>

አስቸኳይና ጥብቅ መልእክት ለስደተኛው ሲኖዶስና ለመለካውያኑ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

አስቸኳይና ጥብቅ መልእክት ለስደተኛው ሲኖዶስና ለመለካውያኑ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
* ወይ ጉድ ካድሬነት (ወስዋሽነት) ቤተክርስቲያንን በጠበጠ እኮ ምእመናን!!!
መለካውያኑ (የአገዛዙ ቅጥረኞች) የጥፋት ተልእኳቸውን ለመፈጸም፣ የቅጥረኝነታቸውን ተግባር ለመወጣት የሚያስችል መንገድ ቢያጡ ደሞ “እንደራሴ” የሚል ቃል አምጥተው እያወኩ ይገኛሉ፡፡
የእንደራሴነት ተግባር ቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ አለው እንዴ ደግሞ??? የእንደራሴነት አገልግሎት በቤተክርስቲያን ውስጥ ጨርሶ የለም!!! መንፈሳዊ አገለግሎትንና መንፈሳዊ ሥልጣንን የሚጻረር ለቤተክርስቲያን ባዕድ የሆነ አስተሳሰብ ነው፡፡ ካድሬዎቹ መለካውያን ይሄ ስለማይገባቸውና ስለማያውቁትም ነው እንደራሴ እንደራሴ እያሉ ያሉት፡፡ እንደራሴነት የሚያገለግለው መንፈሳዊ ሥልጣን በሌለበት በመንግሥት ሥራ ላይ ብቻ ነው፡፡
ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ሕግ መሠረት የፓትርያርኩን መንፈሳዊ ተልእኮና አገለግሎት ጳጳሱ፣ የጳጳሱን ኤጲስ ቆጶሱ፣ የኤጲስ ቆጶሱን ቆሞሱ፣ የቆሞሱን ቄሱ፣ የቄሱን ዲያቆኑ፣ የዲያቆኑን አናጎኒስጢሱ፣ የአናጉንስጢሱን ምእመኑ መሥራት ስለማይችልና ፈጽሞ የተከለከለ መንፈሳዊ ሥልጣንን የሚፃረር ስለሆነ ነው፡፡
መለካውያኑ ወይም የወያኔ ቅጥረኞች ቅዱስ ፓትርያርኩን ቤተክርስቲያን ወይም ክርስቶስ ከጣለባቸው አደራና ተልእኮ በማቀብ በበዓታቸው ዘግተውባቸው በጸሎትና በቡራኬ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ ለማድረግ፣ አቦይ ማትያስና መዝባሪ ጠንቀኛ የወያኔ ጭፍራ ቡድናቸው ደግሞ የቤተክርስቲያኗን አሥተዳደር በእንደራሴነት ይዘው እስከዛሬ በቤተክርስቲያን ላይ ሲያደርሱ የነበሩትን ወደር የለሽ አረማዊ ጥፋት መፈጸማቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ በዚህ እንዲስማማ ስደተኛውን ሲኖዶስ ለማሳመን ጥረታቸውን እንደተያያዙት እየተሰማ ነው፡፡ አያሳዝንም??? እጅግ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው!!!
ቆይ ለምንድ ነው እሱ ቅዱስ ፓትርያርኩ የአሥተዳደር ሥራቸውን እንዳይሠሩ የሚፈለገውና የሚከለከሉት??? አሁንም ቤተክርስቲያን ከአገዛዙ ጣልቃገብነትና ጫና ነጻ ሆና ቀኖና ቤተክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ሥራዋን የማትሠራ ከሆነ በስደት ላይ ያለው ሲኖዶሷ ሀገርቤት መግባቱ ጥቅሙ ምንድን ነው???
