>

እነሆ ከ27 ዓመታት በኋላ ... (ዘመድኩን በቀለ)

እነሆ ከ27 ዓመታት በኋላ
ህውሓት ወንበር ተነፈገች፣ ዐማራ ተፈነገለ
ሻአቢያና ኦህዴድ/ ኦነግም በይፋ ተጋብተዋል
                    
ዘመድኩን በቀለ
~ እኔ በእኔ መነጽር የማየውን ብቻ ነው የምጽፈው። ስለ ሌሎቻችሁ አያገባኝም። ይኸው ነው። ከመንጋው ጋር እንድንበጫበጭ አትጠብቁ። እውነቴን እጽፋለሁ። ለታሪክም ይቀመጥልኛል። አዳሜ ስታላዝን ውለህ ብታድር እኔ ዘመዴ ወይ ፍንክች። ኬሬዳሽ ።
~ አንቺ ተአምረኛ የሆንሽ ሀገር ሆይ እንደምን ውለሽ አድረሽልኛል። መቼም አንቺ አታሳዪን አታመጪው ነገር የለም። አጃኢብ እኮ ነው።
~ ከ27 ዓመት በኋላ ዛሬ በአዲስ አበባ እንዲህ ሆነ።
ህውሓትን ጠፍጥፎ የሠራውና ዳይፐር እየቀየረ አሳድጎ በጫንቃው ተሸክሞ ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ያስገባው ሻአቢያ በህውሓት በኩል ደሟን ሊመጣት የነበረችውን ኢትዮጵያን እንደተመኘው ማድረግ አልቻለም ነበር። ኤርትራውያን ለትግራይ ያላቸውን ንቀት መቼም ብንደብቀውም የማይደበቅ መሆኑ ይታወቃል። ወዛደር፣ ኩሊ ነው ይሉታል ኤርትራውያን የትግራይን ህዝብ። ንቀታቸው እዚህ ድረስ ነው። የኤርትራን በለስ ለመልቀም የሚመጣ ረሃብተኛም ነው ይሉታል ኤሪዎቹ። ከምር ይጠየፉዋቸዋል አይገልጸውም።
~ ታዲያ ይሄን የሚያውቁ በህውሓት ውስጥ ኤርትራዊ ደም የሌላቸው ታጋዮች ኢትዮጵያን ዘርፈን ትግራይን አሳድገን ከኤርትራውያን እኩል መሆን አለብን። እነሱ ጣልያን በሠራት አስመራ እኛን ሲያበሻቅጡን መኖር የለባቸውም ብለው አንጃ ፈጠሩና እንደልቧ ኢትዮጵያን እየዘረፈች የነበረችውን ኤርትራን ጉሮሮዋ ላይ ቆመው የደም ስሯን ዘጉት። ከዚያም ብቻቸውን ኢትዮጵያን ጠቅልለው ወተቷ የማይነጥፈን ላም ማለብ ጀመሩ። ኤርትራውያኑ አበዱ። በባድመ ሰበብ ጦርነት ከፈቱ። ህውሓት ሆዬ ዐማራና ኦሮሞን ፈንጅ አምካኝ አድርጋ ሻአቢያን አይቀጡ ቅጣት ቀጥታ ባዶ እጁን አስቀረችው።
~ ህውሓትም ብቻዋን ኢትዮጵያን ዘረፈች። የትግራይ ምድር ኧረ ኡኡኡ ወገቤ ጎበጠ እስክትል በፋብሪካና በመሰረተ ልማት አጨናነቀችው። ዐማራ አፈር ከድሜ ጋጠ። ሱማሌ እንኳ ከዘላኑ ኅብረተሰብ ካዝና ሽጉጥ እየተደቀነበት ለትግራይ እንዲገብር ተደረገ። ዐማራ በጀቱን መጠቀም ስላልቻለ ለትግራይ እንዲሰጥ በእነ በረከት ተገደደ። ትግራይ የአፍሪካ ቀንድ አውሮፓዊት ከተማ መሰለች። እነ ኢሳይያስም አበዱ ። አበዱ አይገልጸውም። እንዲያውም አይተ ኢሳይያስ በአንድ ጊዜ ቃለመጠይቃቸው እንዲህ ብለው ነበር። ” እኛ ትልቁን ስህተት የሠራነው ወያኔን አምነን ኢትዮጵያን መስጠታችን ነበር። ያን ጊዜ ለኦነግ ብንሰጠው ኖሮ እንዲህ አንቆጭም ነበር በማለት ነበር እየተብሰከሰኩ የተናገሩት።
