>

አስቸኳይ ሕዝበ ውሳኔ በአዲስ አበባ  ከተማ ላይ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

አስቸኳይ ሕዝበ ውሳኔ በአዲስ አበባ
 ከተማ ላይ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
ከ12 ዓመታት በፊት በተደረገ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች በብሔረሰብ፣ በሃይማኖትና በቋንቋ እንዲህ አስቀምጧቸዋል፦
የብሔረሰብ ስብጥሩ፦
* አማራ 56.04%
*ኦሮሞ 19%
*ጉራጌ 16.34%
*ትግሬ 5.18%
*ስልጤ 2.94%
*ቀሪዎቹ 0.5% ነው ይላል፡፡
የሃይማኖት ስብጥር ደግሞ፦
* ኦርቶዶክስ 74.7%
* እስላም 16.2%
* ፕሮቴስታንት 7.77%
* ካቶሊክ 0.48%
* ሌሎች 0.85 መሆኑን ይናገራል፡፡
የቋንቋ ስብጥሩን ሲገልጽ ደግሞ፦
* አማርኛ ተናጋሪ 71%
* ኦሮምኛ ተናጋሪ 10.7%
*ጉራጊኛ ተናጋሪ 8.37%
* ትግርኛ ተናጋሪ 3.6%
* ሌሎች 6.33 እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡
የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር በአዲስ አበባ ከ19% የማይበልጥ መሆኑ የአዲስ አበባን ፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) ለመጫወት እንደማያስችል የገባው ኦሕዴድ ይሄንን አኀዝ ለመለወጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት በቀደም ለታ “ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን!” ያላቸውን በመንግሥት ወጭ የጋራ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) በመገንባት በአዲስ አበባ ለማስፈር ለቤት ግንባታ ዝግጅት መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ይሄንን ሥራ ይፋ ባደረጉ ማግስት ዐቢይ ይሄን ጉዳይ የሚያስፈፅም ሰው ዛሬ በምክትል ከንቲባነት የከንቲባ ሥልጣን ሰጥቶ ሾሟል። ይሄ አዲሱ ከንቲባ በአዲስ አበባ ለኦሮሞ ተወላጆች ልዩ ጥቅም ሲከራከር የነበረ ሰው በመሆኑ የተጣለጠትን አደራ በብቃት ይወጣል ተብሎ ታምኖበታል።
ዐቢይና ለማ የሚከተሉት አስተሳሰብ “ሁሉም ዜጋ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እኩል እንዲታዩ ማድረግ፣ ክልላችን ምንትስ ማለትንና ከሌላ ክልል የመጣውን ዜጋ እንደባዕድ የሚቆጠርበትን ጠባብ አሠራር ማስቀረት፣ የክልል መለያ መስመሮች የአሥተዳደር ወሰኖች ናቸው እንጅ የሀገር ድንበሮች አይደሉምና ወሰኖች እንደድንበር የሚታዩበትን አመለካከት ማስቀረት….!” የሚል እንደሆነ ሲነግሩን ሰንብተው ነበረ፡፡ ዓላማቸው ይሄ ከሆነ ለኦሮሞ ተወላጆች ለይተው አዲስ አበባ ላይ ቤት የሚገነቡበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም ነበረ፡፡ አስተሳሰባቸው ዜጎችን በዜግነታቸው እኩል የሚመለከት ከሆነ በዚህ በቤት ግንባታው አማራ ተፈናቃዮችንም ማካተት ነበረባቸውና ነው፡፡
ይሁንና ቀደም ሲል ከላይ የገለጽኩትን ሲናገሩት የነበሩት ለሽንገላ እንጅ ስለሚያምኑበት አልነበረምና ቀደም ሲል ሲነግሩን የነበሩትን ትተው “በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ተወላጆች ልዩ ጥቅም!” የሚል አጀንዳ (ርእሰ ጉዳይ) አንሥተው ያንኑ ሲያወግዙት የነበሩትን ጉዳይ ለማስፈጸም መንቀሳቀስ መጀመራቸውን  እያየን ነው፡፡ ፍላጎታቸው ይሄ ከሆነ አማራ ከንቲባ ቢሾምስ ይሄንን የኦሕዴድን አጀንዳ በአማራ እጅ በማስፈጸም ከአማራ ተቃውሞ ለማምለጥ ካልሆነ በስተቀር አማራ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት መሾሙ ፋይዳው ምንድን ነበር ታዲያ???
አዳሜ ዐቢይ “መደመር፣ አንድነት፣ እኩልነት፣ ኢትዮጵያ!” ምንትስ እያለ እያጃጃለ ሥራውን ሲሠራልሽ “ሞኝና ወረቀት ያሲያዙትን አይለቅም!” እንዲሉ አንች አሁንም መደመር መደመር እያልክ ትጃጃይልኛለሽ!!!
