>

ደብረማርቆስም ይሁን አዲስ አበባ በረከት ሞቷል! (ጌታቸው ሽፈራው)

ደብረማርቆስም ይሁን አዲስ አበባ በረከት ሞቷል!
ጌታቸው ሽፈራው
የደብረማርቆስ ሕዝብ አንድ ሆቴል ከበበ፣ መኪና ያዘ፣ እቃ ያዘ፣ ሹፌሩን ፈትሾ መረጃ አስተላለፈ። በዚህ ሁሉ ወቅት ፖሊስ ሆቴሉ ውስጥ አንድ አካል እንዳለ አስመሰለ። ወይንም አደረገ። በረከት አዲስ አበባ እንዳለ የሚናገሩ አሉ። ሕዝብ ደግሞ ደብረማርቆስ ነው ብሎ ከብቦ ውለዋል!
ምን አልባት ይህ ሴራ ይሆናል። ቅድም እንዳልኩት ሁሌም መግደያ ሰበብ ይፈልጋሉ፣ ወይንም ከእነ በረከት  በተቃራኒ ያሉትን መክሰሻ ምክንያት ይፈልጉ ይሆናል።
 ይህ የእነ በረከት ሴራ ከሆነ ከበረከት በላይ  ገዱ አትርፏል። ዶክተር አብይ አትርፏል።  በረከት ስሞን ከአሁን በኋላ በጎንደር፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን ጎዳናዎች መንቀሳቀስ እንደማይችል የዛሬው ቤተ ሙከራ ነው።  ሕዝብ በባነር ብቻ ሳይሆን በአካል እንደሚዘምትበት አሳይቷል። ሕዝብ የቀን ጅብ ያላቸውን ላይ እርምጃ በመውሰድ ከእነ አብይና ገዱ ጎን እቆማለሁ ብሏል። በሕዝብ ሕግና ስሜት መሰረት!
አንድ አካል ጠላት ብሎ የሚፈርጀው አካል ይኖራል። የሀገሬ ሰው የሰይጣናን ያህል ክፉ አልተሳለለትም። መብራት ሲጠፋም፣ መብረቅ ሲጥልም ያማትባል።  ክፉ ነገር አለበት ብሎ ባሰበው ሁሉ ሳይጣንን ያባርርልኛል ብሎ ያሰበውን ያደርጋል።
 የደብረ ማርቆስን ሕዝብ ከበባ እንደስህተት የሚያይ ካለ በረከት ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጠላትነት አቃልሎታል ማለት ነው። ልክ ሰይጣን ተደርጎ የተሳለን ሁሉ ሰይጣን እንደሚደረግ ሁሉ በረከት ነው የተባለን በረከት ብሎታል።  ሰውን ብቻ ሳይሆን ሰው የሚመስልን ግዑዝም ቢሆን “በረከት ሄደልህ” ቢባል ያለውን ጨብጦ የሚገሰግስ ሕዝብ ተፈጥሯል። ሕዝብ የሚያስበው በተበደለው መጠን ነው!
ሰው ጠላቴ ነው ላለው ምክንያት ይቆጥባል። የመበደል ስሜት፣ የመበደል ብዛት ስሜትን ይወልዳል። አንድን ምስኪን ልጁ የተገደለበትን ሰው ከፊት ለፊቱ የሚሄድን “ይህ ነው የገደለው” ብትለው ተረጋግቶ ከሚያስበው ይልቅ የልጁ ሀዘን የጫነው ስሜታዊነቱ መሰረት የሚወስደው እርምጃ ያመዝናል።
እንኳን ያላቀደ፣ የታቀደበት ሕዝብ ይቅርና አሜሪካ እንኳ ከእሷ የሚያንስ መዋቅር ያላት ኢራቅ ውስጥ አለ ያለችውን አጥታለች።  የሰጋችው የከፋ ስለነበር ብዙ ለፍታ አጥታለች። አለ ብላ ወስና አላገኘችም። በመሆኑም የደብረማርቆስ ሕዝብ በረከት ነው ተብሎ ከቦት የዋለውን ባያገኘው፣ ቢሳሳት ይህን ያህል መነጋገሪያ ሊሆን አይችልም።
ዋናው በረከት አለመገኙ አይደለም። በረከት አስመራ ሆነ አዲስ አበባ ሞቷል። መኪናውን ያቃጠለው ሕዝብ እሱንም ከማቃጠል አይመለስም ነበር። በረከት ሞቷል። ነገም ቢገኝም አይተርፍም! እንደ ሕዝብ ስሜት!
ራስን ማጥፋት ወንጀል ነው።  ትክክልም አይደለም። እንደ በረከት የተደረገበት  አእምሮ ያለው ሰው ራሱንም ሊያጠፋ ይችላል። ነገ ሲያገኙኝ ይገድሉኛል ብሎ አይደለም። ሕዝብ ላይ የፈፀመውን እንደገና አስቦ “እኔ በሕይወት መኖር የሌለብኝ ሰው ነኝ” ብሎ በስሜት ያስወስናል።
በረከት ይህ ላይጨንቀው ይችላል። ግን በረከት ሞቷል! አዲስ አበባ፣ አስመራ፣ ዋሽንግተን መገኘቱ አይደለም ዋናው።  በዚህ ሕዝብ ዘንድ ከአሁን በኋላ ቦታ የለውም። ይህ ሕዝብ በየጎዳናው ሲያየው ተሸማቅቆ፣ ፈርቶ የሚያልፈው አይደለም። እንደ እባብ ቀጥቅጦ የሚገድለው ሰው መሆኑን በተግባር አሳይቷል። በረከት ቢኖር እንደመኪናዋ እንደሚቃጠል ግልፅ ነው! በረከት ተገኘም አልተኘም ሞቷል! ይህን ቢያስብ ይሻለዋል!
ትልቁ ነገር ግን! ጠላትን ለመምታት ማለም፣ ማነጣጠር ያስፈልጋል።  ጠላቱን የሚፈልግ መረጋጋት አለበት። ሌላ ጠላት ላለመፍጠር መረጋጋት አለበት! የዛሬው የሕዝብን ስሜት ለመውቀስ የሚጥር ካለ እሱ የዚህን ሕዝብ መከራ ያቃለለ ወይንም የማያውቅ መሆን አለበት! ይህ የተበደለ፣ የዘረፈ፣ የተገረፈ ሕዝብ “ቀስ! ተረጋግተህ!” ሊባል ይገባ ይሆናል።  ያን ሁሉ መከራ የሰራበትን የሚመስል ሲያይ “ነው” ማለቱ የሚፈልገውን ጭራቅ ባህሪ፣ ከስቃዩ፣ ከበደሉ አንፃር ስሜታዊ መሆኑን ሊነገረው ይችል ይሆናል እንጅ ስህተት ነው ማለት አይቻልም።
በረከት ግን የትም ይሁን ሞቷል!
Filed in: Amharic