ይሄ ቤተክርስቲያንን ከቀኖናዋ ውጭ ያደረጋት የወያኔ ጫናና ጣልቃገብነት ተወግዶ ቤተክርስቲያን ያለ ማንም አሉታዊ ጣልቃገብነት ቀኖናዋ በሚያዛት መሠረት ሐዋርያዊ ተልእኮዋን እንድትወጣ መታገል መጣር ይኖርብናል እንጅ ፈጽሞ አግባብነት ለሌለው አረማዊ አገዛዝ ጣልቃገብነት ዛሬም እጅ ሰጥተን ቤተክርስቲያን ከቀኖናዋ ውጭ በሆነ መንገድ እንድትጓዝና ኢፍትሐዊነትና ግፍ የበዛበት አሠራር እንዲቀጥል መተባበሩ ከቶ ኦንዴት ሆኖ ነው ከኛ የሚጠበቀውና ይሄም ተግባር አስታራቂነት ሊሆን የሚችለው???
ይሄ እንዲሆን የሚፈልግና በዚህም ወያኔን የሚተባበር ሰውስ እንዴት ሆኖ ነው እኔ ጳጳስ ነኝ፣ ቄስ ነኝ፣ መነኩሴ ነኝ፣ ዲያቆን ነኝ፣ ምእመን ነኝ ሊል የሚችለው??? ኧረ ተዉ ኧረ ተዉ የእስከዛሬው ይብቃንና ቀሪ ዘመናችን እንኳ ትክክለኛ አቋም ይዘን ትክክለኛ ሥራ እንሥበት??? ተዉ ተዉ ተዉ???
ዘለዓለም የግል ጥቅማችንን እንዳሳደድን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአላዊው ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ ታዛዥ እንደሆንን ማለፍ አለብን እንዴ??? ተዉ ተዉ ተዉ??? እውነት በእግዚአብሔር የምናምንና ነገ በፊቱ ለፍርድ እንደምንቀርብ የምናምን ከሆነ ይሄንን እምነታችንን በሥራ እንግለጥ!!!
ተዉ ተዉ ተዉ??? እግዚአብሔርን አንፈታተነው ተዉ ተዉ ተዉ??? እናንተ ከሠለስቱ ምዕት በልጣቹህ ነው ወይ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ጥሳቹህ ከቀኖና ውጭ የሆነ ሥራ በቤተክርስቲያን ስም ለመፈጸም የምትደፍሩት??? ይሄንን ስታደርጉ እየተፈተናቹህና በፈተናውም እየወደቃቹህ እንደሆነ እንዴት አይገባቹህም??? እንዴት ቀኖና ቤተክርስቲያን በመሻር እንታረቅ ይባላል??? ለምንና ለማንስ ተብሎ ነው ይሄ የሚደረገው??? እያጠፉ፣ እየቀጠፉ፣ እያፈረሱ፣ እየተፃረሩ፣ እየተቃወሙ፣ እየሻሩ እግዚአብሔርን ማስደሰት፣ ቤተክርስቲያንን መጥቀም ይቻላል ወይ ልበ ደንዳኖች??? ኧረ ተዉ ተዉ ተዉ ድፍረታቹህን በልክ በቅጡ አድርጉት ተዉ በኋላ ለራሳቹህ ይብስባቹሃል ተዉ???
በዚህ በእርጅና በሽምግልና ዘመናቹህ ልባቹህን እንደ ጥቁር ድንጋይ አደንድናቹህ ራሳቹህን ዐመፃ በመፈጸም ከጠመዳቹህ መቸ እንደፈቃዱ ልትኖሩ ነው??? ኧረ ተዉ ኧረ ተዉ አድቡ ልብ ግዙ ተዉ??? ሕዝበ ክርስቲያኑ “ለዚህ መከፋፈል የዳረገንን የቤተክርስቲያንን ችግር ቀርፋቹህ ሰላም ፍጠሩልን፣ አንድነታችንን መልሱልን!” አለ እንጅ የቅጥረኛ ሥራቹህን አጧጡፉልን አለ እንዴ???
