ በኋላ ነው ወደ ማቃጠሉ የገቡት
በተደጋጋሚ ግዜ ፍትህን ጠይቆ ምንም ምላሽ ስላላገኘ በራሱ መንገድ የተጠማውን ፍትህ ለማግኘት ጥረት አድርጓል
ይህ ደግሞ ሊያስኮንነው አይገባም ትናንት ፍትህን በማጣቱ ሲያደርገው የነበረ ነው ዛሬም እያደረገው ይገኛል መልስ ካላገኘ ነገም ይቀጥላል
በረከት ደብረማርቆስ ላይ የእውነት ቢገኝም ባይገኝም ለእሱም ሆነ ለሌሎቹ የቀን ጅቦቹ ጥሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ካሁን በኋላ በገደሉት በአሰቃዩት በሚጠሉት ህዝብ መሃል ሌላ ጥፋት ለመስራት እንደስከዛሬው አይንቀሳቀሱም
ለነሱ መሸሸጊያ የሚሆኑ ሆቴሎችም አገልግሎት ለመስጠት አይደፍሩም እና የዛሬው የደብረማርቆስ ወጣቶች የሰሩትን ስራ ምንም ጥፋት አላየሁበትም ህዝብ ሁሌም ትክክል ነው
የዛሬው ጥሩ ማስጠንቀቂያ ቢሆንም ለሚመጣው መጠንቀቅ አግባብ ነውና ይታሰብበት
Filed in: Amharic