>

ሊፈተሽ የሚገባው የይቅርታ ስርአት!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

ሊፈተሽ የሚገባው የይቅርታ ስርአት!!!  
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
እነኝህ በቅሊንጦ ያሉ በደረቅ ወንጀል የታሰሩ እስረኞች (ታራሚዎች) “ይቅርታው እኛንም ይመለከታልና ፍቱን!” ሲሉ መጠየቃቸውንና “እናንተን አይመለከትም!” የሚል መልስ ከእስር ቤቱ ኃላፊዎች እንደተሰጣቸው ከብዙኃን መገናኛ ሰምተናል፡፡
ሲጀመር የእስር ቤቱ ኃላፊዎች የታሳሪዎችን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንጅ ለእስረኞቹ ጥያቄ መልስ የመስጠት ሥልጣንና ኃላፊነት የላቸውም፡፡
ሲቀጥል ይቅርታው ደረቅ ወንጀለኞችንም ይመለከታል ብለው ነውና እንደ እነ ገብረዋሕድን የሚያካክሉ በሙስና የታሰሩትን ከባባድ ደረቅ ወንጀለኞችን ከሕሊና ወይም ከፖለቲካ እስረኞች ጋር የፈቷቸው ይሄ ከሆነ የቅሊንጦ እስረኞች “ይቅርታው እኛንም ይመለከታልና ፍቱን! ድሃ ስለሆንን ዘመድ ስለሌለን ነው ወይ የማንፈታው? እባካቹህ የድሃ ልጆች ነን ፍቱንና ሠርተን እንብላበት?” ብለው መጠየቃቸውና ማመፃቸው ትክክልና ሊደገፍም የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
እነ ዐቢይ “ይቅርታው ደረቅ ወንጀለኛን አይመለከትም!” ካሉ ወንጀለኝነታቸው በበርካታ ማስረጃዎች የተረጋገጠባቸውን እነ ገብረዋሕድና ማነው ደሞ ያ የኢትዮጵያ አውራ መንገዶች ሥራ ድርጅት ኃላፊው እነሱ የተፈቱት በስሕተት ነውና እነዚህ ግለሰቦችን መልሰው በማሰር የሕግ የበላይነትንና እኩልነትን ያረጋግጡ???
ይሄ የሕግ የበላይነትንና በሕግ ፊት ሁሉም እኩል መሆኑን የማረጋገጡ ሥራም ሌሎቹን “ማን ይነካናል?” ብለው በነጻነት እየፏለሉ ያሉ ወንጀለኛ የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናትንም ተጠያቂ በማድረግ ይረጋገጥ???
ካልሆነ ግን እስረኞቹ እያሉ እንዳሉት ሁሉ ዝምድናና ገንዘብ እንጅ ፍትሕና እኩልነት እየሠራ አይደለምና ትግላችን ይፏፏም!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic