>

ወያኔ  ሆይ! ለማያውቅሽ ታጠኝ!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ወያኔ  ሆይ! ለማያውቅሽ ታጠኝ!!  
አቻምየለህ ታምሩ
እነ ነውር ጌጡና ደጋፊዎቻቸው አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የሚሰማቸውን የአማራ ጥላቻ  ዛሬ በመቀሌ  ባካሄዱት ሰልፍ  ከኢትዮጵያ በግፍ ላባረሯቸውና  እንደ እጃቸው መዳፍ ለሚያውቋቸው ኤርትራውያን እንዲህ ሲሉ አሳይተዋል ፤
«ደቄ ኤሬ! አምሓሩ ባሕርኹም ይደልዩ፤ ተጋሩ ፍቕርኹም ንደሊ!!!»
 
ይህ የትግርኛ መፈክር ወደ አማርኛ ሲመለስ፤  
 
«የኤርትራ ልጆ! አማራ ባሕራችሁን ይፈልጋል፤ እኛ ትግራዎች  ግን የምንፈልገው  ፍቅራችሁን ነው!!!» ማለት ነው። 
ጤና ይስጥልኝ እነ ነውር ጌጡ! «የአይናችሁን ቀለም አላማረኝም» ብላችሁ  ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ያባርራችኋቸው ፍቅራቸውን ስለምትፈልጉ ነው? ወያኔ  «የአይናችሁን ቀለም አላማረኝም» ብሎ ኤርትራውያንን ሲያባርር «ከወንድሞቻችን የሚለየን ሞት ብቻ ነው፤ እኛን ገድለው እናንተን ያባሯችሁ» ብለው  ወያኔ የሚያሳድዳቸውን  ኤርትራውያንን የደበቁ አማሮችን በሻዕብያ ሰላይነት ያሰረና  የገደለ ማነው?
ኤርትራውያንን «የአይናቸው ቀለም አላማረኝም» ብላችሁ  ከኢትዮጵያ ሲታባርሩ በእንባ የሸኛቸው ማነው?  የወያኔ  ሰዎች ኤርትራውያን እንዲባረሩ ያሉበትን አድራሻ ሲጠቁሙ  ኤርትራውያን በግፍ እንዳይባረሩ ከለላ የሰጠና የደበቀ ማነው?  ጎጃም ደብረ ማርቆስ ውስጥ ወያኔ ኤርትራውያንን ሲያባርር የኔ ዘመድ የሆነ ሰው ጎረቤቱ የሆነን ኤርትራዊ «ክንዴን ሳልንተራስ አይነኩህም» በማለት ወጀቡ እስኪያልፍ ድረስ ገጠር ዘመዶቹ ጋር ልኮ ከነቤተሰቦቹ አንድ አመት ተኩል ያህል ደብቆት ነበር።  ንብረቱንና ገንዘቡን  ግን  ወያኔዎች ወረሱት።
ከዚህ በተጨማሪስ  ወያኔዎች  የዘረፉትን የኤርትራውያን ንብረት ለኤርትራውያን ለማስመለስ ፍርድ ቤት ድረስ  ቀርቦ የተሟገተላቸው አማራ አይደለምን?  ይህንን  አሁንም ድረስ አስመራ ውስጥ በሕይወት የሚኖረው  ኢታሎ  ቫሳሎ ሊመሰክር ይችላል!  የእግር ኳስ ዶክተሩ አማራው  መንግሥቱ ወርቁ ችሎት ድረስ ቀርቦ የኢታሎ  ቫሳሎን ንብረት ከዘረፉ ወያኔዎች ጋር ፊት ለፊት ተሟግቷል። ምንም እንኳ ሙሉ በሙሉ ባይሳካለትም  መንግሥቱ ወርቁ ግን የቻለውን ያህል ተሟግቶ  ፍርድ ቤቱ  በመጨረሻ ላይ  ለኢታሎ  ቫሳሎ የበየነለትን ንብረቱን  ሽጦ ገንዘቡን  ወደ ሶስተኛ አገር ባንክ እንደላከለት ኢታሎ ቫሳሎ ራሱ  በአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ክፍል  ቀርቦ ተናግሯል።
አማራ  ማንም ያለምንም ምንም እንዲደርስበት አይሻም። ይህ አስተዳደጋችን ነው። ይህ ተፈጥሯችን ነው። እኛ ስናድግ ወገናችን መላው ኢትዮጵያዊ እንጂ ጎሳችን ነው ተብለን አላደግንም።  መታወቅ ያለበት አንድ ነገር ግን አለ። ሊያጠፋን የመጣን ጠላት ግን እስኪጨርሰን ድረስ ዝም ብለን አናየውም። ወያኔ እየበላን እስካሁን ድረስም መዘግየታችንም  አጥፊያችን ልብ ይገዛ እንደሆነ ብለን ነው።
Filed in: Amharic