>

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከቻይና ለምን ተጠሩ? (ስዩም ተሾመ)

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ #ከቻይና ለምን ተጠሩ?
ስዩም ተሾመ
“በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር #ብርሃነ_ገብረክርስቶስ ወደ ሀገር ቤት ተጠሩ” ይላል የፋና ዘገባ፡፡ ፋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮችን ዋቢ በማድረግ “አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ሀገር ቤት የተጠሩበት ምክንያት ረዥም ዓመታትን በማገልገላቸው ነው” ሲል ዘግቧል። እኛም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሚገኙ ምንጮቻችን ጋር ስልክ በመደወል አምባሳደሩ የተጠሩበትን ምክንያት ለማጣራት ሙከራ አደረግን፡፡ በዚህ መሠረት ያገኘነው መረጃ ግን የተለየ ነው፡፡ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተጠሩበት ምክንያት “ረዥም” አመት በማገልገላቸው ሳይሆን ለረጅም ግዜ ስለ #አብዮታዊ_ዴሞክራሲ ዲስኩር በማሰማታቸው ነው፡፡ አምባሳደሩ ለትምህርት #ቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስብሰባ በመጥራት በ1993 ዓ.ም በመለስ ዜናዊ የተፃፈውን “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” የሚለውን የህወሓት “መፅሃፍ ቅዱስ” ይዘው “ኢትዮጲያ ውስጥ መንግስት ወደ ስልጣን የሚመጣው ሆነ ሀገር የሚመራው በዚህ ነው፡፡ “የሰውዬው” (ዶ/ር አብይ) አካሄድ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን መርህ ስለሚቃረን ልንቃወመው ይገባል” እያሉ ሲሰብኩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ በመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት ተጠቅመው ከቻይና መንግስት ሃላፊዎች ጋር በመገናኘት ቻይና በዶ/ር አብይ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፏን እንዳትሰጥ ቅስቀሳና ውትወታ ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም አምባሳደሩ የተጠሩበት ምክንያት ከኋላቀር የፖለቲካ አመለካከት ራሳቸውን ነፃ ማውጣት ስለተሳናቸው፣ በዚህም የሀገሪቱን ጥቅም ከማስከበር ይልቅ የህወሓትን የስልጣን ጥማት ማርካት በማስቀደማቸው ነው፡፡
አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ በጡረታ ተሰናበተ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
  በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ሀገር ቤት ተጠርቷል። በይፋም ገና አገሩ ሳይገባ በጡረታ እንደተሰናበተ ተገልፇል።
 በነገራችን ላይ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ  ለድርጅታዊ ስራ የሚውል የህውሃትን በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር   በስሙ አሜሪካ አገር ባንክ አስቀምጦ ይሄን ገንዘብ በግል አካውንቱ መግባቱን የምታውቅ ሚስቱ ፍች ጠይቃ  ከተቀመጠው ገንዘብ ግማሹን  መዛቋ ይታወሳል። መለስ ዜናዊም የብርሃነን ሚስት በማግባባት የድርጅት ገንዘብ እንደሆነ በማስረዳት ዶላሩን ለማስመለስ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካ የአንድ ሰሞን መነጋገሪያ ነበር።  የብርሃነ ገብረክርስቶስ ሚስት ይሄን ያደረገችው ብረሃነ በወቅቱ ከበፊቷ የመንግስት ቃለአቀባይ ሰሎሜ ታደሰ ጋር  በነበረው በነበረው የፍቅር ግንኙነት ቆሽቷ በማረሩ ነበር።
በነገራችን ላይ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የመለስ ዜናዊ እጅግ ታማኝ ፣ሚስጥረኛና የመለስን የመጨረሻ እጣ ፈንታ ከሚያውቁ በጣም ጥቂት ሰዎች አንዱ ነበር።
Filed in: Amharic