>

መጀን ! መጀን ! (ቬሮኒካ መላኩ)

መጀን ! መጀን !
ቬሮኒካ መላኩ

* ለካ ይች ኢትዮጵያ የምትባል አገር አልተረፈችም ነበርሳ። ስጋዋን ግጠው በአጥንት ኖሯል ያስቀሩልን
* ለካ መንገድ ዳር የጀበና ቡና የምትሸጥን ምስኪን ሴት ግብር ክፈይ በማለት ረከቦት ” ታሽጓል ” እያሉ የሚፅፉበት ስርአትና የሸጠቻትን የስኒ ቡና ብር መቀነት ፈትተው በግብር መልክ የሚዘርፉት ።
* በእንጨት ጭስ አይኗ እየተለበለበች እንጀራ ጋግራ የምትሸጥን ምስኪን እናት ካሽ ሪጅስተር ካልገዛሽ እያሉ አንገቷን አንቀው ግብር የሚሰበስቡት።ለዳንኤል ብርሃነና ለዳዊት ከበደ ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሚሊዮን ብር በአመት ለመክፈል ነበር።

አቃቢ ህግ ዛሬ ከኢትዮ ቴሌኮምና ከፖስታ አገልግሎት ድርጅት ህዝብን ከህዝብ ለማባለት ” በየአመቱ ለዳንኤል ብርሃነና ለዳዊት ከበደ በአመት ለእያንዳንዳቸው የሚከፍለውን አንድ አንድ ሚሊዮን ብር ደመወዝ አቋርጫለሁ ” አለ አሉ ።ኦ ክርስቶስ! !!

ለካ ይች ኢትዮጵያ የምትባል አገር አልተረፈችም ነበርሳ። ስጋዋን ግጠው በአጥንት ኖሯል ያስቀሩልን
እኔ እኮ እዚህ ፌስቡክ ላይ ዳንኤል ብርሃነና ዳዊት ከበደ ባለፉት 3 ወራት እንደ ክረምት ዝናብ 24 ሰአት ከአይናቸው በእንባ መልክ ውሃ ሲንዤቀዤቅ ከአዲሱ መንግስት ጋር የብሄር ቅራኔ ብቻ ያለባቸው ይመስለኝ ነበር ለካ ቅራኔው የብሄር ብቻ ሳይሆን የመደብ ቅራኔም ጭምር ነበር ።
ለእኛ ነው እንጅ ይሄ ለውጥ ሪፎርሜሽን የሚባለው ለእነሱማ እንደ 1966ቱ አቢዮት በህዝቡ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ደሙን ይመጡ የነበሩትን መዥገሮች እስከ መጨረሻው ድረስ ፋይሉ የዘጋ ስር ነቀል ለውጥ ነው።ለዚህ ነው ለካ ሰማዩ የተደፋባቸው። ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን ።

Filed in: Amharic