እንዲህ ስታደርጉ በመኖራቹህ ቤተክርስቲያን ለታላቅ ውድቀት፣ እጅግ ለሚያሳዝን ኪሳራ፣ ለማያላውስ ስብራት፣ አንገት ለሚያስደፋ ውርደት መዳረጓ እንዴት በዚህ ጊዜ እንኳ አያሳዝናቹህም??? እንዴት አይሰማቹህም??? ባለዕዳዎቹ እናንተው መሆናቹህ እንዴት አይታወቃቹህም???
የሚጸጽታቹህ፣ የሚታወቃቹህ፣ የሚሰማቹህ ቢሆንማ ኖሮ “አሁንስ በቃ!” ብላቹህ ቤተክርስቲያንን የሚያውካትን የጥፋት ኃይል ለመዋጋት “በአንድ ግንባር እንሰለፍና አጽራረ ቤተክርስቲያንን እንዋጋ!” ትሉ ነበረ እንጅ ዛሬም ይሄንን ሁሉ ኪሳራ፣ ውድቀት፣ ውርደት፣ ስብራት ላደረሰባት አገዛዝ አድራቹህ ቤተክርስቲያንን “ከቀኖናዋ ውጭ ካልተራመደች፣ ካልሠራች ሞተን እንገኛለን!” ብላቹህ ድርቅ ትሉ ነበረ ወይ??? አሁን እናንተን ምን እንበላቹህ??? እናንተን የሚገልጽ ምን ቃልስ ሊገኝ ይችላል???
በእውነት እንዲህ የናቃቹህት፣ የተዳፈራቹህት፣ ያዋረዳቹህት የቅድስት ድንግል ጽዮን ማርያም ልጅ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንጦርጦስ፣ እመቀመቃት የዘለዓለም እሳት አውርዶ ያቃጥላቹሃ ሌላ ምን ይባላል???
ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ በስደት ያላቹህት በግፍ የተሰደደው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አባቶች ሆይ! እባካቹህ ስለ እግዚአብሔር ብላቹህ በእነኝህ አሳቾች እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ??? እስከዛሬ ጸንታቹህ ጸንታቹህ መጨረሻው ሲደርስ እንዳትወድቁና ዋጋ እንዳታጡ በእጅጉ ተጠንቀቁ!!!
በምንም ተአምር ቢሆን ቀኖና ቤተክርስቲያንን ለድርድር እንዳታቀርቡና የእግዚአብሔርን ክብር እንዳታስደፍሩ፣ ቤተክርስቲያንን እንዳታዋርዱ በእጅጉ ተጠንቀቁ!!! ልፋታቹህ ተጋድሏቹህ ሁሉ ከንቱ እንዳይቀር ተጠንቀቁ!!! ለእግዚአብሔር ቀን አይመሽበትምና ታግሳቹህ ጠብቁት፡፡
የምትሹትን ላታገኙ፣ ቤተክርስቲያንም ላትጠቀም፣ እግዚአብሔርን መቅደም ላይቻል ነገር መታገስ አቅቷቹህ እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ!!! በእነሱ ዕዳ እናንተም ተጠያቂ ነው የምትሆኑት ተጠንቀቁ!!! በቀኖና ቤተክርስቲያን መስማማት መግባባት የማይፈልጉ፣ የማይስማሙ ከሆኑና ፍላጎታቸው እንንተንም የቅድስት ቤተክርስቲያንን ቀኖና አስጥሰው፣ አሽረው ማሳትና በነሱው በደል ላይ መጣል ከሆነ ፍላጎታቸው “ፃእ እርኩስ መንፈስ!” ብላቹህ መልሷቸው!!!
መድኃኔዓለም ክርስቶስ የቤተክርስቲያንን ትንሣኤ ያቅርብልን ያሳየን!!! ከአሳሳቾች፣ ከአሰናካዮች፣ ከአርካሾች፣ ከፈታኞች፣ ይሠውረን፣ ይጠብቀን፣ ይታደገን!!! አሜን!!!
ድል ለቅድስት ቤተክርስቲያን!!!
Filed in: Amharic