>

አንድነት በልዩነት መቀራረብ እንጂ ፍፁም መመሳሰል  ሆኖ አያውቅም!!!  (ኦቦ ለማ መገርሳ)

አንድነት በልዩነት መቀራረብ እንጂ ፍፁም መመሳሰል  ሆኖ አያውቅም!!!  
ኦቦ ለማ መገርሳ
ኢትዮጲያዊ ማንነት ከአማራው፣ ከኦሮሞው፣ ከትግራዮ፣
ከሶማሌው …ወዘተ ነው የሚቀዳው ከነዚህ የተነጠለ በራሱ የቆመ ኢትዮጲያዊነት የለም፡፡
 …
በሚኒሶታ የኦሮሞ ባህል ከፍ ብሎ መታየቱ   ክፋት የለውም፡፡ኦሮሞ የኦነግን ባንዲራ መውደዱ ከኢትዮጵያዊነት አያጎለውም፡፡መደመር ራስን ሆኖ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊነት ቀለም እንደ መጡበት ማህበረሰብ ይተረጎማል፡፡
 …
 ተጋሩው ባለኮከቡን ሰንደቅ ይወዳል፡፡መብቱ ነው፡፡
 …
አማራው ና ብዙው ኢትዮጲያዊ ደግሞ አረንጓዴ  ቢጫ ቀዮን ይወዳል፡፡
 …
 ኢትዮጲያዊነት ችግር የሚሆነው የኔው ብቻ ነው ትክክል ማለቱ ላይ ነው፡፡አንድ ህዝብ የሚወደውን መከልከል ነው ጥፋቱ፡፡
 …
 አንዳንዶች ኢትዮጲያን አይረዷትም፡፡ ዥንጉርጉርነቷን መቀበል ግድ ነው፡፡በዥንጉርጉርነቷ ፈካ ብለህ እንድታይ የራስን ባህል ማሳደግ ነው፡፡መደራጀት ነው፡፡
 …
 አንድነት በልዮነት መቀራረብ እንጂ ፍፁም መመሳሰል  ሆኖ አያውቅም፡፡
  …
ለዚህ ነው የአማራ ብሄርተኝነት በመደመር ዘመንም  የበለጠ አስፈላጊ የሚሆነው፡፡ ራስን ረስቶ መደመር የለም፡፡ ራስን ሞልቶ፣የራስን ጥቅም አስከብሮ መደመር  ነው ፡፡ ከዛ ኢትዮጲያን አማራም፣ኦሮሞም እንደራሱ ፍላጎት ይገልፃታል፡፡
 …
 አማራው አረንጓዴ  ቢጫ ቀይ ሲይዝ ህገመንግስት አፈረሰ መባል የለበትም፡፡ አማራ የሚወደውን ሌሎች ሊጠሉት አይገባም፡፡ሊሆኑት ግን  ግድ የለባቸውም፡፡ የኦነግ ባንዲራ የሚያስደስተው መከልከል የለበትም፡፡ ፍላጎቱ እና ስሜቱ ነው፡፡ኢትዮጵያዊነት ፍላጎት መገደቢያ አይደለም፡፡
 ..
 ይልቁንም ለኢትዮጵያዊነት አንድ አይነት ቀለም አለው ብለው   ብሄርተኝነት ሃራም  አድርገው  የሚያወግዙ  ከነባራዊው እውነታ ርቀው   ህልም ላይ ያሉ ሰዎች መታረም እና መንቃት  ይገባቸዋል፡፡
Filed in: Amharic