>

ከፌደራል መንግስት ጋር ጫማ መለካካት የጀመረው የትግራይ ክልል መስተዳድር!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ከፌደራል መንግስት ጋር ጫማ መለካካት የጀመረው የትግራይ ክልል መስተዳድር!!
ቬሮኒካ መላኩ
የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል መለዮ እና አርማ ያደረጉ  መትረጌስን ጨምሮ የተለያየ የጦር መሳሪያየታጠቁ ሰዎችን  አሳፍሮ  የነበረዉ አንቶኖቭ አውሮፕላን ከሱዳን አዲስ አበባ ለመጓዝ አልመዉ በስሕተት መቀሌ አርፈው በቁጥጥር ስር ውለዋል ” 
ይሄ ዜና በቢቢሲና ዶቼ ቬሌ የተዘገበ ነው። ቀኑን ሙሉ ሲከነክነኝም የዋለ ዜና ነው።በግራም በቀኝም ፣በሁለት አንግል ስመለከተው አደገኛ ሆነብኝ። በሁለቱም እሳቤ ትግራይ ክልል በፌደራል መንግስቱ ላይ አደገኛ ጆከር እየሳበ መሆኑን ያመለክታል።
ሲናሪዮ 1 ~ ይሄ አውሮፕላን መነሻው ከሱዳን ሲሆን መድረሻው ደሞ አዲስ አበባ ነው ተብሏል። 
ይሄ አውሮፕላን በማን አገር ስም የተመዘገበ ነው?  
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ አየር ክልል ሲገባ ራዳር እንደት አልተመለከተውም?   መቀሌ ምን ሊሰራ አረፈ?  ይሄኛው ሲናሪዮ ከተመለከትን ትግራይ ክልል ከሱዳን ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላላት መፈንቅለ መንግስት የታሰበ ስለሚመስል ራዳሩም ቢጠናከር   ቦሌን ሳይሆን አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ በደንብ መቆጣጠር እንዳይረሳ ።
ሲናሪዮ 2 ~  መቀሌ አረፉ የተባሉት  ሰዎች ትክክለኛ የፌደራል ፀረ ሽብር ፖሊሶች ከሆኑ ለምን በቁጥጥር ስር ሊውሉ ቻሉ?  በወንጀል ህጉም ሆነ በህገመንግስቱ ከባድ ወንጀሎች ጁሪስድክሽኑ የፌደራል መንግስት እስከሆነ ድረስ ፌደራል መንግስት በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል እየተወረወረ ፀጥታን መጠበቅ ወንጀለኛን መያዝ ይችላል።
ፌደራል ከላይ የተጠቀሰው ህገመንግስታዊ ስልጣን እንዳለው እየታወቀ ለምን በቁጥጥር ስር ማዋል ፈለገ?
ለነገሩ ትግራይ ክልል ፌደራል መንግስቱን መናቅ ከጀመረ ቆየ ። እኔ የምፈራው የትግራይን አለመታዘዝ እየተመለከቱ ሌሎቹም ክልሎች ምሳሌውን በመከተል ፌደራል መንግስትን ጥርስ የሌለው አምበሳና የዘመነ መሳፍን የምልክት አሻንጉሊት እንዳያደርጉት በፍጥነት ፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር የገባውን አጉል መናናቅ ራሱን በማስከበር መቋጨት ለነገ የማይባል የዛሬ ስራ ነው ።
Filed in: Amharic