>

ተፈናቃይ ዜጎችን በአ.አ ማስፈሩ አፈናቃዮችን "ግፉበት!" ለማለት ካልሆነ መፍትሄ ሊባል አይችልም! (ግርማ ካሳ) 

ተፈናቃይ ዜጎችን በአ.አ ማስፈሩ አፈናቃዮችን “ግፉበት!” ለማለት ካልሆነ መፍትሄ ሊባል አይችልም!!!  
ግርማ ካሳ 
ከሶማሌ ክልል ተፈናቀሉ የተባሉ ወደ ፩፰፻ የሚሆኑ ዜጎችን በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ መንደር ሊሰራቸው እንደሆነ ተመዘግቡን አነበብኩ። በዚህ ጉዳይ የተለያየ አስተያይተ እየተሰጠ ነው። እኔም ትንሽ ማከል ፈለኩ።
አንደኛ – እነዚህ ዜጎች የግፍ፣ የዘር ፖለቲካ ሰለባዎች ናቸው። መታወቂያቸው እየታየ፣ “ኦሮሞ” ስለሆኑ ብቻ በጭካኔ ከቅያቸው ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ናቸው። እስከ አሁን ድረስ ሳይቋቋሙ በካምፕ እየኖሩ ያሉ ናቸው። ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ደህንነታቸው የሚያረጋገጥ አካል አላገኙም። እነዚህ ወገኖች ወደ  ቅያቸው ተመልሰው ፣ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ መደረግ ነበረበት። የሚፈልጉትም ያንን ነበር። ግን አልተደረገም። ያን ማድረግ ባለመቻሉም እንደ ሁለተኛ መፍትሄ በሌላ አካባቢ እንዲቋቋሙ የተወሰነ ይመስላል።
ይሄ አፈናቃዮችን “ያደረጋችሁት ጥሩ ነው፣ ቀጥሉበት፣ ነገ ዜጎችን ብታፈናቀሉና መሬታቸውንና ቤታቸውን ብትወስዱ ፣ እኛ ሌላ ቦታ እናዘግጅላቸዋልን፣ እናቋቁማቸዋለን ” እንደማለት ነው።
በነገራችን ላይ ከኦሮሞ ክልል ሶምሌ፣ አማራ፣ ጌዴዎ.. ስለሆኑ ብቻ ብዙ ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል። የዘር ፖለቲካ ሰለባ የሆኑት ኦሮሞዎች ብቻ አይደለሉም። የኦሮሞ አክራሪዎች ላለፉት  ፪፯ አመታት አማራዎችን ፣ ላለፉት ፪ አመታት ደግሞ ሶማሌዎችን ፣ በቅርቡ ደግሞ ጌዴዎችን በግፍና በጫካኔ የኦሮሞ ነው ከሚሉት ክልል ሲያፈናቀሉ ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎችን  በዘራቸው ምክንያት  የማፈናቀሉን ነገር በጭራሽ መታገስና ማስታመም አያስፈልግም። የዘር ፖለቲካውና አየዘር አወቃቀሩ በየቦታው ነው እሳትን እየጫረ እያፋጀን ያለው» በቶሎ መቆም አለበት።  ዘርን ከፖለቲካችን ማወጣት መጀመር አለብን። ማንም ዜጋ በሁሉም የአገሪቷ ክፍል በሰላም የሚኖርበት የሕግ ዋስተና ማመቻት አለበት። ይሄ መሬት የትግሬ፣ ያ መሬት የኦሮሞ፣ እዚያ ማዶ የሶማሌ…የሚለው ነገር መቅረት አለበት። የዘር ፌደራሊዝሙ ፈርሶ ለአስተዳደር አመች የሆነ ፌዴራሊዝም መዘርጋት አለበት።
ሁለተኛ – የሚመረጠው ተፈናቃዮች ወደ ⷃቸው ተመልሰው በሰላም ኑሯቸውን እንዲኖሩ ማድረጉ ነበር። ያን ካለመዳረግ የተነሳ ግን ለረጅም ጊዜ በድንኳን ውስጥ፣  ልጆቿቸው ወደ ትምሀርት ቤት ሳይሄዱ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም። በመሆኑም በአዲስ አበባ ሆን በማንኛዉም ሌላው የአገሪቷ ክፍለ እንዲቋቋሙ መደረጉ ፣ ዜጎጎችን ሜዳ ላይ ጥሎ ከመርሳት በጣም የተሻለ ነው።
በዚህ አጋጣሚ አንድ ሊሰመርበት የሚገባ ነገር ማንኛዉም ኢትዮጵያ በማንኛው የአገሪቷ  ክፍል የመኖር ፣ የመስራት፣ የመቋቋም  መብት አለው። ተፈናቃዮች ከቅቸው ተፈናቅለው፣ በግድ በዚህ ቦታ ኑሮ መባል የለባቸው። የሚኖሩበትን ከተማ እንዲመርጡ መደረጉ አስፈላጊ ነው። ሸገርን መኖርን ፈልገው ወደ ሸገር ለመምጣት የወሰኑ ወገኖችን በሸገር  እግሮቻቸውን ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ የሸገር ልጆች ይሆናሉ። ሸገር የሁሉም ናትና።
በዚህ አጋጣሚ  በሸገር መኖሪያ ቤት ሊሰራላቸው ያሉ ወገኖቻችን በሸገር መኖርን ሲመርጡ የሚያመላክተው ትልቅ ነገር አለ።  እርሱም ሸገር ተወዳጅ መሆኗን ነው።
ሸገር ዜጎች በዘራቸው ምክንያት የማይሸማቀቁባት፣  የማይፈሩባት፣ ቀና ብለው የሚኖሩባት ምርጥ ከተማ ናት። የሽገርን ድንበር አልፋቹ ኦሮሞ ክልል ዘለቅ ስትሉ ግን የሰማይና የምድር ልዩነት ነው የምታዩት።ይደብራል ዘረኝነቱ፣ ይሄ ከፈረንጆች ያመጡት አስቀያሚው ላቲኑ …..
Filed in: Amharic