>

የፖለቲካ ጌሙን በብቃት መጫወት እንጂ "እንዲህ ብሎኝ ነበር" እያሉ  ዳር መቆም አያዋጣም!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የፖለቲካ ጌሙን በብቃት መጫወት እንጂ “እንዲህ ብሎኝ ነበር” እያሉ  ዳር መቆም አያዋጣም!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ሀ~ Well  የኢሳያስ አፈወርቂን ጉብኝት ምክንያት አድርጎ ይች የቅኝ ገዥነት (Colonial thesis)  ትርክት በዛች ።
ኢሳያስ አፈወርቂ ” ኢትዮጵያ ቅኝ  አገር ነች ብሎ እንደት እንቀበለዋለን ?” የሚል አሪጊዩመንት ነገር መሆኑ ነው።
እርግጥ ነው የኤርትራ ትግል መሰረቱ “የኤርትራ  ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው። መፍትሄውም ነፃ መውጣት ነው” የሚል እንደነበርና በዛውም አግባብ መልሱ እንደተመለሰ ግልፅ ነው።
 ሁ~ ግን እኮ እውነት ለመናገር በኋላ እነ ኢሳያስ እርምትና ማስተካከያ ቢያደርጉበትም   ቅኝ ተገዝተናል የሚሉት በኢትዮጵያ ሳይሆን ቀጥታ በአማራ ነበር።
“አማራ ቅኝ ገዝቶናል ” የሚለው የፖለቲካ ነዳጅ ደሞ  የዛን ዘመን የአገራችን  ብቻ ሳይሆን አውሮፓ ድረስ የዘለቀ መቀስቀሻ ትርክት ነበር።  ኢሳያስን ብቻውን በዚህ ጉዳይ ላይ መውቀስ ወይ የዋህ መሆን ነው ወይ አላዋቂነት ነው።  ኢሳያስ አለም ሲጠቀምበት የነበረውን የፖለቲካ ፋሽን ተቀበለ ።
ሂ~ከአድዋ ድል በኋላ አውሮፓውያንን እኮ ” አማራ  የሚባል ህዝብ ሊወራችሁ  ነው”  የሚል መሰረቱን ሮም አድርጎ  ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ይሰራጭ ነበር።
በዚህ ጉዳይ ላይ ኢሳያስን ብቻ ነጥሎ መውቀስ ያዋጣል ወይ?
ሃ~የኦሮሞ ኤሊትና የፖለቲካ ሀይሎች እስካሁንም ድረስ አርጊዩመንት “የኦሮሞ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ፣ መፍትሄውም ከቅኝ ገዥው ሃበሻ (አማራ)  ነፃ ወጥተን ኦሮሚያን መመስረት ነው ” የሚል Colonial thesis አይደለም ወይ?
ሄ~ብዙ ጊዜ በፅሁፌ የምገልፀው ኦውስትሪያዊው የጀርመን ኤምባሲ ድፕሎማት ሰር ባሮን ሮማን ፕሮችስካ ” የነጭ የሰው ዘር የሆነ ሁሉ ለዚህ አማራ ለሚባል ህዝብ በፖሊሲ የታገዘ መፍትሄ ካላበጀለት ይሄ ህዝብ ከአፍሪካ አልፎ ለአውሮፓም ያሰጋል ” አላለም ወይ ? The powder barrelን ማንበብ በቂ እኮ ነው።
ህ~ሀይስኩል ታሪክ ትምህርት ላይ የአለም ኮለኒያል ቅኝ ገዥ አገሮች
1~ እንግሊዝ
2~ ፈረንሳይ
3~ ቤልጅየም
4~ ፖርቱጋል
5~ጣሊያን
6~ ስፔን
7 ~ ጀርመን
~ አማራ  ኢንፎርማሊ
የአለም አካዳሚክ ኮሚዩኒት በየመፅሀፋ አማራ ያው ጥቁር ህዝብ ስለሆነ  8ኛ ተራ ቁጥር  ላይ ቅኝ ገዥ ብሎ አላስቀመጠውም እንጅ ኢንፎርማሊ እኮ አማራ በአለሙ ሁሉ ቅኝ ገዥ ተብሎ ሌብል ተደርጓል።
ሆ~አሁን ከስትራቴጅ አንፃር የሚያዋጣው ምንድነው ያለፈውን እያኘኩ “እንድህ ብሎኝ ነበር” እያሉ  ራስን ገለል ማድረግ ነው ወይስ የሀይል አሰላለፍን አስተካክሎ ለህዝብህ ዘላቂ ጥቅም የፖለቲካ ጌሙን መጫወት ነው ? መልሱን እዛው ለራስህ መልሰው ለእኔ አትመልስልኝ እኔማ መልሱ ምን እንደሆነ አውቀዋለሁኝ።
Filed in: Amharic