ወገኖቸ የነ ዐቢይ አካሔድ ይሄ ከሆነ 56.04% የአዲስ አበባ ነዋሪ አማራ ነውና የአዲስ አበባን የልዩ ዞን ጥያቄ አንሥተን የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ እንዲሰጥ እንዲደረግልን በመጠየቅ እንደ አሠራራቸው አዲስ አበባን ኦሮሞያ በሚሉት ክልል የአማራ ዞን መሆኗ እንዲረጋገጥ መንቀሳቀስ ይኖርብናልና በሉ ጎበዝ ማንቀላፋቱ ይብቃና ለዚህ እንንቀሳቀስ???
ይሄ የዞን ጥያቄ ከተነሣ እንደሚታወቀው የአማራ ክልል በሚሉት ኦሮሚያ ክልል ለሚሉት ዞን ተሰጥቷቸው ለኦሮሞ ተወላጆች የአማራ ክልል በሚሉት በቋንቋቸው ከመጠቀም፣ ከመማር፣ ከመዳኘት ጀምሮ እራሳቸውን በራሳቸው የማሥተዳደር መብቶቻቸው ለአንድ ቀን ሳይስተጓጎል ተጠብቆላቸው እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡
በአንጻሩ ግን እነሱ ኦሮሚያ ክልል በሚሉት አማሮች በብዛት ወይም ሙሉ ለሙሉ ብቻቸውን ባሉባቸው አካባቢዎች ይህ ሕገመንግሥታዊ መብት ለአንድም ቀን ሳይከበር ዜጎች ሙሉ 27 ዓመታት በስቃይ መኖራቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ የሚለው የወያኔ አሕዮች ቡድን ብአዴንም የወያኔ ወኪል እንጅ የአማራ ሕዝብ ወኪል ባለመሆኑ ይሄ ግፍ ሲፈጸም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አንድም ያደረገው ነገር የለም፡፡ ጭራሽ እንዲያውም ትንሽም ሳያፍር “ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ አማሮች ጉዳይ አይመለከተኝም!” በማለት እንደነ ታምራት ላይኔ ባሉ አመራርሮቹ በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ያሉ አማሮችን ሲያስፈጀን የኖረና በእኛ ላይ የጠላት ጉዳይ አስፈጻሚ ቡድን ሆኖ የኖረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ዐቢይና ለማ ከላይ የገለጽኩትን የጎሳ ፌዴራሊዝም (የራስገዝ) የአሥተዳደር ሥርዓት የሚሰጠውን መብት እየተቃወሙና እያወገዙ እንደመምጣታቸው መጠን የጎሳ ፌዴራሊዝም (የራስገዝ) የአሥተዳደር ሥርዓት እንዲቀጥል የሚፈልጉ ባይመስሉም እንዲቀጥል የሚያደርጉ ከሆነ ግን አማሮች ኦሮሚያ በሚሉት የሀገራችን ክፍል በብዛት ወይም ሙሉ ለሙሉ ባሉባቸው ቦታዎች ለኦሮሞዎች የአማራ ክልል በሚሉት እንደተሰጣቸው መብት ኦሮሚያ በሚሉትም ለአማሮች የዞን መብት በመስጠት ለ27 ዓመታት የነበረውን ኢፍትሐዊ አሠራር ያስተካክላሉ የሚል ተስፋ ሰንቀን ነበር፡፡ ተስፋው ባዶ ቅዠት ሆነና እንደምታዩዋቸው ጭራሽ ሌላ ግፍ ለመጨመር በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡
እንግዳውስ እውነቱ ይሄ ከሆነ ዘንዳ እነሱ ትናንት መጥተው በወረራ የሰፈሩባትን የትናንቷን ከተማችንን በራራን (ጠብቆ ይነበብ) ወይም የዛሬዋን አዲስ አበባን “የኛ ነው!” ብለው የተለየ መብት ለራሳቸው የመስጠት እፍረተቢስ ድፍረትን ለመፈጸም ከተንቀሳቀሱ እኛ ባለ ሀገሮቹ፣ ባለ ርስቶቹ፣ ባለ መሬቶቹ አርፈን በመቀመጥ ርስታችንን፣ መሬታችንን አስወርሰን እንደ መጻተኛ፣ እንደ ሰፋሪ የምንቆጠርበት አንድም ምክንያት የለምና ወገን ሆይ! ለመብትህ ቆርጠህ ተነሥ!!! ዝምታህ፣ ታጋሽነትህ፣ ቻይነትህ፣ ይሉኝታህ ባዶ አስቀረህ እንጅ ፈጽሞ አልጠቀመህምና ይብቃህ!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic