>

በቂሊንጦ ብጥብጥ ተነስቷል

በቂሊንጦ ብጥብጥ ተነስቷል

ሪፖርተር – ታምሩ ጽጌ 

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ውስጥ ዓርብ ሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ብጥብጥ መነሳቱ ታወቀ፡፡

የታሳሪ ቤተሰቦች ምግብ ለማድረስ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በሥፍራው ቢገኙም እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎችና አድማ በታኞች በግቢው ውስጥ እየተሯሯጡ ሲሆን፣ ከውስጥ የጥይት እና “አብይ ውሸታም … ጨረሱን ገደሉን..” የሚል በሲቃና ዋይታ የተሞላ የጩኸት ድምፅ እየተሰማ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ ጠያቂ ቤተሰቦችም የተፈጠረውን ባለማወቃቸው፣ በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ የማረሚያ ቤቱን ኃላፊዎች ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡

https://www.facebook.com/812185372196585/posts/1743192685762511/

 

ፖሊሶች እናስራችኋለን “ዶክተር አብይ ሲያስፈታችሁ እናያለን!!!” እያሉን ነው!!
የማረሚያ ቤት ሃላፊ ቢቀየርም ድብደባው ከታራሚ ወደ ጋዜጠኞች ዞሯል፡፡
.
አዲስ ቴቪ
.
መነጋገሪያ ሆኗል፡፡በራሱ ድክመትና በጋዜጠኞቹ ጥንካሬ..የአዲስ አበባ ምክር ቤት አገራዊ ለውጡንና አንድነቱን በመደገፍ ለመስራት ዝግጁ አይደለም  ብሎታል፡፡
.
የህዝብ ፍላጎትና ችግር እንዳይነገር የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ አመራሮች አፈና እንደሚያደርጉ የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለስራ የሄዱ ጋዜጠኖች በፖሊስ ተደብድበዋል፡፡
.
እስረኛ ጠያቂዎች እየተንገላቱ ነው፡፡ፖሊሶች እናስራችኋለን፡፡  ዶክተር አብይ ሲያስፈታችሁ እናያለን እያሉም ነው፡፡
በዚህ ሰዓት  ዶክተር አብይን መደገፍ ግድ ሆኗል፡፡ካልሆነ የለየላቸው አንባገነኖች ሊበሉን ይችላሉ፡፡ዳግም ሊያኮላሹና ቶርች ላያደርጉ የሚችሉበት ምክንያት የለም፡፡ዶክተር አብይ ርምጃቸውን እንዲያፈጥኑና እከታች እንዲያደርሱ ልናበረታቸው ይገባል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=266968550727505&id=100022430873964

 

Filed in: Amharic