>

ከዶ/ር አብይ አህመድ የአሜሪካ ዲያስፖራ ውይይት ምን ይገኛል? (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

ከዶ/ር አብይ አህመድ የአሜሪካ ዲያስፖራ ውይይት ምን ይገኛል?
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ሰሞኑን etv የጠቅላይ ሚንስትሩን የአሜሪካ ጉብኝት አስመልክቶ በፕሮፖጋንዳ የታጀበ ዜና በተደጋጋሚ እየሰራ ነው።በዚህ ሂደት ውስጥ ዋነኛ የጉዳዪ ተሳታፊ የሆኑት አካላት ማለትም የዶ/ር አብይ መንግስትና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከውይይቱ ምን ይጠብቃሉ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የውይይቱን ውጤታማነት ለመገመት እድል ይሰጣል።በኔ እምነት የዶ/ር አብይ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የፍይናንስና የፖለቲካ ድጋፍ ለመንግስታቸው ለማድረግ ቃል እንዲገቡና ለተግባራዊነቱ እንዲንቀሳቀሱ መሰራት መጣል ይፈልጋሉ።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በሀገራቸው የሚታየው የለውጥ ተሰፍ ተጠናክሮ በመቀጠል የዴሞክራሲ ተቁዋማት ተገንብተው ሀገራቸው ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ እንድትሸጋገር በዶ/ር አብይ በኩል ለውጡ መዋቅራዊ ቅርፅ እንዲኖረው ሊሰሩ ስለታሰቡ ጉዳዮች ግልፅ ፍኖተ ካርታ እንዲኖር ይፈልጋሉ።በኔ ግምት ከተሳታፊው ብዛትና ከጊዜው ውስንነት አንፃር ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ  በዝርዝር ተወያይቶ ግልፅ አቁዋም ለመያዝ በብዙ ምክንያቶች ከባድ ሊሆን ስለሚችል ሁሉም ወገኖች በመርህ ደረጃ ተስማምተው የዶ/ር አብይ በቀን አንድ ዶላር ፕሮጀት እንደመጀመሪያ የስምምነት ማሳያ ሀሳብ ተወስዶ ተግባራዊነቱን ለመጀመር የሚስማሙ ይመስለኛል።ነገርግን ትንሽ የሚመስልን ቃል ኪዳን አክብሮ ግዴታን መወጣት በኛ ባህል ብዙም የተለመደ አይደለም።ከዚህ በፊት ለሀገር ብዙ የሚጠቅሙ መልካም ሀሳቦችና ተግባሮች ቀላል የሆነውን ግዴታችንን የመወጣት በህል ስለሌለን መክሽፋችንን የሚያሳዩ ብዙ ምሳሌወች አሉ ለምሳሌ ያህል የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባኤ እና ኢሳት እንደዚህ አይነት የፕሮጀክት ሀሳብ አቅርበው  ከላይ በጠቀስኩት ባህላችን ምክንያት ብዙም ውጤታማ አልነበሩም።የዶ/ር አብይም በቀን አንድ ዶላር ሀሳብ ሌሎች ተግዳሮቶች እንደተጠበቁ ሁነው ግዴታችንን በተከታታይና በዘላቂነት የመወጣት ድክመታችን ምክንያት ተግባራዊ ያለመሆን እድሉ ሰፊ ስለሆነ ከባድ ስራ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው ።የተጠየቀው ገንዘብ ቀላል ቢሆንም ችግሩ የአመለካከት ስለሆነ በቶሎ ውጤት ለማምጣት አስቸጋሪ ይመስለኛል።
Filed in: Amharic