>

የቴዲን ከፍታ በወፍ በረር!!! 

የቴዲን ከፍታ በወፍ በረር!!! 
ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ
* ቴዲ፡ ዘፋኝ፡ ብቻ፡ አይደለም የዜማ፡ ደራሲ፡ ጭምር እንጂ፡፡ የዜማ፡ ደራሲም፡ ብቻ፡ አይደለም፡ ገጣሚ፡ ጭምር፡ እንጂ፡፡ገጣሚ፡ ብቻ፡ አይደለም፡ የታሪክ፡ አዋቂ፡ ጭምር፡ እንጂ፡፡የታሪክ፡ ፀሀፊም፡ ብቻ፡ አይደለም፡ ፡ ፖለቲከኛ፡ ጭምር፡ እንጂ፡፡
* ቴዲ፡ በዘመናችን፡ መክሊቱን፡ የሚኖር፡ ብቸኛ፡እድለኛ፡ ሰው፡ ነው፡፡
* ቴዲ፡ ሀይማኖተኛ፡ ቅን፡ አዛኝ፡ የፍቅር፡ ሰው፡ ነው፡፡ዘፈን፡ ሀጢያት፡ ነው፡ ብየ፡ አስባለሁ፡፡ ቴዲን፡ ስሰማ፡ ግን፡ እንባየን፡ መቆጣጠር፡ የማልችልበት፡ ቀን፡ አለ፡ ፡
* ቴዲ፡ ታሪክን፡ መከተብ ፡ ይችላል፡፡ ፍቅርን፡ ማሳየት፡ ይችላል፡፡ ጀግናን፡ ማወደስ፡ መቼም፡ የተፈጠረበት፡ ነው፡፡
* ቴዲ፡ ጃንሆይን፡ ሚኒሊክን፡ ቴዎድሮስን፡ ሀይለ/ገስላሴን፡ ቀነኒሳን፡ በቅንነት፡ ከፍ፡ ያረገ፡ ጀግና፡ ነው፡፡
* ቴዲ፡ አንደበተ-ርቱም፡ ነው፡፡ በሂወቴ፡ ቃለ፡ መጠየቁን፡ ሳደምጥ፡ ያስገረመኝ፡ ሰው፡ ነው፡፡
* ቴዲ፡ ቄሱንም፡ ፖስተሩንም፡ ሼኩን፡ ወጣት፡ አዛውንቱን፡ ባንድላይ፡ ሙዚቃ፡ እንዴት፡ ሀጢያት ይሆናል ? ብለው፡ እንዲጠይቁጰ ያረገ፡ ይመስለኛል፡፡
* ቴዲ፡ 100% አድናቂ፡ ቢኖረውም፡ ጠላቶችም፡ ያፈራ፡ ወንድ፡ ነው፡፡
* ቴዲ፡ የሚወደድም፡ የሚጠላም፡ ዘፋኝ፡ የለም፡፡
* የቴዲ፡ ቀንደኛ፡ ጠላቶች፡ ሰዎች፡ አይደሉም፡፡ * ቴዲን፡ መልኩን፡ አይተህ፡ የምትወደው፡ እንጂ፡ የምትጠላው፡ ሰው፡ አይደለም፡፡
* የቴዲን፡ ስራ፡ አይተህ፡ ግን፡ ወይ፡ ጠላቱ፡ ወይ፡ ወዳጁ፡ መሆን፡ ግድ፡ ይልሃል፡፡
* ስለቴዲ፡ መሀል፡ ሰፋሪ፡ መሆን፡ ይከብዳል፡፡
* ቴዲ፡ ገና፡ ብዙ፡ ሲወሳ፡ የሚኖር፡ ሰው፡ ነው፡፡
ባለማችን፡ በጣም፡ ትልልቅ፡ ዘፋኝ፡ ይኖሩ፡ ይሆናል፡ በደጋፊ፡ ቁጥር፡ በገንዘብ፡ በዝና፡ ከቴዲ፡ በላይ፡ የሚጠሩ፡ እመኑኝ፡በስራ፡ ግን፡ ምንአልባት፡ ቦብማርሊ፡ ካልሆነ፡ ማንም፡ አይደርስበትም፡፡
የትኛው፡ እውቅ፡ ዘፋኝ፡ ነው ፡ ኮንሰርት፡ እንዳያዘጋጅ፡ በሀገሩ፡ የሚከለከለው ??
እረ የቱ፡ ነው፡ ከሀገሩ፡ መንግስት፡ ጋር፡ ድብብቅ፡ የሚጫወተው ? ቢዮንሴ ? ሪሀና ? ባገራቸው፡ ጠ/ ሚኒስቴር፡ አዝማሪ/ አሚና፡ የተባሉት ?? የቱ ነው፡ መንግስትን፡ ስለወቀሰ፡ የታሰረው ??የቱ፡ ዘፋኝ፡ ነው፡፡ ዜማውን፡ ግጥሙን፡ ታሪኩን፡ ብቻውን፡ የሰራው? ስት ሰራ ??ይህ፡ ልጅ፡ የምቀናበት፡ እድለኛ፡ ፈተናዎች፡ ይበልጥ፡ ያጠነከሩት፡ ጀግና፡ ነው፡፡
ሀውልት፡ ወይም፡ መንገድ፡ ሊሰየምለት፡ የሚገባ፡ ሰው፡ ነው፡፡ ይሁንና፡ መንግስት፡ ስለማይወደው፡ ብቻ፡ በሀገሩ፡ መዝፈን፡ እንኳን፡ አልቻለም፡፡ በሰፊው፡ ህዝብ ፡ ልብ፡ ግን፡ ደምቆ፡ ገኖ፡ እየኖረ፡ ነው፡ ገና፡ ይኖራል፡፡ ምክንያቱም፡ ታሪክ፡ ሰርቷል፡፡ይህ፡ ነው ቴዲ፡፡
Filed in: Amharic