~ እነሆ ከ27 ዓመታት በኋላ አይተ ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚፈልጉት ኦህዴድ/ኦነግ የኢትዮጵያን መንበረ መንግሥት ተረክቧል። ህውሓትም አድፍጣ ይሁን ተወቅጣ ባይታወቅም ለጊዜው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ገሸሽ ተደርጋለች እናም ሻአቢያ ጊዜው አሁን ነው በማለት ጥርሱን አግጥጦ ፣ ጥፍሩንም አሹሎ ፍጥጥ ብሎ ከች ብሏል።
~ አንድ እግር ቡና የሌላት ኤርትሪያ ከኢትዮጵያ ደቡብ ይርጋ ጨፌ በነፃ ትቃርም በነበረው የኢትዮጵያ ቡና በዓለም የቡና ላኪዎች የደረጃ ሰንጠረዥ የ4ተኝነት ደረጃ የሚያሰጣትን ማእረግ እስክታገኝ ድረስ ስሟ መጠራቱ ይታወሳል። እነሆ ዛሬም አይተ ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ በቀጥታ ያመሩት ወደ ደቡብ ነበር። በዚያም የናፈቁትን የይርጋ ጨፌ ቡና ለሚስታቸው ጭምር ተሸልመው ሲፈነድቁ ታይቷል።
~ የሀገሪቱ የጦር መሪ ሜጀር ጀነራሉ አይተ ሰኣረ፣ የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት ዶር ደብረ ጽዮን፣ የህውሓቱ አይተ አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ ግን በአቶ ኢሳይያስ የግብዣ ሥነሥርዓት ላይ ቢገኙም የሚገባቸውን ክብር ሳያገኙ ወንበር አጥተው በኤርትራውያኑ ፊት መሳቂያ ተደርገው መዋላቸው ተነግሯል። 27 ዓመት ሙሉ ሲያዙበት በነበረው ቤተመንግሥት ሻአቢያና ኦነግ በይፋ የጋብቻ ሥነሥርዓት ፈጽመዋል። አከተመ ።
የብአዴኑን አቶ ገዱን የክብር ዶክትሬትህን ውሰድ በማለት ወደ ሀረር ልከው እነሱ የፍንጥር ውስኪም፣ ቡናም ሲራጩ አምሽተዋል።
~ በድኑ ብአዴን ከባህርዳር እንዳይወጣ በስብሰባ ጠርንፈው ሽባ አድርገው አስቀምጠውታል። አቶ ገዱ ቤተመንግሥት የሆነች ቦታ ላይ ብቅ ብለው ከመታየታቸው በቀር ወፍ የለም። በፈረንሳይኛ ሂድ ንካው ተብለዋል።
~ ህውሓት አንጀቴን በልታኛለች። ዐማራው ግን ይበለው። በቶሎ ካልነቃ ገና ለ3ተኛ ጊዜ የመከራ ቋቱን ይሸከማታል። ለማንኛውም መሃል ሀገሩ በጭፈራ ደርቷል። ዳር ሃገሩ ሞት በርክቷል። ስትጮህ ውለህ ብታድር የሚሰማህ አንዳች ኃይል የለም።
~ አብዲ ኢሌ በምስራቅ ኢትዮጵያና በባሌ የኦሮሞን ልጆች አርዶ ይበላል። በአዲስ አበባ ደግሞ ዋነኛው የመደመር ቀመር አቀንቃኝ ሆኖ ይታያል። እንዲያውም አዋሳ ድረስ ግመል ጭኖ በማምጣት ለኢሳይያስ አፈወርቂ ሲሸልም ታይቷል። ጨዋታው ቀጥሏል።
