>

አቶ ስብሀትነጋ "ኢፈርት የአክሲዮን ሽያጭ ያድርግ"በሚለው አጀንዳ ባለመስማማት ረግጠው ወጡ (አስገደ ገብረስላሴ)

አቶ ስብሀትነጋ “ኢፈርት የአክሲዮን ሽያጭ ያድርግ”በሚለው አጀንዳ ባለመስማማት ረግጠው ወጡ
ከአስገደ ገብረስላሴ 
አቶ #ስብሀትነጋ የ #ኢፈርት ሀብት የትግራይ ህዝብ በአክስዮን ባለቤትነት ይያዝ  በሚል አጀንዳ    የማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባ ረግጦ ወጣ!!!
በመቀለ ከተማ በትግራይ ክልል ርእሰከተማ በስልጣን ያለው የህወሓት ማ /ኮ እና በተለያዬ ምክንያት በጡሮታ ፣በብቃት ማነስ ፣በሙሱና  ወዘተ ተሰናብተው የነበሩ  ቡዱኖች ተሰብስበው ኤፈርት በማን ባለቤትነት ይያዝ የሚል አጀንዳ በዶክተር #ደብረጽዮን ቀርቦ  ሲያበቃ ቤቱ ለሁለት ተካፋፈለ ።
    1 ኛ . የዶክተር ደብረጽዮን ቡዱን የኢፈርት ደርጅቶች እስከ ኣሁን የሀሜት ምንጭ ሆነው ስለቆዩ ለወደፊት ባለው ጥሬ ገንዘብ የተቸገሩ አካል ጉዳቶኞችና የተዳከሙ ያለኣንዳች ድጎማ የተባረሩ  ደካማ ታጋይ ነበር እናቋቁምበት ።
2ኛ የቀረው ሀብት ግን በኣክስዮን ሸር በባለቤትነት በህዝብ እጅ  ሆነው  ትርፉ በየአመቱ ኦዲት እየተደረገ ሌላ ተቃማት እየፈጠረ  የትግራይ ህዝብ መሆኑ በህግ እናስረክበው በነዚ ድርጅቶች የህዋሓት ማ/ኮሚቴ እጁ ማስገባት የለበትም ሲሉ
የ #ነስብሀት ነጋ ቡዱን እነ #ኣባይጸሃዬ ፣ #ስዩምመስፈን ስብሀት ነጋና ተከታዮቻቸው ግን የኤፈርት ሀብት   በማናቸውም መስፈርት የትግራይ ህዝብ ሀብት አይደሉም በማለት ደረቅ ኣቋም በመያዝ ይህ  ሀብት የህወሓት ማክላይ ኮሚትቴ ነው ብለዋል ።
በመጨረሻ እነደኩተር ደብረጽዮን የኤፈርት ተቃቋማትና  ባገር ውስጥም በማናቸውም ቦታ ይኑር የኢፈርት ባለቤትነት ነበር ፣ ለወደፊትም በህዝብ የአክስዮን ሸር ባለቤትነት ሊሆን ነው  ብለው ኣቋም ሲወስዱ ፣
      ኣቶ ስብሀት ነጋ  ግን እንግዳውስ  ተቋሟቱ ወደ የህዝብ ባለቤትነት ይሁኑ ካላቹሁ በእኔ ስም የሚታወቅ እጅግ ቡዙ ሚሊን የሚገመት ከንዘብ  በእኔ ስም  ኣለኝ ለእናንተ ኣላስረክብም  የራሴ ሀብት ነው በማለት ስብሰባ ረግጦ እንደወጣና ስብሰባው ተበትኖ እንዳልተሳካ ከህወሓት መንደር ምንጮች ጠቁመዋል ።
በተጨማሪ ደብሰጽዮን ቡዱን የተናደዱ መሆናቸው ታውቀዋል ።
                         መቀለ
                 12 / 11 /20 10
Filed in: Amharic