~ በአዲስ አበባ ዛሬ ሰልፍ የወጡት አብዛኛዎቹ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያንና ህውሓትን ማብሸቅ የሚፈልጉ የሸገር አራዶች ናቸው። እነዚህ ሰልፈኞች በቦሌ ደረታቸውን እየደቁ ዋይ ዋይ ተለያየን ሲሉ ታይተዋል። ቤተመንግሥት ሲደርሱም ከመለስ ፎቶ ስር ቆመው ” ነፍስህን አይማረው። ዘረኛ፣ ሌባ ” ሲሉ ተደምጠዋል። በቪድዮም ተቀርጸዋል።
~ የአዲስ አበባ ህዝብ ቅኔ ሀሆነ ህዝብ ነው። ከባድ ህልም የሆነ ህዝብ ነው። ፈቺ የሚያስፈልገው ህዝብ። 17 ዓመታት ሙሉ መስከረም 2 በመጣ ቁጥር ከጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም አመራር ጋር ወደፊት ሲል የከረመ ጉደኛ ህዝብ ነው። መስከረም ላይ ወያኔ ትውደም ሲል ከርሞ ግንቦት ላይ ወያኔን ቄጤማ ጎዝጉዞ የተቀበለ ጉደኛ ህዝብ ነው። የአዱ ገነር ህዝብ 27 ዓመታት በሙሉ መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው ሲል የከረመ ባለ ቅኔ ህዝብ ነው። ሚያዚያ 29ለኢህአዴግ ፣ ሚያዚያ 30 ለቅንጅት ግልብጥ ብሎ አደባባይ ወጥቶ አይዟችሁ ብሎ ለሁለቱም ሞራል የሰጠ ህዝብ ነው።
~ የአዲስ አበባ ህዝብ በጥይት ለረፈረፈው መለስ ዜናዊ ለምን ሞትክብን ብሎ ደረቱን እየደቃ ፣ ፀጉሩን እየነጨ አልቅሶ ባዶ ሳጥን የቀበረም ኮሚክ ህዝብ ነው። 120 ሺ ወገኑን በባድመ ሰበብ የፈጀበትን ኢሳይያስን ሲያወግዝ ኖሮ ዛሬ ደግሞ አደባባይ ወጥቶ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ቆማ ማየት ለማይፈልገውን ሻአቢያን ተንበርክኮ አልቅሶ እየሰገደ ሲያስተናግድ የታየ ደብል ፌስ የሆነ ሰምና ወርቅ ቅብ ህዝብ ነው። አዱ ገነት ጣጣ አላት እንዴ? መንጌን ትናፍቃለች። መለስ ዳግም ቢነሳም ነጠላዋን፣ ጃኬቷንም አንጥፋ ትቀበለዋለች። ያውም እያለቀሰች።
~ ለማንኛውም እኔ ዛሬ !  ህውሓት አሳዝናኛለች ። በኢሳይያስ ፊት መቀመጫ ነፍገው በቁሟ አንከራትተው በማሳቀቅ የሌለ ግፍ ፈጽመውባት አሳዝናኛለች። አህታችኋል ወንበር የያዙት እንዴት ተሳቅቀው እንደሚያዩዋቸው። አሁን ማንን አስነስተው ሊያስቀምጧቸው ነው በማርያም። አሁን ደግሞ እንደድሮው ደንግጦ የሚነሳም ያለ አይመስለኝም። ብቻ ፈጣሪ ይሁነን።
መልካም ጋብቻ ብያለሁ ለኦህዴድ/ኦነግና ለሻአቢያ።
ዐማራ ግን ንቃ !  ወጥር ብዬሃለሁ። ተጠራራራ፣ ተመካከር፣ ተወያይ፣ ተሰባሰብ፣ ተደራጅ። ነግሬሃለሁ ። ብልጥ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚሞኘው። ለ2ተኛ ጊዜ ከተሞኘ ጥፋቱ የራሱ ብቻ ነው የሚሆነው።
~ የለውጡ እንቅፋት እንዳትሆን። ለውጡን ግን በጥንቃቄ ተመልከተው። አከተመ።
ሻሎም !  ሰላም 
Filed in: Amharic